>

ፍርድ ቤቱና ፖሊስ ጣቢያው ባለመግባባታቸው ስንታየሁ ፍ/ቤት አልቀረበም (ጌጥዬ ያለው)

ፍርድ ቤቱና ፖሊስ ጣቢያው ባለመግባባታቸው ስንታየሁ ፍ/ቤት አልቀረበም…

ጌጥዬ ያለው

የምርመራ መዝገቡ ቢዘጋም የስርዓቱ አስጨናቂ አቶ #ስንታየሁ ቸኮል ዛሬም ከወራሪዎች እስር አልተፈታም። “የቡረዩ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት ብይን ይሰጡበታል”በተባለው በዛሬው ቀጠሮ ስንትሽ አልቀረበም። ያልቀረበው ፍርድ ቤቱና ፖሊስ ጣቢያው ባለመግባባታቸው እንደሆነ ተነግሯል። ነገ ጥቅምት 2 ቀን 2015 ዓ.ም. ለማቅረብም ተለዋጭ ቀጠሮ ተይዟል። በእረኛ ቋንቋ ሲጠቃቀሱ ለነገውም መግባባታቸውን እንጃ፤

Filed in: Amharic