>

የዐቢይና ግብረ በላዎቹ አገዛዝ በምን ሞራሉ ነው  ወያኔን በጦር ወንጀለኛነት  ሊከሰው የሚችለው...!!! (አቻምየለህ ታምሩ)

የዐቢይና ግብረ በላዎቹ አገዛዝ በምን ሞራሉ ነው  ወያኔን በጦር ወንጀለኛነት  ሊከሰው የሚችለው…!!!

አቻምየለህ ታምሩ

የዐቢይ አሕመድ አገዛዝ ልሳኖች ከሰሞኑ ሲያወሩ ውለው የሚያድሩት “አሸባሪው ሕወሓት የሰው ማዕበልን በጦርነት ስልትነት በመጠቀም በአለም አቀፍ የጦር ሕግ መሰረት የጦር ወንጀለኛ መሆኑን” በመወትወት ነው። የዐቢይ አሕመድ አገዛዝ ራሱን የአለም አቀፍ የጦር ሕጎችን አክባሪ አድርጎ በመቁጠር ፋሽስት ወያኔ ግን በአለም አቀፍ የጦር ሕግ መሰረት የጦር ወንጀሎችን እየፈጸመ እንደሆነ ካመነ በአለም አቀፍ የጦር ሕግ መሰረት የጦር ወንጀለኛ ከሆነ አሸባሪ ጋር ጦርነቱ ቆሞ ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን በማወጅ ያደራድሩት ዘንድ ወደ ምዕራባውያን ለምን ምልጃ ሲልክ ይውላል? ራሱን የአለም አቀፍ የጦር ሕግ አክባሪ አድርጎ በመቁጠር ፋሽስት ወያኔን በአለም አቀፍ የጦር ሕግ መሰረት የጦር ወንጀለኛ እንደሆነ ሲከስ የሚውለው አገዛዝ ከሚከሰው አለም አቀፍ ወንጀለኛ ቡድን ጋር የፖለቲካ ድርድር ለማድረግ ፍቃደኛ መሆን በራሱ በአለም አቀፉ የጦር ሕግ መሰረት ወንጀለኛነት ነው። ባጭሩ በአለም አቀፍ የጦር ሕግ መሰረት የጦር ወንጀለኛ እንደሆነ ሲከሰው የሚውለውን አሸባሪ ቡድን ሳይጠየፍ ከአለም አቀፍ የጦር ወንጀለኛው ቡድን ጋር ለመደራደር ፍቃደኛ ሆኖ ከቡድኑ ጋር ይታረቅ ዘንድ ምልጃ ሲልክ የሚውለው የዐቢይ አሕመድ አገዛዝ በምን ሞራሉ ነው ፋሽስት ወያኔን በአለም አቀፍ የጦር ሕግ መሰረት የጦር ወንጀለኛ እንደሆነ ሊከሰው የሚችለው?

Filed in: Amharic