>
4:38 pm - Saturday December 2, 1730

ፊልም ካነሱ አይቀር !! [እንግዳ ታደሰ]

ይህ መንግሥት ከጥንቷ የሶቭየት ኮሚንስት ፓርቲ አመራር ጋር የሚመሳሰልበት ነገሩ እጅግ የበዛ ነው ፡፡በአንድ ወቅት የታላቁን የሶቭየት ሶሻሊስት ሪቮሊሽን በአል በማስመልከት የፓርቲው ሰብሳቢ ስለ አብዮቱ ስኬት እንዲህ በማለት ይናገራል ፡፡ጓዶች ! ከአብዮታችን ማግስት ጀምሮ በህብረተሰባችን ውስጥ ያደረግነው ስኬት እጅግ ከፍተኛ ነው ፡፡ ለምሳሌ ማሪያን ብንወስዳት ከአብዮታችን በፊት ማይም ገበሬ ነበረች ፡፡ልብስ ቢኖራትም ጫማ አልነበራትም ፡፡ አሁን ግን የአካባቢያችን ከፍተኛ ወተት አምራች ገበሬ ናት ፡፡ኢቫን አንድሬቭን ውሰዱት ፡፡ በመንደራችን እጅግ ድሃ የነበረ ፣ ፈረስና ላም የሌለው እንደውም ጭራሽ መጥረቢያ እንኳን የሌለው ሰው ነበር ፡፡ አሁን ግን ባለጫማና የትራክተር ሾፌር ነው ፡፡ ትሩፊም ሴሜኖቪችን ውሰዱት ፣ አደገኛ የሰፈራችን ቦዘኔ ነበር ፡፡ ክረምቱ እንጂ የሚያግደው ፣ በየሰፈሩ እየዞረ እቃ የሚሰርቅ ሌባ ነበር ፡፡ አሁን ግን የፓርቲያችን ዋና ጸሃፊ ሆኖ እያገለገለ ነው ፡፡

የአብዮታዊ ዲሞክራሲ አራማጆች ወያኔዎችም ዛሬ ስለስኬቶቻቸው ልክ እንደሶቭየት ፓርቲ መሪዎች የማይደሰኩሩት እድገትና እመርታ ነገር የለም ፡፡ የእስረኛ አመራመር ዘዴያቸውም ከጓንታናሞ በላቀ ያለስቃይ ምርመራ አካሂደው ፣ ያለስቃይ ሽብርተኛነታቸውን የሚመሰክሩ ሽብርተኞችን ለዚያውም ተለዋዋጭ ልብስ በአንድ ቀን እያለበሱ የሚመረምሩ መርማሪዎች እንዳሉን ነው ኢቲቪ ውሸት እየጋተን ያለው ፡፡ ቴዎድሮስ አድሃኖም የዛሬ ሁለት ወይም ሶስት ወራት ገደማ ፣ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን እንቅስቃሴ አስመልክቶ ከአለም አቀፍ አክራሪ የሙስሊም ሽብርተኞች ጋር እንደሚሰሩ ስላወቅን፣ ከሲአኤና ጓንታናሞ የስለላ ድርጅቶች ጋር በጋራ እየሰራን ነው ባለበት ማግስት ፣ ያን ሁሉ ረስተው አሜሪካን በሽብርተኞች ላይ የምታደርገውን ኢሰባዊ ድርጊት በማውገዝ እኛ ግን በአመራመር ዘዴ በልጠን ሰው ሳናሰቃይ የምናስለፈልፍ አቻዮ ዲፌሮ ነን እያሉ ነው ፡፡

Ato Andargachew Tsige (photo by Seyoum Workneh)እንኳን አንድ መንግሥት ነኝ ባይ ይቅርና ጉልት ውስጥ የሚገኝ ቪድዮ ቤት እንኳ የሚገጣጠም ቪድዮ ከዚህ የበለጠ ሊሰራ ይችላል ፡፡ አገራችንን እነማን እንደሚገዟትና ፥ በነማን እንደምንገዛ ነው ይህ ቪድዮ የሚያጋልጠው ፡፡ ማንም መደዴ ሰው/ layman ሊሰራው የማይችለውን ስህትት ነው እነኚህ ሰዎች እየሰሩት ያለው ፡፡ የተደራረተ ቃላትና የተቆራረጠ ፊልም እየጣፉ ያሳዩትን ፊልም ህዝብ ያምንልናል ብለው ሲደክሙ ሲታይ ህወሃት መለስ ከሞተ ወዲህ ምን ያህል በደናቁርት ወያኔዎች እንደሚመራ ነው ፊልሙ የሚያሳየው ፡፡ እንደ ሶቭየቱ ትሩፊም ሴሜኖቪች ከቦዘኔነት ወደ ፊልም አንሺነት የገቡት ወያኔዎችን ትንሽ እንኳ ቀለም ብጤ እንዳላራሳቸው ነው ድሪቶው ፊልም የሚያሳየው ፡፡

እንኳን አንዳርጋቸው ስጋ ለባሹ የእግዚአብሄር ልጅ የሆነው አንድየ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳ ግርፋቱና ጣሩ ቢበዛበት አባት ሆይ ቢቻልህ ይህችን ቀን ከኔ አሳልፋት ብሏል ፡፡ምንድነው ያገኙት ? እጅግ ያናደዳቸው ብርሃኑ ነጋ አንዳርጋቸው ጣቱንም ቢቆራርጡት የሚናገረው የለም ያለው ቃል ነው በይበልጥ ያበሳጫቸው ፡፡ ከፊልሙም የቀደመው ይህ ቃል ነው ፡፡ ሳያውቁት በብዙ ሚልዮን ህዝብ ተከታይ ያለውን የእስልምና እምነት መሪዎችን ጭምር ነው በፊልሙ ላይ ማላገጫ ያደረጓቸው ፡፡ይህ በሚልዮን የሚገመት ሙስሊም ህብረተሰብ ከአንዳርጋቸው ጎን እና ከሙስሊም መሪዎቹ ጋር እንዲሰለፍ የበለጠ የሚያነቃቃው ነው ፡፡ እንደሚያነሳሳባቸው ነው ያልተርደዱት ያደረጉት ፡፡

Filed in: Amharic