>

መልስ  ለአቶ ታምራት ላይኔ (አሸናፊ)

መልስ ለአቶ ታምራት ላይኔ

አሸናፊ

አቶ ታምራት በቀደመው የአሽከርነት ዘመናቸውአማራን ህዝብ እንደህዝብ ከበደሉት ዋናው ናቸው ። አማራ ገዥ መደብ ነው የሚለውን ትርክት አምኖ ከመቀበል ባለፈ በተግባር በመተርጎም ያማራን ስቃይ ከፍ ካደረጉ ዋናው ናቸው። የአሰራረቅ ፍጥነታቸውም ጌቶቻቸውን ስላስቀና የመጨረሻውን የውርደት ካባ ተከናንበው ከርቸሌ ቤታቸው አድርገው ጌቶቻቸው የወሰኑባቸውን ቅጣት ኮሽ ሳይሉ ተቀብለው በቃዋት ሲባሉ ከከርቸሌ የወጡ ናቸው። እንደወጡ የመጀመሪያ ስራቸው ያደረጉት እየሱስ ተገለጠልኝ ብታስሩኝም ብትገፉኝም ይቅር ብያለሁ እኔ ሀገሪ በሰማይ ነው የምድሩን ለናንተ ትቻለሁ እያሉ ሲምሉ ሲገዘቱ ከረሙ። ያኔ ታዲያ ወያኔ ከነ ሙሉ ክብሯ ነበረች። እሳቸውም ኮሽ ሳይሉ መጸሀፋቸውን በብብታቸው ከተው ባህታዊ መሰሉ።

ልክ የለውጡ ንፋስ ሽው ሲል ወያኔ ብሩን አራት ኪሎን ስትሰናበት የማሉትን የተገዘቱትን ሩጫ ወደ ሀገርቤት ሆነ ።ድመት መልኩሳ     አመሏን አትረሳ እንደሚባለው በየሚዲያው ቀርበው የተደረገባቸውን መከራ መለፍለፍ ጀመሩ ሁሉን እረሱት ። የሚገርመው አንዳንድ ከንቱአማራ ነን ባዪች ሾርት ሚሞሪዋች የማይገባቸውን ካባ ደረብላቸው። እኔም ሆዴን እስኪያመኝ ሳኩ። ቢያንስ አማራ ጨቋኝ ነው
በሚል ትርክት ይቅርታ እንዲጠይቁ ሳያሳስብ። አቶ ታምራት የወጣለት ሌባ ጉበኛ እንደነበር በቅርብ ጊዜ ኮካ ድርጅት የነበራቸው ሼር መጠን በቂ ማስረጃ ነው። ዶር አብይ ስልጣን ላይ ወጡ በፍርድ ቤት ነው የተሸጠው። መቼም ወያኔ አሽከር ሆኖ ማን ንጽ አለ ብላቹ የሱን ሌብነት ወደ ቅዱስነት አትለውጡትም ብዪ ነው የማምነው።  ታምራት አራት ኪሎ አካባቢ ሲንጎራደድቢከርምም ከ ዶ.ር አብይ መላእክ ይሁን ሴጣን ሹክ ያላቸው በዘዴ ገለል ሲያደርጓቸው የድሮ ነሳችባቸው። የወያኔ አ ሽ ከርነታቸው የባርነት ዘመናቸው። ተመልሰው ወያኔ እግር ስር ወደቁ። የሚያስቀው ደግም ትናንት ጨቋኝ በዝባዥ እያሉ መከራ የከተቱት የአማራ ህዝብ ተቆርቋሪ እና አዳኝ መስለው ነው። ዛሪ ደግሞ ለሌላ መከራ ሊያዘጋጅት። ለሌላ ስቃይ ሊዳርጉት።
አቶ ስኳሪ በመጀመሪያ መጠየቅ ያለባቸው ጥያቄን  የወልቃይት እና የራያ መሪት የማነው ብለው ያምናሉ? ሁለተኛ ጦርነቱ ከመነሳቱ በፊት ትህነግ ኢትዬጵያ እንዳገር እንድትቀጥል ይፈልግ ነበር ወይ?ሶስተኛ የዶር አብይ መንግስት ችሎም ይሁን ሳይችል ትግራይን ለቆ
ሲወጣ ትህነግ አማራ ህዝብን ምን አደርገዋለሁ ብላ በመሪዋቿ ተናገረች። አራተኛ ከወሎ ተነስታ ሰሜን ሸዋ እስክትመጣ አሁን እርሶ
እቆረቆርለታለሁ የሚሉት የአማራ ህዝብ ምን አደረገችው?    ይሄንን ጠንቅቀው መመለስ ሲችሉ የርሶ አማራነት ተቆርቋሪነት ፍንትው
ብሎ ይወጣል።
ዛሪ ብድግ ብለው የአማራ ህዝብ ጠላት ኦሮሞ ነው ሲሉ አለማፈርዋ ትናንት በጋራ አብረው የገነደሱትን አፓርታይድ ስርአት ሊመልሱ
እየጣሩ መሆኑ ያልገባው ሞኝ ብቻ ነው። እረ  ለመሆኑ የርሶ ትህነግ በኩልነት አምና ታውቃለች እንዴ?27 አመት ተምክሮዋ ይህንን
ያሳያል እንዴ? እኔ ልንገሮት የመሀል አዲስአበባ መሪት ምርጥ ነው ብላ ለምታስበው ለብሔሯ  ታያለች። በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ምርጥ የሚባለውን የመንግስት መስሪያቤት ለምሳሌ ቦሌ ጉምሩክ ገቢዋችን ባንክን ሁላ ባንድ ብሔር ጠቅጥቃ የሞላች  ከአስመጭነት እስከ ላኪነት ከኮንስትራክሽን እስከ ልማት ባንክ ተበዳሪነት ለአንድ ብሔር ያደለች ። ኮንዶሚኖ እጣ እያለች ለብሔሯ እና ለአሽከሮቿ ያደለች። የአዲስ አበባ መሪትሲያልቅባ ዙሪያውን ያለ ገበሪ እያፈናቀለችለዘመዷቿ ያደለች ማን መሰሎት እርሶ ጥብቅና
የቆሙላት ትህነግ ናት። እረ እኩል እንሁንብለው የተቃወሙ በአደባባይ የገደለች ያሰረች የደፈረች ትህነግ ነች እኮ እና እርሷ የሚሉት
ከዚች ጋር አብር ነው የሚሉት ? ለአማራ ቆሚያለሁ የሚሉት ከዚች ጋር አብሮ እርሶ ስ ርአት ነው የሚሉትን አራት አመት

