>

የጭራቅ አሕመድ የሰቆቃ ዘመን ለምን ረዘመ? (መስፍን አረጋ)

የጭራቅ አሕመድ የሰቆቃ ዘመን ለምን ረዘመ?

መስፍን አረጋ


ጭራቅ አሕመድ ስልጣን በያዘ ባንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በአማራ ሕዝብ ላይ የፈጸማቸው ወንጀሎች የሞት ፍርድ ቢቀርለት እንኳን ዓለም በቃኝ ሊያስወረውሩት ከበቂ በላይ ነበሩ፡፡  በተቃራኒው ግን ጭራቅ አሕመድ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈጽመውን ወንጀል ይበልጥና ይበልጥ እያከበደ፣ በአማራ ሕዝብ ላይ ይበልጥና ይበልጥ ጭራቅ እየሆነ አምስት ዓመታት ለመድፈን ተቃረበ፡፡  ስለዚህም ዋናውና አንገጋቢው ጥያቄ የጭራቅ አሕመድ የሰቆቃ ዘመን ከስድስት ወራት በላይ ለምን ረዘመ የሚለው ነው፡፡  

ኢትዮጵያዊነትን ለማታለያነት እየሰበከ የመጣውን ጭራቅ አሕመድን ሆ ብሎ ቤተመንግስት ያስገባው የኦሮሞ ወይም የትግሬ ሕዝብ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያዊነቱን ከአማራነቱ በላይ የሚያስቀድመው የአማራ ሕዝብ ነው፡፡  ስለዚህም አማራን በመግደል ኢትዮጵያዊነትን እየገደለ ያለውን ጭራቅ አሕመድን ከቤተመንግስት ሆ ብሎ የሚያስወጣው የኦሮሞ ወይም የትግሬ ሕዝብ ሳይሆን የአማራ ሕዝብ ነው፡፡  በመሆኑም  የጭራቅ አሕመድ የሰቆቃ ዘመን ለምን ረዘመ የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ የአማራን ሕዝብ ስነልቦና መረዳት ያስፈልጋል፡፡

የአማራን ሕዝብ ከቀሩት ኢትዮጵውያን ጋር በተለይም ደግሞ ከአሮሞና ከትግሬ ጋር የሚለየው አንድ ትልቅ ቁምነገር አለ፡፡  ይሄውም፣ አማራ ቅድሚያ የሚሰጠው ላመራር እንጅ ለዘር አለመሆኑ ነው፡፡  ኦሮሞ በኦሮሞነቱ ዙርያ ሊሰባሰብ ይችላል፡፡  ትግሬም በትግሬነቱ ዙርያ ሊሰባሰብ ይችላል፡፡  አማራ ግን በአማራነቱ ዙርያ ለመሰባሰብ እጅግ በጣም ይከብደዋል፣ ምንም እንኳን የጭራቅ አሕመድ ጭራቅነት ሳይወድ በግዱ እንዲሰባሰብ እያደረገው ቢሆንም፡፡

የአማራ ሕዝብ የረጅም ዘመን መመርያ ተመልከት ዓላማህን ተከተል አለቃህን ነው፡፡  የአማራ ሕዝብ ያንድን ግለሰብ አመራር እስከወደደው ድረስ የግለሰቡ ዘር ዴንታ አይሰጠውም፡፡  የአማራ ሕዝብ እድሜ በጠገበው አስተዳደራዊና ባህላዊ ትውፊቱ ሳቢያ ተዋረዳዊነት (hierarchy) ከደሙ ጋር የተዋሃደ ሕዝብ ነው፡፡  በመሆኑም መሪ በአማራ ሕዝብ ዘንድ የሚጫወተው ሚና፣ በኦሮሞ ወይም በትግሬ ሕዝብ ዘንድ ከሚጫወተው ሚና እጅግ የበለጠ ብቻ ሳይሆን ወሳኝ ነው፡፡  ከኦሮሞና ከትግሬ ሕዝብ በተለየ ሁኔታ የአማራ ሕዝብ የሚነሳውም የሚወድቀውም በመሪ ነው፡፡   

