በመቱ እንዲህ እየሆነ ነው…!!!
ዘመድኩን በቀለ
• ተቀበል…!
“…በኦሮሚያ ክልል፣ ኢሉባቦር ዞን ዶረኒ ወረዳ ወረቦ ቀበሌ ኦነግ ሸኔ ገብቶ ዐማራ የሆነውን ሁሉ እያፈናቀለው፣ እየዘረፈው፣ እየገደለውና ከትናንት ጀምሮ ደግሞ የዐማራን ሴቶች በሙሉ አስገዳጅ የወሲብ አገልግሎት ለታጣቂው ሸኔ እንዲሰጡ በማስገደድ እየደፈሩ ነው ተብሏል።
“…ከሳምንት በፊት የኦሮሚያ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ከላይ ከኦቦ ሽመልስ አብዲሳ ቢሮ የወጣ ትእዛዝ ነው በሚል ሕጋዊ የጦር መሣሪያ የተባለን በሙሉ ከህዝቡ ላይ ገፈፉ፣ ገፈፉና ህዝቡን ባዶ እጁን አስቀሩት። ከሳምንት በኋላ የኦሮሚያ ፖሊስና የኦሮሚያ ልዩ ኃይል እየጨፈሩ ለቀው ወጡ። እነሱ እንደወጡ የእነሱን እግር ተከትለው ባለጉድሩዎቹ፣ ባለ ሹርባዎቹ ተግተልትለው ገቡ።
“…ሸኔ የተባሉት ኦነጎች ከታንክ በቀር ከባድም፣ ቀላልም መሳሪያ እስከአፍንጫቸው የታጠቁ ናቸው። አሁን ኦነጎቹ በኢልአባቦራ ዞን በዶረኒ ወረዳ በምትገኝ ወረቦ ከተማ ከገቡ ቀናትን አስቆጥረዋል። እስከ አሁን መዝረፍ፣ ማፈናቀል፣ መግደል ነበር፣ አሁን ደግሞ የዐማራ ሴቶች ለኦነግ ሠራዊት የወሲብ አገልግሎት ይስጡ ተብለው አንድ ሴት ለብዙ ኦነግ እንድትደፈር እየሆነ ነው ነው ያሉኝ የደወልኩላቸው ተፈናቃዮች።
“…በዚያም አለ በዚህ ታርጌቱ ዐማራን ማድቀቅ ነው። ዐማራን መስበር ነው። ትግሬም፣ ኦሮሞም ጠላቱ ያደረገው ዐማራን ነው። ዐማራ ግን ገራሚ ፍጥርት ነው። የማይሰበር፣ የማይደክም፣ የማይጠፋ፣ የማይዝል፣ የማይታክት፣ የማይሸነፍ፣ የማይንበጫበጭ፣ እጅ የማይሰጥ፣ አልሞት ባይ ተጋዳይ፣ ቂምበቀል የሌለው፣ ታጋሽ፣ እንደመሬት ሁሉን ቻይ፣ የማይጎብጥ፣ ደግሞም እንደጠላቱ ብዛት የማይጠፋ። አመስጋኝ፣ ይቅር ባይ። ግን ደግሞ ጀግና፣ እናቱ የወለደችው ጀግና። አቤት መታደል። ስቀናባቸው እኮ አትጠይቁኝ።
• ማርያምን እውነቴን ነው።