>

በጎጃም ብቻ ከ1000 በላይ ወጣቶች ጫካ መግባታቸውን ፋኖ አስረስ ማረ ገለፀ!!

 

• በጎጃም ብቻ ከ1000 በላይ ወጣቶች ጫካ መግባታቸውን ፋኖ አስረስ ማረ ገለፀ!!

ሰሜን አሜሪካ ባልደራስ

• በተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች ድሮኖች እያንዣበቡ ናቸው!

 

በጎጃም ብቻ ከ1000 በላይ ወጣቶች ወደ ጫካ ገብተው ራሳቸውን ከመንግስታዊው አፈና እየተከላከሉ በመሆኑ፣ በአርሶ አደሩ የእርሻ ስራ ላይ ከፍተኛ እንቅፋት ፈጥሯል ሲሉ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተለው ፋኖ አስረስ ማረ ዳምጤ ገለፀ።

ፋኖ አስረስ ማረ የአማራ ህዝባዊ ኃይል (ፋኖ) አመራር አባል ሲሆን፣ አሁን በመሳደድ ላይ ይገኛል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፣ በምስራቅ ጎጃም ዞን፤ ሞጣ ከተማ የታሰሩ ዜጎች “ፋኖዎች ናችሁ” በሚል በፖሊስ እየተደበደቡ መሆኑን ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል። የአማራ ሕዝብ፣ የሰብዓዊ መብቶች ክትትል ተቋማት እና ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ጉዳዩን እንዲያውቀሐትም ጥሪ አቅርበዋል። በአካባቢው ፋኖዎችን ፈልጎ ማግኘት ያልቻለው የአገዛዙ አፋኝ ቡድን፣ በንፁሃን ዜጎች ላይ ወከባ እና ድብደባ እያደረሰ ይገኛል።

በተያያዘ፣ በተለያዩ የዐማራ ክልል አካባቢዎች ድሮኖች በሰማይ ሲያንዣብቡ እንደታየለ የዓይን እማኞች ተናግረዋል።

ዘገባ——ሰሜን አሜሪካ ባልደራስ

Filed in: Amharic