>

የብልፄ አጭር ድራማ…!! የድራማው ርዕስ "ሳናጣራ አናስርም" (ዘመድኩን በቀለ)

የብልፄ አጭር ድራማ…!!

ዘመድኩን በቀለ

የድራማው ርዕስ “ሳናጣራ አናስርም”

ደራሲ የዓሰሎጠሚዶኮ ዐቢይ አሕመድ

“…ድራማው የሚጀምረው በሽብር ወንጀልና ሕገ መንግሥቱን በኃይል ለመናድ በሚል የሽብር ክስ የተከሰሱ ጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ፣ ደራሲ አሳዬ ደርቤ እና ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ የተባሉ ወጣት ኢትዮጵያውያን ፍርድ ቤት ቀርበው ፍርድ ቤቱ በዋስ እንዲፈቱ ሲወስንላቸው ነው የሚታየው።

“…ቆይቶም የእስረኞቹ ጠበቆችና ቤተሰቦች የፍርድ ቤት ውሳኔንና የመፈቻ ወረቀቱን ትእዛዝ ይዘው ወደ ሕግ አስፈጻሚውና አስሮ ወዳስቀመጣቸው ፌደራል ፖሊስ ዘንድ ይሄዳሉ። እነማ? የእስረኞቹ ቤተሰቦች። ፖሊስ ምን ቢል ጥሩ ነው። አዎ ፍርድ ቤቱ ሊፈታቸው ይችላል፣ ነገር ግን ዐቃቤ ሕግ ”ይግባኝ ልጠይቅ እችላለሁ” ስላለን አንፈታም የሚል ምላሽ ሰጥቶ ጥፉ ከዚህ ብሎ ያባርራቸዋል።

“…ይመሻል… ይነጋልም… በሌላኛው ቀን ጥቅምት 1/2015 ዓ.ምም ይሆናል። ድንገት ፌደራል ፖሊስ ጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድን፣ አሳዬ ደርቤንና ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይን ጠቅላይ ፍ/ቤት አንከልክሎ እያዳፋ ይቅርታ እያጋፋ ያቀርባቸዋል። ፍርድ ቤቱም ፎሊስን ይጠይቃል።

ዳኛ፦ እነ መዓዛን ለምን አቀረብካቸው?

ፎሊስ፦ ዝም፣ ጭጭ ጮጋ።

ዳኛ፦ እህሳ ዐቃቤ ሕግ? አንተስ?

ዐቃቤ ሕግ “ለምን እንደቀረቡ አላውቅም”

ዳኛ፦ ፍርድ ቤቱም “እኛ የምናውቀው ከእስር እንደተፈቱ ነው” ስለዚህ አያገባኝም ይላል። ከዚያም እስረኞቹን ፖሊስ ይዟቸው ወደ ዘብጥያ መልሷቸዋል። ድራማው አላለቀም። አሁን መብራት ስለጠፋ ለጊዜው አቁሜዋለሁ። መብራት ሲመጣ ፍጻሜውን አይቼ እነግራችኋለሁ። ጋሽ ሳናጣራ አናስርም ሰምተሃል…?

…ሰበር ዜና…

“…መብራት መጣች… !! እኔም ድራማውን እያየሁ ነበር። ሳናጣራ አናስርም የሚለውን ድራማ። ቅድም የጀመርኩላችሁን ድራማ ከቆመበት አንሥቶ እያየሁ ነበር። ጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ እና አሳዬ ደርቤ ተፈተዋል። ደስስ ይላል። ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ግን ሲፈታ አላየሁም። ሁለቱ እንደተፈቱ ያ መከረኛ መብራት ጠፋ። ቆይቶ መብራት ሲመጣ አይቼ እነግራችኋለሁ።

“…በሉ ዛሬ ሐሙስ አይደል የእኛ ሚዲያ (ኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ) ላይ እንገናኝ። መዓዚ እና አሳዬ እንኳን ደስ አላችሁ።”…

ይህን የመሳሰሉ ድራማዎችን ለማየት ከታች ያለውን ሊንክ ጠንቆል አድርገው በነፃ ይመልከቱ። ⇓

http://t.me/ZemedkunBekeleZ

Filed in: Amharic