>

የጋዜጠኛ መምህርት መስከረም አበራ ፍርድ ቤት ቀረበች...!!! (ይድነቃቸው ከበደ)

የጋዜጠኛ መምህርት መስከረም አበራ ፍርድ ቤት ቀረበች…!!!

ይድነቃቸው ከበደ


*….  “የዐማራ ክልል ከፌደራል መንግስት ለመነጠል ገንዘብ ተከፍሏት እየሰራች ነው…!!! ”

*  …..በፋኖ እና በፌዴራል መንግስት መካከል  እምነት እንዳይኖር ቅስቀሳ አድርጋለች…..!

ፖሊስ

ዛሬ ግንቦት 15 ቀን 2014 ዓ.ም ጠዋት በዋለው ችሎት መምህርት መስከረም አበራ ከጠበቆቿ ሔኖክ አክሊሉ እና ሰለሞን ገዛኸኝ ጋር ፤

የፌ/የመ/ደ/ፍ/ቤት አራዳ ምድብ 2ኛ የጊዜ ቀጠሮ የወንጀል ችሎት ተገኝቷል ።

ፖሊስ በችሎት እንደገለጸው ” መስከረም አበራ የተለያዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም ሁከት እና ብጥብጥ እንዲነሳ በማድረግ ፤ የዐማራ ክልል ከፌደራል መንግስት ለመነጠል ገንዘብ ተከፍሏት እየሰራሽ ነው ። እንዲሁም በፋኖ እና በፌዴራል መንግስት መካከል  እምነት እንዳይኖ እና ቅሬታ እንዲፈጠር ቅስቀሳ እያደረገች ነው። ይህን በመሆኑ ፤ ተባባሪ አባሪዎችን ለመያዝ ፣ የኤልክትሮኒስ ማስረጃቸውን ምርመራ ለማከናወን ፣ ምስክሮችን ለማሰባሰብ ፤ ተጨማሪ የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ይሰጠን በማለት ” ለፍርድ ቤቱ ጥያቄ አቅርቧል ።

የጋዜጠኛ መምህር መስከረም አበራ ጠበቆች ለፖሊስ በሰጡት ምላሽ የሕግና የፍሬ ነገር ክርክር ያካሄዱ ሲሆን ፤ የሕግ ክርክሩን በተመለከተ ፦

“ተጠርጣሪ ጋዜጠኛ ስለሆነች እና ወንጀሉም ተፈፀመ የተባለው በሚዲያ እንደመሆኑ መጠን ፤ ፖሊስ ተፈጸመ ያለው ወንጀል በመገናኛ ብዙሃን  መደበኛው የጊዜ ቀጠሮ ሳይሰጥ ለዐቃቤ ሕግ ተመርቶ ክስ ይመሠረትበታል እንጂ የምርመራ ጊዜ የሚጠየቅበት ስርዓት የለም።

እንዲሁም ለቀጠሮ መጠየቂያ ምክንያት የሆኑት ነገሮችም ገና ወንጀል ስለመፈፀሙ ለማጣራት እንጂ ፓሊስ ምንም ዓይነት የተፈፀመ ወንጀል ስለመኖሩ ማስረጃ ኖሮት አይደለም፤ ተጠርጣሪዋ አየር መንገድ ላይ ሳይሸሸጉ በነፃነት ሲንቀሳቀሱ መያዛቸው ንፁህ መሆናቸውን የሚያሳይ ነው።

ወ/ሮ መስከረም ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብታቸውን ተጠቅመው ስርዓቱን በመሞገታቸው ለማሸማቀቅ የቀረበ እስር እንጂ ፤ ለእስር የሚዳርግ

ተግባር ፈፅመው አይደለም ። በተጨማሪ የ7ወር አራስ መሆናቸውን ታሳቢ በማድረግ የዋስትና መብታቸውን ሊከበር ” ይገባል በማለት ተከራክረዋል ።

ፍርድ ቤት የገራና ቀኝ ክርክር ከሰማ በኋላ በጉዳዩ ላይ ብይን ለመስጠት ለነገ ግንቦት 16 ቀን 2014 ዓ.ም. ጠዋት 3፡30 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል

Filed in: Amharic