>

40 ቀንና ሊሊት....!!! (ወግደረስ ጤናው )

40 ቀንና ሊሊት….!!!

ወግደረስ ጤናው

በዚህ ሥርዓት ብቻ እስካሁን ድረስ እየታሰርኩ ስፈታ ለ5ኛ ጊዜ ነው።እኔን እና መሰሎቼን በማሰር የሚመጣ ሀገር እና ህዝብን የሚጠቅም ለውጥ ቢኖር ኖሮ 5 ጊዜ ተለውጠን ነበረ ማለት ነው።ግን የለም።

ይልቁንስ የተረኛው ሦርዓት ሀገር የመናድ፣ቅርስ፣ታሪክ እና ባህልን እንዲሁም ህዝብን በኃይል እየወረሩ የማጥፋት፣የመሰልቀጥ እና ሀገርን አስይዞ እቃ፣እቃ በመጫዎት የቀጠለ የኋላዮሽ ለውጥ ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ገዥው ሥርዓት በግልፅ የስልጣን መንበሩን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ ሀገር የመበተን ስራውን ሳይሳሳት በያዘለት የጊዜ ዕቅድ መሰረት እየፈፀመ ይገኛል።ሀገር አየፈረሰ እና ህዝብ እያለቀ እኛ ግን ዛሬም ባንድ በኩል አስፈፃሚያቸው በሌላ በኩል ደግሞ እሳቱ እቤቴ እስካልገባ ድረስ “ምን አገባኝ” በሚል የጨለማው ዘመን አስተሳሰብ ቀጥለናል።

ውሸት፣ነውር፣አድርባይነት፣ማስመሰል፣ፋራቻ፣ባዶ ሆድን እያደሩ ሆድን መውደድ እና መለማመጥ ሆኗል የዘመኑ ኅቅ።እውነትን መከተል ደግሞ እብድ ያስብላል።ለነገሩ ከ99 ውሸት መካከል እንድ እውነት ከተገኘ ውሸቱ እውነት ነው እንዲሉ፣ብቻውን ለሃቀ የቆመው ብረቱ እስክንድር “እብድ”ሲባል ሰምተናል።አሁን እብዱ ማን እንደሆነ የምንለይበት ጊዜ ደርሷል።

ልዑል እግዚአብሔር ይመስገን!!

በውጭም በሀገር ውስጥም እስከመጨረሻው ድምፅ በመሆን ያልተለያችሁን ሚዲያዎች፣ተቋማትና ግለሰቦች እጅ ነስተናል።

ትግል ይቀጥላል!!

ድልለኢተዮጵያ!!

Filed in: Amharic