>
5:33 pm - Sunday December 5, 4275

በጥበበ ግዮን ሆስፒታል በስራ ላይ እንዳለ የታፈነው ፕ/ር ዶር የሺጌታ ገላው  በጥቂቱ...!!!  አማራ ሚድያ ኔትዎርክ

በጥበበ ግዮን ሆስፒታል በስራ ላይ እንዳለ የታፈነው ፕ/ር ዶር የሺጌታ ገላው  በጥቂቱ…!!! 

አማራ ሚድያ ኔትዎርክ

ፕ/ር የሺጌታ ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል እስኪማሩ አንደኛ ደረጃ እየያዙ ያለፉ እና በድሮው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በዳሞት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የመጀመሪያ የሆነውን ሁሉንም ት/ት A በማምጣት ጅማ ዩንቨርስቲን የህክምና ትምህርትን ተቀላቅለዋል።

ፕ/ር የሺጌታ በዶክተሬት ዲግሪ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ የወርቅ ሜዳሊያ በመሸለም ተመርቆ እዛው ጅማ ዩንቨርስቲ በመምህርነትና በተለያዩ ኃላፊነቶች አገልግሏል፡፡

ፕ/ር የሺጌታ ከተመረቀበት 1995 ጀምሮ የተለያዩ ጥናቶች ላይ ሙሉ ግዜውን በማሳለፍ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ በወጣትነቱ ሙሉ ፕሮፌሰርነት ለማግኘት ችሏል፡፡

በምስራቅ አፍሪካ በዓይን ህክምና ስፔሻላይዝ በማድረግ ሙሉ ፕሮፌሰርነት ደረጃ የደረሰ ብቸኛ ኢትዮጵያዊ ነው።

በአሁኑ ሰአት የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዳይሬክተርና የባህ ዳር ዪንቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ሆኖ እያገለገለ ሲሆን ሆስፒታሉ ያለበትን በርካታ ችግር በአመራር ጥበብ በመበጣጠስ ሆስፒታሉ ዛሬ ለደረሰበት ደረጃ ደርሷል።

በነገራችን ላይ የሆስፒታሉን ስም “ጥበበ ግዮን” የሚለውን ስም ያወጣው ራሱ ፕሮፌሰር የሺጌታ ሲሆን ስሙም በባህር ዳር ዩንቨርስቲ ሴኔት እንዲፀድቅ ተደርጓል።

ላልተማሩ የብአዴን ጎጠኛ መሀይሞች አፈናው አቁመው ፕሮፌሰሩን ወደ ቦታው እንዲመልሱት አሁንም እናሳስባለን።

https://t.me/amnmedia24

Filed in: Amharic