>

የገዳ ሥርዓት ባለቤት ኦሮሞ ወይስ ባንቱ??? (አቻምየለህ ታምሩ)

የገዳ ሥርዓት ባለቤት ኦሮሞ ወይስ ባንቱ???

ቻምየለህ ታምሩ

የኦሮሙማው ዋና ስራ አስፈጻሚ ዐቢይ አሕመድ ከኦነግ በቀሰመው ድንቁርና እየተመካ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የኦሮሞን ሕዝብ የገዳ ሥርዓት ባለቤት አድርጎ አቅርቦታል። ስለ እሬቻ የደረተውን በሚመከት የምንመለስበት ኾኖ በዚህ ጽሑፍ የምናተኩረው ገዳ ስለሚባለው የወረራ ሥርዓት ባለቤትነት የደገመውን ኦነጋዊ ድንቁርና ነው። እውን የገዳ ሥርዓት ባለቤት ኦሮሞ ነውን? እስቲ ዶሴው ይውጣና እውነታው ይታይ!

የገዳ ሥርዓት የባንቱ የወረራ ሥርዓት ነው። ኦሮሞ የገዳ ሥርዓትን ከባንቱ ከመውረሱ በፊት የሥርዓቱ ባለቤት የባንቱ ሕዝብ ነበር። ይህን ታሪክ የሚነግረን በኦሮሞ ጥናት ግንባር ቀደሙ ተመራማሪ፣ የኦሮሞ ብሔርተኛ ዶክተሮችና ፕሮፈሰሮች ሁሉ እሱን ሳይጠቅሱ አንድ የጻፉት ታሪክ የማይገኝላቸው ጣሊያናዊው ፕሮፌሰር ኢኔርኮ ቸሩሉ ነው። ፕሮፌሰር ኢኔርኮ ቸሩሊ ደግሞ የገዳ ሥርዓት የባንቱ ሥርዓት እንደነበር፤ ኦሮሞም የገዳ ሥርዓትን የወረሰው ከባንቱ እንደሆነ የነገረን እ.ኤ.አ. በ1543 ዓ.ም. በአርብኛ ቋንቋ የተጻፈውን ቱህፋት አል ሙጀሃዲን የተባለውን ጥንታዊ በመጽሕፍ በመጥቀስ ነው።

ለቴክኖሎጂ ምንጋና ይግባውና ፕሮፌሰር ኢኔርኮ ቸሩሊ የገዳ ሥርዓት የባንቱ ሥርዓት እንደነበርና ኦሮሞ የገዳ ሥርዓትን ከባንቱ ወርሶ ኢትዮጵያን እንደወረረ የጻፈበት ብቻ ሳይሆን ኦሮሞ የገዳ ሥርዓትን ከባንቱ ወርሶ ኢትዮጵያን ከመውረሩ በፊት የተጻፈውና የገዳ ሥርዓት የባንቱ ወታደራዊ ሥርዓት እንደሆነ የሚነግረን ጥንታዊው የቱህፋት አል ሙጀሃዲን መጽሐፍም በእጃችን ገብቷል።

የገዳ ሥርዓት የባንቱ ሥርዓት እንደነበርና ኦሮሞ የባንቱ ሥርዓት የሆነውን ገዳን ወርሶ ኢትዮጵያን እንደወረረ የሚያሳየው ፕሮፈሰር ቸርሊ የተረጎመው ቱህፋት አል ሙጀሃዲን መጽሐፍ የተጻፈው የአባ ባሕርይ ዜናሁ ለጋ*ን ከመጻፉ አስርት ዓመታት በፊት ሲሆን መጽሐፍ የአካባቢው ቀደምት ታሪክ የተመዘገበበት በጥንት ጊዜ የተጻፈ የሰነድ ማስረጃ ነው።

ፕሮፈሰር ቸሩሊ እ.ኤ.አ. በ1957 ዓ.ም. በጣሊያንኛ ቋንቋ አርሞ ያሳተመው [ታሪኩን ዣን ዶሬስ እ.ኤ.አ. በ1971 ዓ.ም. ወደ ዘፈረንሳይኛ ተርጉሞታል] ይህ ጥንታዊ መጽሐፍ ውስጥ የምናገኘው ታሪክ እንዲህ ይላል፤

“ዛሬ ሱማሊያ በሚባለው ምድር ሱማሌ ጋ*ን ተካ። መጀርቲን በሚባለው አካባቢ አንድ መዘክር ወይም የጥንት መጽሐፍ ይገኛ። ይህም ሰነድ ዑባያ በተባለ አካባቢ በሱማሊኛ Galka’yo (ጋል ካ አዮ) የተባለ ቦታ እንዳለ ይጠቅሳል። የቦታው ትርጉም “ጋ*ሎች የለቀቁት [ቦታ]” ማለት ነው… ከሰሜን ምስራቅ የመጣ የጋ* ሕዝብ ከመቶ ዓመት በላይ ከዘለቀ ትግል በኋላ ባንቱን ከማዕከላዊ ሱማሊያ አስወጣ። ብዙውን ወደ ራሱ አዋህዷል። የገዳ ሥርዓትን የወረሰው ከባንቱ ነው። ሶማሌ ጋላ*ን ወግቶ ከሱማሌ አስወጣ። ጋ* [ከባንቱ በወረሰው] የገዳ ሥርዓት በመጠቀም በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያን ከፍተኛ መሬቶች ወረረ”

