>

በዘመነ ካሤ የአማራ ህዝባዊ ላይ ተኩስ ተከፍቷል!! (ባልደራስ)

በዘመነ ካሤ የአማራ ህዝባዊ ላይ ተኩስ ተከፍቷል!!

ባልደራስ


*…. የመርዓዊ ከተማ ኗሪ በተቃውሞ ጫካ እየገባ ነው፣

*…. በሞጣ ንፁሃን ተገድለዋል!!

የአማራ ሕዝባዊ ሃይል (ፋኖ) ሰብሳቢ በሆነው ፋኖ ዘመነ ካሤ ላይ ተኩስ ተከፍቶበታል። በምዕራብ ጎጃም ዞን፤  ሰሜን ሜጫ ወረዳ መርዓዊ አካባቢ ነው ዛሬ አርብ ግንቦት 12 ቀን ማለዳ ተኩሱ የተከፈተው።

የመርዓዊ ኗሪ በአሁኑ ጊዜ በቁጣ ወደ አደባባይ ወጥቷል። ከፊሉም ወደ ካጫ እየገባ ነው።

በተመሳሳይ፣ በምራቅ ጎጃም፤ ሞጣ ውጥረት ነግሷል። ባዶ እጃቸውን የወጡ ንፁሃን ከአገዛዙ ወታደሮች በተተኮሰ ጥይት  ተገድለዋል። ከፊሎች ቆስለዋል። ተጨማሪ ሰራዊት እየገባ ነው። ጥቃቱ የከባድ መሳሪያ ተኩስ የተሰማበት ነው።

Filed in: Amharic