>

ሕዝባዊ አመጽ እየተቀጣጠለ እየመጣ ነው...!!! (አስማረ ዳኘ)

ሕዝባዊ አመጽ እየተቀጣጠለ እየመጣ ነው…!!!

አስማረ ዳኘ

*…. ሰው ብቻ አይደለም እየታፈነ ያለው፤ ፋኖነት ብቻ አይደለም እየታፈነ ያለው፤  ንቁ የማህበረሰብ ቁንጮዎች ብቻም አይደሉም እየታፈኑ ያሉት፤ የፋኖ ካንፕም አይደለም እየታፈነ ያለው፤  ሚድያ ብቻም አይደለም እየታፈነ ያለው።
ነፃነት፣ ማንነት፣ ክብርና ታሪክ ነው እየታፈነ፣ እየተሳደደና እየተገደለ ያለው።  የነፃነት ታጋይ ፖለቲከኛህን፣ የማንነት አቀንቃኝ ወንድሞችህን፣ ክብርህን አስጠባቂ ፋኖህን፣ ክብርህን አስቀጣይ ወገንህን፣ ታሪክህን ነቃሽ ሙህራንህን እያፈነ #ነገ ነፃነትህን ገርስሶ ማንነትህን ደልዞ፣ ክብርህን አዋርዶ፣ አቅመ ቢስ አድርጎ ሊገዛህ እንጅ  እውነት ህግ ማስከበር አይምሰልህ❗❗
 
የአማራ ህዝብ ፋኖን አትንኩብኝ ካለ፣ ህግ የሚከበረው ለማን ነው❓ለህዝብ ወይስ ለገዢው ስርዓት ደህንነት?
በቃ በል❗
የበላይ ዘለቀ አገር ለኦህዴድና ተላላኪው አፋኝ ቡድን እረመጥ ሆኖ እንደቀጠለ ነው !!
1. የወጣቱ ቁጣ ጫፍ ላይ የደረሰ ቢሆንም አንድም ቦታ ላይ ጉዳት አላደረሰም:: ቁጣውን በሰለጠነና ጨዋ በሆነ መንገድ እየገለፀ ነው::
2. የአማራ ልዩ ሀይልና ህዝባዊ ፖሊስ ወደህዝባችን አንተኩስም ብሎ ከህዝብ ጎን እንደቆመ ነው:: የብልጽግና ካድሬው በየጉሬው ተደብቆ ርምጃ ውሰዱ እያለ ቢወተውትም የህዝብ ልጅ የሆነው የአማራ ልዩ ሀይል የህዝብ ልጅ መሆኑን አስመስክራል::
May be an image of 1 person, standing and road3. አሳምነው አሳምነው
አማራ ነው አማራ ነው:
አማራ ልዩ ሀይል የፋኖ ወንድም
አብይ አህመድ ኦነግ ሸኔ ነው
ብልጽግና አማራን በላ
ጀነራል ተፈራ ቀና ብሎ ሲያይ የሚያስፈራራ
ብአዴን አሽከሩ የአብይ ፈረስ ነው::
ፋኖ ማለት አማራ፣ አማራ ማለት ፋኖ ነው
ከክፉ ስርዓት አልፈን አውሬ ስርአት ላይ ደርሰናል::
ጀኔራል ተፈራና ሌሎች በየአካባቢው የታፈኑ የአማራ ልጆች ባስቸኮይ ይፈቱ::
በሞጣ ላይ ሽብር ያወጀው ብልጽግና ነው::
እያለ ተቃውሞውን እየገለፀ ነው::
በመርጦለማያም ግንደወይን: የጁቤ: ፍኖተ ሰላም : አዴት በጠቅላላው የጎጃም ህዝብ ተገቢውን ምላሽ እየሰጠ ይገኛል!!
አማራ ሆይ ምቢ በል!
መሪዎችህን አላስነካም በል::
Filed in: Amharic