>

የትምህርት ጥራቱን እያስጠበቀው ነው" ማለት ትርጉሙ በእናንተ...?!? (ወግደረስ ጤናው)

የትምህርት ጥራቱን እያስጠበቀው ነው” ማለት ትርጉሙ በእናንተ…?!?

ወግደረስ ጤናው

=-አኖሌ ሐውልትን በ8ኛ ክፍል የተማሪዎች መፃሃፍ  አካቶ”ነፍጠኛ ጡት ቆረጠ፤አጤ ምኒልክ ጨፍጫፊ ናቸው።” የሚል በሬ ወለደ ሥርዓት አበጅቶ እያስተማረ

= “የግዕዝ ቁጥሮች ከግሪክ መጡ፤በላይ ዘለቀ ኦሮሞ ናቸው፤አማራ ጨቋኝ ገዥ ነበረ።”እያሉ ማስተማር ነው የትምህርት ጥራቱን ማስጠበቅ?

=”..ኦሮምያ፣ኦሮምያ የ100 ዓመት ዕድፍሽን በደማችን አጠብንልሽ፤ነፈጠኛን ሰባበርንልሽ፣ታላቋን ኦሮምያ በደማችን አቆምናት…” እያሉ የባዕድ ሀገር ባንዲራ እያውለበለቡ በየት/ቤቶች እንዲዘምሩ፣እንዲማሩ ማድረግ ነው?? ወይስ..

= የአፍሪካ ብቸኛ ፊደል የሆኑትን የአማርኛ/የግዕዝ/ፊደላት ከየትምህርት ቤቶች ጠፍተው የላቲን (ቁቤ) ፊደላት በሃገሪቱ ተንሰራፍተው የባዕድ ሃገራትን ቋንቋ፣ባህል እና ማንነትን መውረሰ ነው?

=ራሱ “የት/ጥራት አመጣ” የተባለው ግለሰብ “አማራ መጤ ነው፤ሰፋሪ ነው፤ኦርቶዶክስ ወራሪ ናት” በሚልው ጋሃድ የወጣ እሳቤው እና ንግግሩ ህዝብን እንዲፈናቀል፣እንዲገደል፣ታሪኩ እንዲወረር፣ቅርሱ እና አሻራው እንዲፈርስና እንዲጠፋ ባጠቃላይ ሀገር እንድትጠፋ ከገዥው ኢትዮጵያ እና አማራ ጠሉ የኦነግ/ኦህዴድ/ስርዓት ጋር አብሮ መስራቱ ነው?

እና ፌስቡከሩ ሆይ የሥርዓቱ ቀለብተኞች በሚከፍቱላችሁ ቦይ እየፈሰሳችሁ አባካችሁ በቁስላችን ላይ እንጨት አትስደዱ።

#በዘር የተቀፈደደ፣በሃሰት ድሪቶ የተመላ እና የተንሻፈፈ፣መስራትን ሳይሆን ማፍረስን፣መፋቀርን ሳይሆን መጣላትን፣ስልጣኔን ሳይሆን ኋላቀርነትን፣አንድነትን ሳይሆን መበታተንን፣መነሳትን ሳይሆን መውደቅን፣ሀገር እና ሰንደቅዓላማን ሳይሆን በመንደር ፍቅር መውደቅን አስተምሮ በየዮኒቨርስቲዎች ስላስፈተነ”የትምህርት ጥራት” አላችሁት?? “የኢትዮጵያ ትምህርት ተመነደገ፤አደገ!” አላችሁ?? እርግጥ የእናንተ የጥራት እና የብቃት ልኬት ይህ ነው።ስለዚህ በእናንተ እይታ እና ፍላጎት ልክ ናችሁ።ለኛ ግን የዘላለም ስህተት።

Filed in: Amharic