>

አፈናው ቀጥሏል ... !!! (መስከረም አበራ)

አፈናው ቀጥሏል … !!!

መስከረም አበራ


አሁን ደግሞ ተራው የመተከል አማራ ወሰንና ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ የቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት  (ፎቷቸውን ከታች የምትመለከቱት) አቶ እንዳለው አዲስ ሆኗል፡፡ አቶ እንዳለው  በ02/09/2014ዓም ከተወሰደ በኋላ ክስ ሳይመሰረትበት በጃዊ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ ከቆየ በኋላ ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረ ሲሆን የቀረበበት ክስ የመተከል አማራ ወሰንና ማንነት አስመለሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነው የሚል ስለነበረ ፍርድቤቱ ይህ ጥፋት ሆኖ አያስከስም ሲል በነፃ ቢያሰናብተውም ፖሊስ ሊለቀው አልፈቀደም፤ይልቅስ አፍኖ ወዳልታወቀ ስፍራ እንደወሰደው የትግል አጋሮቹ የኮሚቴው አባላት  ነግረውኛል፡፡

በተመሳሳይ በባህር ዳር የአብን አባላት እየታደኑ እየታፈኑ ነው! ታጋይን እንጅ ትግልን ማፈን አይቻልም……..

የቀጠለ

አልቻሉም እንጅ።ለማንኛውም ነገ እኔ ብሞት ህዝብ ማወቅ ያለበት ለዕውነት ብቻ መሆኑን ነው” ብሏል።

በየጊዜው በፋኖ ላይ የሚደርሰው እንግልት እና ውክቢያ እየተጠናከረ ቢመጣም፣ ሰለ አካባበው ሰላም ስንል መታገስን መርጠናል ብለዋል።

በተያያዘ:-

የባህር ዳሩ ኘሮፌሰር የሺጌታ ገላው ታሰሩ!

# በቡሬ ከተማ የአማራ ህዝባዊ ኃይል(ፋኖ) ወታደራዊ አመራር ታዬ ብርሃኑ ቤት በጥይት ተደበደበ !

የፋኖ ጠበቃ አስረስ ማረ ቤት በሕገ ወጥ ሂደት ተበረበረ!

በአማራ መስተዳድር፤ ምዕራብ ጎጃም ዞን፤ ቡሬ ከተማ የአማራ ሕዝባዊ ሃይል (ፋኖ) ወታደራዊ ዘርፍ ሓላፊ የፋኖ ታዬ ብርሃኑ መኖሪያ ቤት በአገዛዙ በጥይት ተደብድቧል።

ቤቱ የተደበደበው ትናንት እሁድ ግንቦት 7 ቀን 2014 ዓ.ም. ሌሊት ለዛሬ አጥቢያ ሲሆን፣ ባለቤቴ እና ልጆቹ በውስጥ ነበሩ። የቤቱ በር መስታዎት  ተሰባብሯል።

በአሁኑ ሰዓት አመራሩን እያደኑት ይገኛሉ። ተኩስ በተከፈተበት ሰዓት በቤት ውስጥ አልነበረም።

በተመሳሳይ የአማራ ሕዝባዊ ሃይል (ፋኖ) ከፍተኛ የአመራር አባል የሆነው የጠበቃ አስረስ ማረ ዳምጤ መኖሪያ ቤት ትናንት እሁድ ግንቦት 7 ቀን 2014 ዓ.ም. ተበርብሯል። ቤቱ የተበረበረው ከ25 በላይ በሚሆኑ ወታደሮች ነው። ቤቱን የበረበሩት የፍርድ ቤት ማዘዣ ሳያሳዩ ነው። ለውንጀላ የሚያበቃቸውን ቁስ አላገኙም። ይሁን እንጂ የፋኖና ጠበቃ አስረስን ቤተሰቦች ወደ ፖሊስ ጣቢያ ወስደው በማገት ሲያጉላሏቸው ከዋሉ በኋላ ለቀዋቸዋል።

አስረስ ማረ ዳምጤ ለረዥም ዓመታት ለፖለቲካ እስረኞች ጥብቅና በመቆምና በመከራከር ይታወቃል። አስረስ ከጥብቅናው በተጨማሪ በአማራ ሕዝባዊ ሃይል (ፋኖ) የአመራር ተሳትፎ ያደርጋል።

የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር የሺጌታ ገላውም “ፋኖን ትደግፋለህ” በሚል በባህር ዳር ዘጠነኛ ፖሊሰ ጣቢያ መታሰራቸውነ‍እ ንስር ብሮድካስት ዘግቧል።

Filed in: Amharic