[ምንጭ፡ Enerico Cerulli, Somalia I (1957); Somalia II (1959), Rome (Italian Version), Jean Doeresse: A Short Hisrory of the horn of Africa, Holland(Translated from the French Version: Histoire Sommaire de la Corne Orientale de l’Afrique (1971) P.138]

ቀደም ሲል ከቀረበው የታሪክ ምንጭ  እንደምናነበው ኦሮሞ የገዳ ሥርዓትን ከባንቱ ወረሰ እንጂ  የገዳ ሥርዓት የራሱ ሥርዓት አልነበረም። ይህን ታሪክ እኔ የፈጠርሁት ተረት ተረት አይደለም። ይህ ታሪክ እኔ ከመታሰቤ ከአምስት መቶ አመታት በፊት በ1543 ዓ.ም. የተመዘገበ የጥንት ታሪክ ነው። ታሪኩም የተጻፈው በአረብኛ ቋንቋ በዘመኑ የተዋጣለት የታሪክ መዝጋቢ ነው። የመጽሐፉም ርዕስ ቱህፋት አል ሙጀሃዲን ይባላል። የመጽሐፉን ሽፋንና ባንቱ ገዳ የሚባል ወታደራዊ የወረራ ሥርዓት እንዳለው የተጸፈበትን ገጽ ከታች አትሜዋለሁ።

የገዳ ሥርዓት የባንቱ እንጂ የኦሮሞ ሥርዓት እንዳልሆነ የነገረንን ይህን ቱህፋት አል ሙጀሃዲን

መጽሐፍ መሞገት እንጂ እኔን ይህን ታሪክ አንብቤ ያገኘሁትን እውነት ያጋራሁትን ሰው የተመዘገበውን እውነት ከላይበራሪ ወደ መድረክ በማምጣቴ የኦሮሞ ጥላቻ እንዳለብኝ አደርጎ ማቅረቡ ርባና የሌለውና የቀረበውን የታሪክ እውነት መሞገት አለመቻልን ብቻ ነው የሚያሳየው። በግልባጩ ኦሮሞ እውነት ሲነገር አይወድም ብሎ እንደመናቅም ይቆጠራል።

ባጭሩ ኦሮሞ ፈጠረው እየተባለ የሚነገረው የገዳ ሥርዓት የባንቱ እንጂ የኦሮሞ አይደለም። ኦሮሞ የገዳ የወረራ ሥርዓትን ከባንቱ ወረሰ እንጂ የሥርዓቱ ፈጣሪ ባለመሆኑ ይህ የወረራ ሥርዓት በዩኔስኮ ጭምር መመዝገብ ካለበት መመዝገብ ያለበት በባለቤቱ በባንቱ ስም እንጂ ሥርዓቱን ከባንቱ በወረሰው በኦሮሞ ስም መሆን የለበትም።

የባንቱ የወረራ ሥርዓት የኾነውን የገዳ ሥርዓትን ኦሮሞ ሊወርስ ይችላል። ሆኖም ግን የባንቱን ሥርዓት የሆነውን ገዳን ባለቤቱ ኦሮሞ እንደሆነ አድርጎ ማቅረብ ወይም ገዳን የኦሮሞ ሥርዓት አድርጎ ማስመዝገብ ስርቆት ነው። የገዳ ሥርዓት የባንቱ እንጂ የኦሮሞ ሥርዓት አለመሆኑን የሚያስረዳ የጥንት ሰነድ ከላይበራሪ ወደ መድረክ በማምጣቴ የሚቆጣና የኦሮሞ ጥላቻ እንዳለብኝ የሚቀሰቅስ ግዝብተኛ ቢኖር የሌባ ዐይነ ደረቅ ብቻ ነው።

ጎበዝ ነኝ፤ አውቃለሁ የሚል የኦሮሞ ብሔርተኛ የታሪክ ምሁር ቢኖር የገዳ ሥርዓት ኦሮሞ ከባንቱ የወረሰው አለመሆኑን የሚያስረዳ እ.ኤ.አ. በ1543 ዓ.ም. እንደተጻፈው ቱህፋት አል ሙጀሃዲን አይነት የታሪክ ማስረጃ በማቅረብ ከባንቱ በፊት ኦሮሞ በገዳ የወረራ ሥርዓት ይጠቀም እንደነበር ያሳይ። ከዚህ ውጭ እውነት ስለተነገረ ኦሮሞ የተጠላ አድርጎ የሚያቀርብ ቢኖር ሕዝብን እውነትን የማይሻ አድርጎ የሚንቅ ግብዝ ብቻ ነው።

ኦሮሞ የገዳን የወረራ ሥርዓት ከባንቱ የወረሰው ስለመሆኑ ከላይ ከቀረበው ታሪክ ተጨማሪ ማስረጃ የሚሻ ቢኖር በዚህ ወቅት በስልጣን ላይ ያለው የገዳ ድርጅና  አባገዳው ስንተኛው አባገዳ  እንደሆነ ብቻ ይመርምር።

