>

በ13 ሽህ ተማሪዎች እጣ ፈንታ ላይ በጭካኔ መፍረድ..! (ሸንቁጥ አየለ)

በ13 ሽህ ተማሪዎች እጣ ፈንታ ላይ በጭካኔ መፍረድ..!

ሸንቁጥ አየለ

ከአማራ ክልል ልክ እንደ አምናዉ ሁሉ ምንም ተማሪ ወደ ዩኒቨርስቲ እንዳይገባ ታቅዶ 13ሽህ ተማሪዎች አልፈተንም አሉ ብሎ የማገድ ዉዥንብራዊ ስትራቴጂ ቢሆንስ ብለህ ጠይቀሃል?

————————————

ከአማራ ክልል አስራ ሶስት ሽህ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መፈተን አልቻሉም::ለዚህ የተሰጠዉ ምክንያት ተማሪዎቹ እንቢ አሉ የሚል ነዉ::

ፈተናዉን በምን ምክንያት አልፈተንም እንዳሉ ወይም መፈተን እንዳልቻሉ የሚያስረዳ አንዳችም ግልጽ ያለ መረጃ የለም::

ምን ጎድሎባቸዉ ነዉ? ነዉ ወይስ ያዉ እንደተለመደዉ የአማራ ክልል ተማሪዎች ስለሆኑ አምና በጦርነት ሰበብ ከክልሉ ብዙሃኑ ተማሪዎች መፈተን እንዳልቻሉት ሁሉ ዘንድሮም የብልጽግና ስትራቴጂስቶች ተማሪዎቹ ባላነሱት ጉዳይ ሰበብ ፈጥረዉ ተማሪዎቹ እንዳይፈተኑ ያቀናበሩት ተንኮል ነዉ?

አዕምሮ ያለዉ ሰዉ መጠዬቅ ያለበት ብዙ ጥያቄዎች አሉ::በዚህ በኢትዮጵያ ዉስጥ የአማራን ህዝብ በተመለከተ የብልጽግና መንግስት ምንም አይነት ስትራቴጂ ቢተገብር በታላቅ ጥርጣሬ ሊመረመር ይገባዋል::

በዚህ ሁኔታ ዉስጥ የብልጽግና መንግስት እራሱን ጻድቅ በማድረግ የ13 ሽህ ተማሪዎችን እጣ ፋንታ ሙሉ ለሙሉ ደፍጥጦ ለማለፍ ተማሪዎቹ አልፈተንም ያሉት ጠግበዉ ነዉ ወይም አምጸዉ ነዉ ወይም ፈተና ፈርተዉ ነዉ የሚል ቅዠታዊ ፕሮፖጋንዳዉን እያጦፈዉ ነዉ::

====

ባገኘዉ አጀንዳ ሁሉ ተወሳጁ እንከፍ ጋዜጠኛ : የድንገቴ ተቃዋሚ ፖለቲከኛ እና የማህበራዊ ሚዲያ ምንትስ ደግሞ በ13 ሽህ ተማሪዎች እጣ ፋንታ ላይ ፈርዶ ከመግስት ጋር ተሰልፎ ተማሪዎቹ ላይ የብዕር ሰይፍ መዞባቸዋል::

በ13 ሽህ ተማሪዎች እጣ ፈንታ ላይ በጭካኔ በመፍረድ ከብልጽግና መንግስት ጎን ተሰልፎ የሚዘባነነዉ ምንትስ ብዛቱን ላስተዋለ ሰዉ መቼም ስለ ሶስት ተማሪዎች እጣ ፋንታ እንኳን የሚጽፉና የሚናገሩ አይመስልም?

በ13 ሽህ ተማሪዎች እጣ ፈንታ ላይ መፍረድ ቀላል ነዉ::በዚያዉም ለብልጽግና መንግስት አጋርነት መግለጫ ነዉና በ13 ሽህ ተማሪ እጣ ፈንታ ላይ እንዳሰኘ መዘባነን ብልጠት መሆኑ ነዉ::

——-

ለምሆኑ ዘንድሮም ከአማራ ክልል ልክ እንደ አምናዉ ሁሉ ምንም ተማሪ ወደ ዩኒቨርስቲ እንዳይገባ ታቅዶ 13ሽህ ተማሪዎች አልፈተንም አሉ ብሎ የማገድ ዉዥንብራዊ ስትራቴጂ ቢሆንስ ብለህ ጠይቀሃል?

በ13 ሽህ ተማሪዎች እጣ ፈንታ ላይ በጭካኔ በመፍረድ ከብልጽግና መንግስት ጎን ተሰልፎ የሚዘባነነዉ ምንት እንዴት እንዲህ አይነት ጥያቄ ይጠይቃል?

በዚህ ሰዓት በኢትዮጵያ ዉስጥ የአማራን ህዝብ በተመለከተ የብልጽግና መንግስት ምንም አይነት ስትራቴጂ ቢተገብር በታላቅ ጥርጣሬ ሊመረመር ይገባዋል::የብልጽግና መንግስት የአማራን ህዝብ ፈጽሞ  ዘሩን እስኪያጠፋ ድረስ እጅግ ብዙ የተቀናጁ ስትራቴጂዎችን እየተገበረ መሆኑን ብዙ ማስረጃዎች  አሉ::

ህዝባችሁን የምትወዱ 13 ሽህ ተማሪዎች እንዲፈተኑ ድምጽ ሁኗቸዉ

በሚሊዮን የሚቆጠር አማራ ሲፈናቀል እና ሲጨፈጨፍ በዝምታ ሀሴቱን የሚያጣጥመዉ የብልጽግና መንግስት ነዉ፥፥ አምና የአማራ ክልል ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ እንዳይገቡ በስትራቴጅ ያስቀራቸዉ ብልጽግንና ነዉ፥፥ የብልጽግና መንግስት የአማራ ተማሪዎች በዬዩኒቨርስቲዉ ሲታፈኑ እና ሲገደሉ በዝምታ ሲቃ የሚያነባ ነዉ፥፥ አሁን ደግሞ 13 ሽህ ተማሪዎች ከአማራ ክልል አልፈተን አሉ የሚል የዉዥንብር ስትራቴጂ ለቆ ተማሪዎቹን ወንጀለኛ ናቸዉ የሚሉ ካድሬዎቹን አሰማርቷል፥፥ ህዝባችሁን የምትወዱ እነዚህ በብልጽግና መንግስት የዉዥንብር ስትራቴጅ እንዳይፈተኑ የተደረጉ 13 ሽህ ተማሪዎች በድጋሜ ሁኔታዎች ተመቻችተዉ ፈተና እንዲፈተኑ ድምጽ ሁኗቸዉ፥፥ ድምጽ መሆን ካልቻላችሁ ግን  ንጹሃን ተማሪዎችን በብእራችሁ ወንጀለኛ አታድርጉ፥፥

Filed in: Amharic