አማራው የት ነው?
ጌጥዬ ያለው
‘‘አብይ አሕመድ እስከ ወዲያኛው ተሸኝቷል፣ በነፍስ ቢኖርም እንኳን ጭንቅላቱ ላይ ያለው ቁስል ከአንድ አመት በፊት ሊያገግም ስለማይችል ወንበሩ ላይ ለመቀመጥ ብቁ አይደለም’ የሚሉ መረጃዎች እየተሰሙ ነው። ከሰሞኑ አባይ ግድብን ይጎበኛል ተብሎ ሽርጉድ እየተባለ እንደሆነ ያልተረጋገጡ ጭምጭምታዎች አሉ።
መረጃዎች እውነትም ውሸትም ሊሆኑ ይችላሉ። በእኔ ማጣራት አልደረስኩበትም። ወራሪው ኦሕዴድ-ብልፅግና እላያችን ላይ እየፈረሰ መሆኑ ግን አያጠራጥርም። ወትሮም ጥቅም እንጂ ሃሳብ ተጋርቶ የማያውቀው የገዥው ፓርቲ ስብስብ እርስ በእርሱ መነታረክ ጀምሯል። ታዬ ዱንድአ ከመሮ ያላነሰ የኦሕዴድ ተቃዋሚ ሆኗል። ጸጋ አራጌ ከበለጠ ሞላ የተሻለ አብን ሆኗል። የጋራ ርዕዮተ ዓለም የሌላቸው ሰዎች ለጋርዮሽ ጥቅም በአንድ ድርጅት ውስጥ ክራባት አስረው ይውላሉ። እዚህ ቡድን ውስጥ ያሉ ሰዎች አንድም ጥቅም፤ ሌላም የአማራ ጥላቻ ያሰባሰባቸው ናቸው። አሁን ግን ይህ መቀጠል አልቻለም፤ እየፈራረሱ ነው። በርግጥ ጠግነው ለማስቀጠል የሚያደርጉት ሙከራ ቀላል ግምት የሚሰጠው አይደለም።
ይህ ወራሪ ቡድን ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ስጋት ነው። ከዚህ በላይ ቤተ መንግሥት ውስጥ ከቆየ የጀመረውን የሀገር ብተና እንቅስቃሴ አጠናክሮ ይቀጥላል። ደቡብ ኢትዮጵያን በተለያዩ ‘ክልሎች’ እየሸነሸነው ይገኛል። በቀጣይ በዚያ የሚኖር አማራ ሁሉ ተፈናቃይ፣ በጅምላ ተጨፍጫፊ፣ ተሳዳጅ ይሆናል። አማርኛ መናገር በሞት የሚያስቀጣ ወንጀል ይሆናል። በደቡብ ‘ክልል’ ከሚኖሩ 56 (ብዙ ጊዜ 55 የሚባለው አማራ ሳይቆጠር ነው) ብሔሮች መካከል በሕዝብ ብዛቱ አማራ ዘጠነኛ መሆኑን ከዓመታት በፊት የተደረገ ጥናት ያመለክታል። ይህ ሁሉ አማራ በቀጣይ የጅምላ ጭፍጨፋ ኢላማ ነው።
ኢትዮጵያን ቅኝ ለመግዛት በቅድሚያ አማራውን ማጥፋት እንዳለበት አስልቶ የመጣው ጣሊያንም የ5 ዓመታት ወረራውን እንደ ጀመረ ያደረገው ከዚህ ተመሳሳይ ነው። አዲስ አበባን እንደያዘ ኢትዮጵያን በአምስት ጠቅላይ ግዛቶች ሸነሸነ። በተለይም ‘የጋላና ሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት’ በማለት በማወቀረው ግዛት ውስጥ የነበሩ አማሮችን ‘አገራችሁ አይደለም’ እያለ አፈናቀለ። በዚህ ሂደት 8 መቶ ሺህ አማሮችን