ከአራት አመት በፊት የቦረናን አባገዳነት ድል ባለ ድግስ የተረከበው አባ አባ ገዳ ኩራ ጃርሶ ነው። አባገዳ ኩራ ጃርሶ የቦረና 71ኛው አባ ገዳ ነው።

ምንጭ ፡ [https://www.opride.com/2017/03/08/meet-kura-jarso-new-borana-abba-gadaa/?fbclid=IwAR007eHDidSQ6CUakEz3lu_XkRbFxjQWLLwdKeRh0SaPI5d2sh4kF0-lC_k]

የአንዱ አባ ገዳ ዘመን 8 ዓመት ስለሆነ አሁን ካለው አባ ገዳ በፊት 71 አባገዳዎች ነበሩ ማለት ነው። ይህ ማለት የመጀመሪያው የኦሮሞ አባገዳ ሥልጣን የያዘው ከ500 ዓመታት በፊት እንደሆነ መረዳት ይቻላል። ይህ ማለት የመጀመሪያው አባገዳ የተሾመው በ1522 ዓ.ም. ዓ.ም. አካባቢ  ነው ማለት ነው። ይህ ማለት እ.ኤ.አ. ከ1522  ዓ·ም· በፊት ኦሮሞ በገዳ የወረራ ሥርዓት አይመራም ነበር ማለት ነው። በሌላ አነጋገር ኦሮሞ በገዳ የወረራ ሥርዓት እየተመራ ኢትዮጵያን ከወረረበት  እ.ኤ.አ. ከ1522 ዓ.ም. በፊት በገዳ ሥርዓት አይነታደርም ነበር ማለት ነው። ይህ ማለት ኦሮሞ የገዳን ሥርዓት ከባንቱ ወርሶ በገዳ የወረራ ሥርዓት እየተመራ ኢትዮጵያን መውረር የጀመረው እ.ኤ.አ. በ1522 ዓ.ም. አካባቢ ነው ማለት ነው።

ታሪክ አጥንተናል ብለው ዶክተርና ፕሮፈሴር የሆኑት የኦሮሞ ብሔርተኞች ሁሉ የሚገግሩንም ኦሮሞ የገዳ ሥርዓትን የጀመረው እ.ኤ.አ. በ1522 ዓ.ም. እንደሆነ ነው። ለዚህ ማስረጃ የሚፈልግ ቢኖር ፕሮፈሰር መሐመድ ሐሰን፣ ዶክተር ነጋሶ ጉዳዳ፣ ፕሮፈሰር ሕዝቅዔል ገቢሳ፣ ልጅ ይልማ ደሬሳ፣ ወዘተ የጻፏቸውን የመመረቂያ ጽሑፎችና መጽሐፍት ያንብብ።

ኦሮሞ የገዳ ሥርዓት ባለቤት ነበር የሚል ማናቸውም ኦነጋዊ ኦሮሞ እ.ኤ.አ. ከ1522 ዓ.ም. በፊት በገዳ የወረራ ሥርዓት ይመራ ነበር እያለን ነው። ይህ ማለት ደግሞ አሁን በስልጣን ላይ ያለውን 71ኛውን የቦረና አባገዳ እየካደ ነው ማለት ነው። ኦሮሞ  እ.ኤ.አ.  ከ1522 ዓ.ም. በገዳ የወረራ ሥርዓት ይመራ ነበር የሚል ወይም  ቦረና ከ71 አባገዳ በላይ ነበረው የሚል ካለ ሙግቱን ከኔ ጋር ሳይሆን 71ኛው አባገዳ እኔ ነኝ ካለው ከኩራ ጃርሶና የ71ኛውን አባገዳ ሲመት ከደገሰው ከኦሕዴድ-ኦነግ ጋር ያድርግ። ይኼው ነው።

ከታች የታተሙት ሶስት ገጾች ከላይ በትርጉም ያቀረብሁት ኦሮሞ የገዳ ሥርዓትን ከባንቱ እንደወረሰ የሚያሳዩ የታሪክ ገጾች ናቸው። የመጀመሪያው ገጽ  ኦሮሞ ገዳን ከመውረሱ በፊት ገዳ የባንቱ የወረራ ሥርዓት እንደነበር የሚነግረን  እ.ኤ.አ. በ1543 ዓ.ም. በአርብኛ ቋንቋ የተጻፈውን ቱህፋት አል ሙጀሃዲን የተባለው ጥንታዊ መጽሐፍ ነው። ሁለተኛው ገጽ ኦሮሞ የገዳ ሥርዓትን ከባንቱ እንደወረሰው የሚያሳይ ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ ኦሮሞ ኢትዮጵያን ከመውረሩ በፊት ይኖርበት የነበረው ጋል ካ ዮ የት እንደሚገኝ የሚያሳይ የካርታ ማስረጃ ነው። ሁለቱም ከተጠቀሰው ዶሴ በተመለከተው ገጽ የሚገኙ ናቸው።

Filed in: Amharic