>

ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ከ80 በላይ ሰዎች በኦነግ ሸኔ ተገደሉ...!!! (ጎበዜ ሲሳይ)

ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ከ80 በላይ ሰዎች በኦነግ ሸኔ ተገደሉ…!!!

ጎበዜ ሲሳይ

በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ በምትባል ቀበሌ ዛሬ ሰኔ 11 /2014 ዓ/ም  ከ80 በላይ ሰዎች በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መገደላቸውን እና ከመቶ በላይ ነዋሪዎች ታግተው መወሰዳቸውን የሟች ቤተሰቦች ለአማራ ድምፅ ገልፀዋል።

በቀበሌዋ  ጃተማ(ስልሳ) ፣ጨቆርሳ እና ጉትን በተባሉ አካባቢዎች የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ ከ80 በላይ ንፁሀንን መግደላቸውንና በርካታ ሰዎችን አፍነው ወደ ጫካ ይዘዋቸው እንደሄዱ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

የሟቾች ቁጥር ከዚህ በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችልም   ለአማራ ድምፅ ገልፀዋል።

https://youtu.be/IOo0HzcTYPY

Filed in: Amharic