ማፈናቀሉን የሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት መሪ አቶ ተክሌ የሻው ያደረጓቸውን ጥናቶች ዋቢ አድርገው በአንድ ወቅት መናገራቸውን አስታውሳለሁ። በመላው ኢትዮጵያ በከፍተኛ ቁጥር የሚገኘው አማራ ወራሪው ኦሕዴድ-ብልፅግና በያዘው የሀገር ብተና እንቅስቃሴ ውስጥ ግንባር ቀደም ተጠቂ ነው። ይህ ራሱን ኦሮሞን ጨምሮ ለሌሎቹም የሚጎዳ እንጂ ከቶ የሚጠቅም አይደለም።
በመሆኑም ወራሪውን ስብስብ አሽቀንጥሮ በመጣል ኢትዮጵያን ከፍርሰት ማዳን ይኖርብናል።
የደርግ መንግሥት በጎሳ ያልተደራጀ (ethnic blind) ቢሆንም ‘የፊውዳል መደብ’ እያለ ያሰቃየው ስለነበር በአማራው ዘንድ የተጠላ ነበር። በመሆኑም ወያኔ ከደደቢት በረሃ ተነስቷ ወደ አዲስ አበባ በሚያደርገው ጉዞ ውስጥ አማራው ደጋፊ ነበር። የአማራ እገዛ ባይኖረው ኖሮ ለወያኔ አዲስ አበባን መርገጥ ሱሪ በአንገት እንደማውለቅ ነበር። እገዛ ብቻ ሳይሆን ከ11ዱ የሕወሓት መስራቾች መካከል አንዱ አብተው ታከለ የተባሉ አማራ ናቸው። በወቅቱ ለፍትሕ፣ ለእኩልነትና ለዴሞክራሲ መታገላቸውን እንጂ የወያኔን ሽብርተኝነት አላወቁም። ለወያኔ የተሰጠው ድጋፍ በሙሉ ፍፁም ስህተት ነበር። የደርግ ርግጫ ሕዝቡ አብዮቱን ማስወገድ ላይ ብቻ እንዲያተኩርና ሌሎች ችግሮችን ሳይመረምር እንዲታገል አነሳስቶታል።
አማራው ወያኔን በታገለበት ጊዜ ግን ደብረ ሲና ደርሶ ሲመለስ በታሪክ በአይናችን አይተነዋል። እዚህም የደረሰው የአማራ ልዩ ሃይል እና ፋኖ እንዳይዋጋ እየተደረገ በሴራ ‘አፈግፍጉ’ በመባሉ ነው። አራት ኪሎ ሊገባ ሲል ግን ማጥቃት በመፈቀዱ ብዙዎች እዚያው ቀርተው ወደ መጣበት ተመልሷል።
ኦሕዴድ ወደ ሥልጣን ሲመጣ አማራው ኦሮ-ማራ በሚል ነጠላ ዜማ ታጅቦ ድጋፍ መስጠት ብቻ ሳይሆን የራሱን መቁንን አሳልፎ ለወራሪ ሰጥቷል። ትብብሩ ብአዴን (የነፋስ አማራው) ራሱን ከምርጫ እንዲያገል እስከማድረግ የደረሰ ነው።
አብይ አሕመድ ኖረም፤ ሞተም እነኝህ ታሪካዊ ስህተቶች መደገም የለባቸው። አማራ ለዚህ ወራሪ የጅምላ ጭፍጨፋዎች አምበል የሰጠውን ሥልጣን በቁሙም ሆነ በሙቱ መልሶ ሊቀበለው ይገባል።
ከብአዴን ተስፋ ሳይጠብቁ ወደ ፊት መግፋት የአማራው ሚና ነው።
ታዲያ አማራው ለዚህ በሚያስችል ዝግጅት ላይ ነው ወይ? ድርጅት አለው ወይ? የሲቪክ ተቋማቱ ለዚህ እየሠሩ ነው ወይ? አማራው የት ነው?