>
5:13 pm - Thursday April 18, 6886

በኮሜዲያን እሸቱ መለሰ አስተባባሪነት በሰሜን አሜሪካ ካልፎርኒያ ለሚገዛው ገዳም ከ1.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተሰበሰበ።

በኮሜዲያን እሸቱ መለሰ አስተባባሪነት በሰሜን አሜሪካ ካልፎርኒያ ለሚገዛው ገዳም ሃያ አራት ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ1.5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተሰበሰበ።

በብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ በሰሜን ካልፎርኒያ ኔቫዳና አሪዞና ሊቀ ጳጳስ አሳሳቢነት ከ15 ኪ.ሜ ስኩዌር በላይ የቆዳ ስፋት ያለውን ገዳም ለመግዛት የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለመደገፍ አንድ ሚሊዮን ዶላር የመሰብሰብ ዓላማን ይዞ የተነሳው ኮሚዲያኑ አስራ አምስት ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከዕቅዱ በላይ ማሳካት ችሏል። እስከዚህ ሰዓት ድረስ ‘ጎ ፈንድ ሚ'(Gofund Me) በተባለው እርዳታ የመሰብሰቢያ መንገድ ብቻ ከአንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ ብር በላይ እንደተሰበሰበ መረጃዎች ያመለክታሉ። ገዳሙን ለመግዛት ከ8.2 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማለትም 450 ሚሊዮን ብር ገደማ እንደሚፈጅ የተገለጸ ሲሆን ብፁዕነታቸው ከቀናት በፊት ለዚህ ዓላማ መሳካት ምእመናንና ምእመናት በአቅማቸው ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

https://fb.watch/gO5FWXo3eu/

ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል

Filed in: Amharic