በዚህ ረገድ የአማራ ሕዝብ በንብ ሊመሰል ይችላል፡፡  እያንዳንዷ ንብ ብርቱ ተናዳፊ ብትሆንም፣ ንብን ንብ የሚያደርጋት አውራዋ ነው፡፡  በተመሳሳይ መንገድ እያንዳንዱ አማራም ብርቱ ነፍጠኛ ቢሆንም፣ አማራን አማራ የሚያደርገው መሪው ነው፡፡  የኦሮሞንና የትግሬን ሕዝብ በግብታዊነት ሆ ብሎ እንዲነሳ ማድረግ እንደሚቻለው፣ የአማራን ሕዝብ በግብታዊነት ሆ ብሎ እንዲነሳ ማድረግ አይቻልም ባይባልም በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡  ስለዚህም የአማራ ሕዝብ ሆ ብሎ በመነሳት ጭራቅ አሕመድን ከጫንቃው ላይ አውርዶ አሽቀንጥሮ እንዲጥለው ለማድረግ ሆ ብሎ የሚያስነሳው መሪ የግድ ያስፈልገዋል፡፡  

ጭራቅ አሕመድ እስከመጣበት ጊዜ ድረስ፣ የአማራ ሕዝብ ኢትዮጵያን እወዳለሁ ወይም ኢትዮጵያ ሱሴ ናት የሚልን ሁሉ በንግግሩ ብቻ የሚወድ የዋህ ሕዝብ ነበር፡፡  ጭራቅ አሕመድ ግን የአማራ ሕዝብ ለኢትዮጵያ ያለውን ስስ ልብ፣ አማራን ለማታለያነት ተጠቀመበት፡፡  በዚህም የአማራ ሕዝብ ለኢትዮጵያዊነት የነበረውን የዋህነት ድምጥማጡን አጠፋው፡፡  በንግግር ብቻ ተደልሎ አደባባዮችን ያጨናንቅ የነበረው የአማራ ሕዝብ በተግባር ካላሳያችሁኝ ብሎ በየቤቱ አደፈጠ፡፡  ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያየ እያሉ በመስበክና በመዝፈን ብቻ የአማራን ሕዘብ በነቂስ ማስነሳት ከጭራቅ አሕመድ በኋላ አከተመ፡፡      

 

  

አምላኩን የኢትዮጵያ አምላክ የሚለው፣ ኢትዮጵያዊነት ሐይማኖቱ የሆነው የአማራ ሕዝብ፣ ጭራቅ አሕመድን በመሳሰሉ፣ አማራን ለማታለል ሲሉ ብቻ ኢትዮጵያዊነትን በሚሰብኩ አያሌ ሐሳዊ ሰባኪወች ላያሌ ግዜ ተክዷል፡፡  ስለዚህም ካሁን በኋላ ለኢትዮጵያ (ስለሆነም ለአማራ) ቁሚያለሁ የሚልን ማናቸውንም ግለሰብ ወይም ቡድን የአማራ ሕዝብ የሚያምነው እውነትም ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊነት የቆመ መሆኑን በተግባር ሲያረጋግጥ ብቻ ነው፡፡ 

ለአማራ ሕዝብ በመቆም ለኢትዮጵያዊነት መቆምን በተግባር ማረጋገጥ የሚቻለው ደግሞ የአማራን ሕዝብ በሚጨፈጭፉትና በሚያስጨፈጭፉት የጭራቅ አሕመድ ኦነጎችና ብአዴኖች ላይ  በተለይም ደግሞ በቀንደኛወቹ ላይ ርምጃ በመውሰድና ለተወሰደው ርምጃ ሙሉ ሃላፊነትን በይፋ በመውሰድ ነው፡፡  ይህን የሚያደርግን ቡድን ወይም ግለሰብ የአማራ ሕዝብ መሪየ ብሎ በነቂስ እንደሚከተለው ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡  የአማራን ሕዝብ ሆ ብሎ እንዲነሳ በማድረግ የጭራቅ አሕመድን የሰቆቃ ዘመን ማሳጠር የሚቻለው በዚህና በዚህ መንገድ ብቻ ነው፡፡ 

   ግራኝ አሕመድ ዛንተራ ላይ ወደቀ፡፡  ጭራቅ አሕመድስ የሚወድቀው የት ይሆን?  ሰንጋተራ?    

 

መስፍን አረጋ

mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic