እጅ አልባን መንግስት ማንም አይጠመዝዘውም…!!!”
አሳዬ ደርቤ
➜የመንግሥትን ቆራጥ ውሳኔ ሲጠብቁ የነበሩ የሰሜን እዝ አባላት ግብዓተ መሬታቸው ተፈጽሟል፡፡
➜የመንግሥትን ትዕዛዝ ሲጠብቁ የነበሩ የምዕራብ እዝ አባላት በላካቸው አካል ዳተኝነት በሕዝብ ተገድለዋል፡፡ የተወሰኑትም ተማርከዋል፡፡
➜በመንግሥት ፉከራ ተማምነው ህውሓትን ሲታገሉ የነበሩ አንዳንድ የአድግራትና የመቀሌ ተወላጆች መንግሥት ባደረገው የተናጠል ተኩስ አቁም ያለምንም ማስጠንቀቂያ ሜዳ ላይ ጥሏቸው ስለወጣ ለሞትና ለስዴት ተዳርገዋል፡፡
➜በመንግሥት ቃላት እና በአካባቢው በሚያየው ሠራዊት እምነት አሳድሮ የተቀመጠው የኮሮም እና የራያ ሕዝብ ባላሰበው ቅጽበት በተፈጸመበት ክህዴት ከአሸባሪው እጅ እንዲወድቅ ተደርጓል፡፡
ስለሆነም…
ዛሬ ባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ ወልድያ፣ ደብረ ብርሐን፣ ፍኖተ ሰላም፣ ደብረ ማርቆስ፣ ወረታ፣ አዲስ አበባ…. ተቀምጠህ በዚህ መንግሥት ንግግርና ዲስኩር ተስፋ የምታደርግ አማራ የነገ እጣ ፈንታህ ከላይ ከተዘረዘሩት ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡
የሰሞኑን እንኳን ብትመለከት በከባድ መስዋዕትነት ከእጅህ ውስጥ የገቡ ድሎችን የሚያሳጣህ መንግሥት የምትለው አካል እንጂ ህውሓት እንዳይመስልህ፡፡
እናም ስለ አገር ቀጣይነት ማሰቡን እና የመንግሥትን መግለጫ መጠባበቁን ትተህ የእራስህን ሕልውና በእራስህ እጅ ለማስከበር ማቄን ጨርቄን ሳትል መነሳት አለብህ፡፡
➜አባቶቻችንን ለኢትዮጵያ ህልውና ማይጨውና ካራማራ ላይ ተሰውተዋል፡፡
➜ወንድሞቻችን ለትግራይ መሬት ባድሜና ሽራሮ ላይ አልፈዋል፡፡
➜እኛ ደግሞ ለእራሳችን ማንነት፣ ለእራሳችን ቀጣይነት ብሎም ለእራሳችን መሬት ወልቃይትና ራያ ላይ ታግለን ድል እናደርጋለን፡፡