>

 በኢትዮጵያ ያለው ጦርነት የፕሬስ ነጻነትን አደጋ ላይ ጥሎታል" ሲሉ ከሰሃራ በታች የሲፒጄ የአፍሪካ ተወካይ ገለጹ (ባልደራስ)

 በኢትዮጵያ ያለው ጦርነት የፕሬስ ነጻነትን አደጋ ላይ ጥሎታል” ሲሉ ከሰሃራ በታች የሲፒጄ የአፍሪካ ተወካይ ገለጹ

ባልደራስ

 

ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ጦርነት “የመገናኛ ብዙኃን ነፃነትን ይበልጥ አደጋ ላይ ጥሎታል” ሲሉ የሲፒጄ ከሰሃራ በታች የአፍሪካ ተወካይ ሙቶኪ ሙሞ አሳወቁ።

ሙቶኪ ሙሞ በዘገቡት ዘገባ ላይ እንደገለጹት በፌዴራል መንግሥቱና በትግራይ አማፂያን መካከል ጦርነት ከተጫረ ወዲህ የፕሬስ ነጻነት ይበልጥ አደጋ ላይ ወድቋል ብለዋል።

ዘገባው እንደሚያሳየው ጦርነቱ ከተቀጣጠለ ወዲህ 64 የሚዲያ ባለሙያዎች መታሠራቸውን የገለጸ ሲሆን ካለፈው ዓመት ኅዳር ወዲህ 16 ጋዜጠኞች እንደታሰሩና ይህ የነፃነት እጦት ማሽቆልቆል  ጋዜጠኞችን በማሰር  ከሰሃራ በስተደቡብ ካሉ ሃገሮች ቀዳሚ ከሆችው ከኤርትራ ጋር ኢትዮጵያንም መድቧታል።

እንደዘገባው ኢትዮጵያ ሃሣብን በመግለፅ ነፃነት ሠንጠረዥ ላይ ወደ 40 ደረጃ ዝቅ እንድትልና ከ180 ሀገሮች ወደ 140ኛ ደረጃ እንድትወርድ ሆናልች።

የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ብዙ እንግልት እንደሚደርስባቸው የጠቆመው ዘገባው በፌደራልና በክልሎች ያሉ ባለስልጣናት ጋዜጠኛውን በጻፈው  ዘገባ ማሰራቸውን ሊያቆሙ ይገባል፣  ጋዜጠኞች በነጻነት መጻፍ አለባቸው፣ ሲፒጄም ለመንግስት ያለው ምክር  ይህ ነው ብሏል።

በሌላ በኩል እኛም እንደ ታዘብነው እጅግ የተወደደው የፕሬስ ህትመት ዋጋ ፕሬሱን በኢኮኖሚ አሽመድምዶ ከገበያ እያወጣው መሆኑን እያየን ነውና የግሉ ፕሬስ ለኢትዮጵያውያን ድምጽ እንደሆነው ሁሉ ኢትዮጵያውያን ለፕሬሳቸው ህልውና መታገል አለባቸው። የግሉ ፕሬስ ሊደጎም፣ ሊደገፍ ሲገባው የተከፈተበትን የኢኮኖሚ ጦርነት በመቃወም ኢትዮጵያውያን የብሄር፣ የሀይማኖት፣ የፖለቲካ አመለካከት ሳይገድበን ፕሬሳችንን ለመጠበቅ በጋራ እንቁም።

Filed in: Amharic