>
5:13 pm - Friday April 20, 7951

ስድስት ጥያቄዎች፥ አንድ ድምዳሜ (ጌጥዬ ያለው)

ስድስት ጥያቄዎች፥ አንድ ድምዳሜ

ጌጥዬ ያለው

፩. የክርስትና ሃይማኖት መስራች ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ነው። የእስልምና መስራች ነብዩ መሀመድ ነው። ‘ኢሬቻ’ የሚሉት ፖለቲካዊ ሃይማኖት መስራቹ ማን ነው? የኦሮሞ ህዝብ በደም እየታጠበ ወንዝ ለወንዝ በመዞር የሚያመልከው አብይ አህመድን ወይስ ሽመልስ አብዲሳን?
፪. የክርስትና ሃይማኖት ቤተ አምልኮ፤ ቤተ ክርስቲያን ነው። የእስልምና ቤተ አምልኮ መስጅድ ነው። ከወንዝ ዳር ወደ መሀል አዲስ አበባ አስፋት የመጣው፤ የኢሬቻ ቤተ አምልኮ ምንድን ነው?
፫. የክርስትና አስተምህሮ በመፅሀፍ ቅዱስ፤ የእስልምናም በኡራን ተሰንዷል። የኢሬቻ አስተምህሮ በምን ተሰነደ? ዶግማ እና ቀኖናስ አለው ወይ? ወይስ በካድሬ ተለዋዋጭ ምላስ ላይ የትጠለጠለ ሃይማኖት ነው ወይ?
፬. ክርስትና ከፓትርያርክ እስከ ዲያቆናት የተዘረጋ የአመራር መዋቅር አለው። እስልምናም ሸሆች አሉት። የኢሬቻ መሪ ማን ነው?
፭. ኢሬቻ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አባል ነውን?
፮. እንደ ሎሌ ለሁለት ጌታ መገዛት ይቻል ይሆናል። እንደ አማኝ ግን ለሁለት አምላክ መስገድ ይቻላል ወይ? ወይስ ኢሬቻ የክርስትና እና የእስልምና አማኝ ኦሮሞዎችን ደጅ አይረግጥም?

ድምዳሜ

ድርጊቱ ሃይማኖት ሳይሆን ፖለቲካዊ #የጣኦት አምልኮ ነው። ከላይ ለተዘረዘሩት ጥያቄዎች ከእየ ህሊናችን የምናገኘው መልስ የሚያረጋግጥልን ይህንኑ ነው።
Filed in: Amharic