>

“ተሸሎኛል መጥቻለሁ...!”  (ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ)

“ተሸሎኛል መጥቻለሁ…!”

 ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አቀባበል ስነ ስርዓት እንደገለጹት በብፁዓን አባቶች ጸሎት፣ በኢትዮጵያ ካህናትና በምእመናኑ ጸሎት ጥሩ ሕክምና አግኝቼ ሕመሜ  ተሸሎኝ መጥቻለሁ ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ናት፡፡ በሃይማኖቷ፣ በምግባሯ፣ በመልካም ሥራዋ፣ በአገልግሎቷ፣ በሊቃውንቶቿ የተከበረችና በዓለም የታወቀች ቤተ ክርስቲያን ናትና አቀባበሉ ለቤተ ክርስቲያን ክብር በመደረጉ እጅግ ደስ ብሎኛል ብለዋል፡፡

ቅዱስነታቸው “በቦሌ አየር መንገድ ስለተፈጠረው ችግርም ብፁዕ አቡነ አብርሃምና ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን(ዶ/ር) በሚገባ መልስ ስለሰጡ አመስግነዋል፡፡

እንደዚያ አይነት ድርጊት የፈጸሙትንም ሰዎች እግዚአብሔር ልቦና ይስጣቸው፤ ይህም ድርጊት ከቤተ ክርስቲያን ጋር የሚያጣላ ነውና እንዳይደገም፣ የሠሩት ሥራም ቀላል አይደለምና እግዚአብሔርን ይቅርታ ሊጠይቁ ይገባል” ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በአቀባበል ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙትን ሁሉ “በቤተ ክርስቲያን ተገኝታችሁ ከፍተኛ የሆነ የአቀባበል ስነ ስርዓት ስላደረጋችሁ እግዚአብሔር ይባርካችሁ” በማለት አመስግነዋል፡፡

በመጨረሻም ሁኔታውና ዘመኑ ከባድ እንደሆነ ይታወቃልና ሁላችንም ስለ ሀገራችን ኢትዮጵያ ተግተን ልንጸልይ ይገባል፣ ትእግስቱን፣ ሰላሙን፣ አንድነቱን፣ ህብረቱን እንዲያመጣልንና ያለውን ችግር እንዲያስወግድልን ጠንክረን መጸለይ ይገባል ሲሉ አባታዊ ምክር ሰጥተዋል፡፡

https://fb.watch/fn605pGFaO/

Filed in: Amharic