“የኦህዴድ ብልጽግና ማፈሪያ “መንግስት” ፋኖ አባቱን ለመያዝ ህጻን ልጁን አገተ…!!!”
አሻራ ሚድያ
*…. ፋሺዝም በተግባር
የየጁቤው ፋኖ አበባው እምቦቃቅላ ሕፃን ልጅ አባትህን አምጣ ተብሎ ታሰረ።
ፋኖው አባ ኮስትር በላይ የሚፋጅ ክንዱ ቢያርመጠምጠው ልጁን የሻሽ ወርቅን አፍኖ መደራደሪያ ሊያደርጋት ሞክሮ አልኾነለትም። የዛሬው ፋሺዝም ለኩረጃ እንጅ ለመማር ጊዜ የለውም።
በምስራቅ ጎጃም ዞን የጁቤ ከተማ ኗሪ የሆነውፋኖ አበባው እጁን ለመንግስት እንዲሰጥ ለማስገደድ በፎቶው ላይ የሚታየውን ህፃን ልጁን የመንግስት የፀጥታ ሃይል ይዞታል ::
በሰሞኑ የብልፅግና እመቃ ጎጃም ውስጥ የመንግስትን ህገወጥ እስር በመቃወም እጅ አንሰጥም ስላሉ በመያዣነት የተፍላጊ ሚስቶች ፣ ወላጆች ፣ ወንድም እና እህቶች ተይዘው ታስረዋል :: ዛሬ ደግሞ ህፃን ልጅ ::
ይሄን ግፍ ነው የምንቃወመው ::
ፋኖ መቶ አለቃ አበበ ለአሻራ ሚዲያ እንደገለፁት ስለ ሴቶች እና ስለህፃናት መብት መከበር ብዙ የሚወተውተው መንግስት እናትና ልጅ ባልሽ ፋኖ ነው ባልሽን ካላመጣሽ በሚል የመሐይም አስተሳሰብ አስሮ እያሰቃያቸው ይገኛል ብለዋል። በባሶሊበን ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ከገቡ 4 ቀን ሆኗቸዋል።ይኸው ይመራል ያስተዳድራል የተባለ መንግስት ህፃን አስሮ ያሰቃያል። የአማራ ህዝብ ይህንን ጉድ ማወቅ አለበት ብለዋል።
እያጣራ የሚያስረው መንግሥት እዚህ ደርሷል።