>
5:33 pm - Wednesday December 5, 7866

ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬን አፍነው ወስደውታል...!!! (ምኒልክ ሳልሳዊ)

ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬን አፍነው ወስደውታል…!!!

ምኒልክ ሳልሳዊ


*… እሕቱን እንደ ማገቻ ይዘው አይተው  ለቀዋታል…!!!

ከትላንት ክትትልና አፈና  የተረፈው ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬ ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ ስድስት የደሕንነት አባላት ቤቱን በማንኳኳት አልከፍት ሲላቸው ደጋግመው ሲያኳኩም ባለመከፈቱ እሕቱን አፍነው በመውሰድ ፖሊስ ጣቢያ አቆይተዋት በስተመጨረሻ የእሕቱን መታፈን ሲሰማ ከታናሽ ወንድሙ ጋር ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሲወጣ ተከታትለው በመያዝ ስልኩን ቀምተው አፍነው ወስደውት እሕቱን ፈተዋታል። ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬ ስልኩ ቢሰራም የሚያነሳው የለም።

“ፋኖ ያስፈልገናል የበለጠ ይደራጅ…!!!”

https://youtu.be/KPdTyyiI_Jk

በሚል ርእሰ ጉዳይ የሰጠው ትንታኔ ከወቅታዊ ሁኔታው ጋር ተያይዞ ለመታፈኑ እንደ ምክንያት ይነሳል።

ሰለሞን ሹምዬ በአሁኑ ወቅት

” ገበያ ኑ ” የሚባል የዩቲዩብ ቻናል ያለው ሲሆን “ቡና እና ሻይ” የሚል ፕሮግራም በቴሌቭዥን ያዘጋጅ ነበር።

Filed in: Amharic