የቆየውን የዶ.ር አብይ ስርአትን ያፍርስ የሚሉት? በእውነት እርሶ ጤነኛ ኖት ? በዚህ ምድር እንደ ትህነግ ያለ አፓርታይድ ስርአት
ያውቁ እንደሆነ ያስረድኝ?  እሳቤ የአብይ ስርአት ሆን ብሎ አማራ እና ትግሪ እንዲጣሉ ብሎ ነው ጦርነት የጀመረው
ማለት ነው። የደ.ጾን ከአማራ ሱዳን ይሻለናል ንግግር ተስፋፊ የጌታቸው እረዳ ሂሳብ እናወራርዳለን አማራን የሚያንቋሽሹበት ዘፈን
ሁላ ለርሶ ምርቃት ነው። ወይ ሊያስብት አይፈልጉም። እኔ እሎታለሁ አማራ ይህን ጦርነት የሚዋጋው እርሶ እንደሚሉት የአብይ
መንግስት ለማቆም ሳይሆን ህልውናውን ለማስጠበቅ ነው። ቀጥሎ ሀገሩን ለማዳን ነው። ደሙ የሚፈሰው የሚሰዋው ለሀገሩ ለነጻነቱ
ነው። ለምን ብሎ ሀገሩን ከሚያፈርስ ባንዳ ጋር ያብራል?ለምን ብሎ ከነጻነት ባርነት ይመርጣል?
እኮ ለምን? እስቲ እርሶ አንድ ጥያቄ ልጠይቆት በደብብ አማራ ብቻ ነው የሚኖረው? በቄለም ወለጋ አማራ ብቻ ነው ያለው? በቤንሻንጉል አማራ ብቻ ነው የሚኖረው?ሌላ ብሔር የለም? እኔ ልንገሮት ትግሪዋችም በብዛት አሉ:: አንድ ቀን ተገደሉ
ሲባል ሰምተው ያውቃሉ? ለምን ይመስሎታል አራጅም ገዳይም ትህነግና አሽከሯ ሸኔ ስለሆኑ
ነው። ይች ደግም አላማዋ የአማራን እና የኦሮምን ጥምረት በመበጠስ ለወያኔ አሽከርነት ለማመቻቸት ነው። ይችን ሴራ የሚጎነጉኑት
በአማራ ስም ያዙኝ ልቀቁኝ የሚሉት የወያኔ አሽከሮች መሆናቸው ሳይታለም የተፈታ ነው። ክብር ለአማራ ህዝብ ከራሱ በላይ ለሀገሩ
የሚያስበው ለምጣድ ሲባል አይጧ ትለፍ ብሎ ችላባይለው ኖሮ እንደ ተላላኪዋቹ ጩሀት ቢሆን ኖሮ
አልቆለት ነበር ። ሀገሩንም አፍርሶት ነበር። ትንሽ ምክር ለዶ.ር አብይ በስሮ ተደርድረው ሌት
ተቀ እርሶን የሚደግፉ መስለው ሀገር ህዝብንየሚያሳዝኑ ብዙ የወያኔ አሽከር ካድሪዋች በልባቸው ዛሪም ወያኔን የሚናፍቁ ሞልተዋል።በዚህ አራት አመት ዋና ስራቸው ኦሮሞ ተረኛ ነው እንዲባል የሚሰሩ የወያኔ አሽከር ኦሮሞች እናኦሮሞ ተረኛ ነው እያሉ የሚጮሁ የወያኔ አሽከር አማሮች ምልተዋል ።እርሷም መጀመሪያ በስሮየተኮለኮሉትን ሳያጠሩ ለውጥ አያመጡም። እርሶ
በአፎ የሚያወሩት ኢትዬጵያ እና ከስሮ ያሉት የሚሰሩት የሰማይና የምድር ይራራቃሉ። እርሶ ስለፍቅር አብሮነት ሲያወሩ ከስሮ ያሉት ስለመለያየት ያወራሉ። መስተካከል ማስተካከል ከፓርቲ አባሎቾ ሳይመሽ ይጀምሩ።

በተረፈ እንደ ስኳሪ ክደቱ ሰነፌ የመሳሰሉትን አማራ መሳይ የትህነግ አሽከሮችን በመስማት ጊዜ ማባከን ጅልነት ነው። ነገሩ  በደህና ጊዜራቁታችሁን ባትቀሩ ኖሮ ዛሪም መከራችን በበዛ ነበር።

ውርደት ለትህነግ እና ለተላላኪዋቿ ኢትዮጵያ አሸንፋለች።

Filed in: Amharic