>

ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናውን ጨምሮ  የባሕር ዳር ፋኖዎች በዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ፍርድ ቤቱ ወሰነ ጌጥዬ ያለው

 

ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናውን ጨምሮ  የባሕር ዳር ፋኖዎች በዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ፍርድ ቤቱ ወሰነ

ጌጥዬ ያለው

የባልደራስ ዘጋቢ ወግደረስ ጤናው እና የአማራ ፋኖ በባሕር ዳር አባላት ፋኖ #ይገርማል በላይ እና ፋኖ #ወልደጊዮርጊስ መኮንን  ዛሬ አርብ፤ ሃምሌ 29 ቀን 2014 ዓ.ም. በአማራ መስተዳድር ጠቅላይ ፍ/ቤት ቀርበዋል። ችሎቱ በዋስትና ከእስር እንዲፈቱ የወሰነ ሲሆን የፖሊስን አስተያየት ለመስማትና የዋስትናውን አይነት ለመበየን ለፊታችን ነሐሴ 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ፖሊስ ዛሬም ተጨማሪ 14 የምርመራ ቀናት እንዲሰጠው ጠይቋል። የእስረኞች ጠበቃ በበኩላቸው ሦስት ጊዜ የምርመራ ቀናት ተፈቅዶለት ማስረጃ አለማግኘቱን ጠቅሰው የዋስትና መብታቸው እንዲከበር ጠይቀዋል። በመሆኑም ችሎቱ የፖሊስን ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል።

በተያያዘ ዜና የአማራ ፋኖ አንድነት አመቻች  አመራርና አባላት የአማራ ጠቅላይ ፍ/ቤት በ25 ሺህ ብር ዋስትና እንዲፈቱ የወሰነ ቢሆኑም የፌዴራል መርማሪ ፖሊስ ለወህኒ ቤት በሰጠው ሕገ ወጥ ትዕዛዝ ምክንያት በእስር ላይ ቀጥለዋል።

Filed in: Amharic