>

ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው ባለሥልጣናትን በመግደል ሙከራ በውሸት ተወጀለ

ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው ባለሥልጣናትን በመግደል ሙከራ በውሸት ተወጀለ

•ሦስት የባሕር ዳር ፋኖዎችም በተመሳሳይ ተወንጅለዋል!

ጌጥዬ ያለው

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የሚዲያ ክፍል ባልደረባ የሆነው ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤና እና ሦስት የባሕር ዳር ፋኖዎች ዛሬ ሰኔ 28 ቀን 2014 ዓ.ም. የአማራ መስተዳድር ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአንድ መዝገብ ቀርበዋል።

ሦስቱ ፋኖዎች ፋኖ ወልደጊዮርጊስ መኳንንት፣ ፋኖ ይገርማል በላይ እና ፋኖ ወዳጀ አንባቸው ናቸው። ውንጀላውን ያቀረበው የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን አራቱንም የኅሊና እስረኞች ባለፈው ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም. በባለሥልጣናት በር ላይ ቦምብ ለማፈንዳትና ባለሥልጣናቱን ለመግደል ሙከራ እንዳደረጉ አስመስሎ የሐሰት ውንጀላ አቅርቧል።  የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜም ጠይቋል። ፍርድ ቤቱ በበኩሉ የእስረኞችን የፍች ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ፖሊስ የጠየቀውን የምርመራ ቀን በሙሉ በመፍቀድ ለሀምሌ 12 ቀን 2014 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። ይህንን ተከትሎ ወግደረስ እና ፋኖዎቹ ከባሕር ዳር 2ኛ ፖሊስ ጣቢያ ወደ ሰባታሚት ወህኒ ቤት እንደሚወሰዱ ይጠበቃል።

ፖሊስ በየትኞቹ ባለሥልጣናት ላይ ግድያ ሊፈፀም እንደነበረ አልገለፀም።

Filed in: Amharic