ልጁን ለማዳን ሲል የተሰዋ አባት…!
ወንድወሰን ተክሉ
የነገደ አማራ ተወላጆችን ከኦሮሚያ ጨፍጭፎ ለማጽዳት በጭፍጨፋ ዘመቻ ላይ ያለው በአቢይ አህመድና በሽመልስ አብዲሳ የተደራጀው የኦሮሚያው ኢ መደበኛ ኋይል ነው!!
አማራን በመጨፍጨፍ ላይ ያለው OLA ሳይሆን የአቢይና ሽመልስ ኢ መደበኛ ታጣቂ ኋይል ነው!!!
በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በሚገኘው ጀጁ ወረዳ በሽመልስ አብዲሳ እና በአቢይ አህመድ ተደራጅተው አማራን ከኦሮሚያ ጨፍጭፎ የማጽዳትን ዘመቻ እያጧጧፈ ያለው ኢ መደበኛ ታጣቂ ቡድን ቤቱን ሰብረው በመግባት የ12ኛ ክፍል ተማሪ የሆነውን ልጁን ለመግደል መሬት ለመሬት እየጎተቱ በገጀራ እያጠቁት ሳለ አባት ድንገት ደርሶ « ልጄን ልቀቁና ከፈለጋችሁ እኔን ግደሉኝ » በማለት እራሱን በመስጠቱ ገዳዮች አባትዬውን ገድለው በገጀራ እየቆረጡ ያለውን ታዳጊ ወጣት እንደቆሰለ ጥለው ሄደዋል።
የአባትዬው ታላቅ አባታዊ ኋላፊነት እስከ አንድያ ህይወቱን መስጠት ደረጃ ያደረሰ የእውነተኛ አባት ተግባርን የፈጸመ ሆኖ በመገኘቱ በጣም ልብ ይነካል።
በሽመልስ አብዲሳ እና በአቢይ አህመድ ተደራጅተው በመላ ኦሮሚያ ውስጥ ያለን የነገደ አማራ ተወላጅን ጨፍጭፈን እናጸዳለን በሚል ዘመቻ በወለጋ በምስራቅ ሸዋ በአርሲና በየትኛውም የኦሮሚያ ግዛት መጠነ ሰፊ ጭፍጨፋን እያካሄደ ያለው የኦሮሚያው ኢ መደበኛ ታጣቂ ቡድን ሆኖ ሳለ እና የዚህ ጨፍጫፊ ቡድን ዋና አዛዥ አቢይና ሽመልስ በሆኑበት ሁኔታ ደናቁርት ጋዜጠኞችና አክትቪስት ነን ባዮች ግን ጨፍጫፊውን ለLOA እና ለኦነግሸኔ የሚባል የዳቦ ስም በመስጠት ተጠያቂነትን ከአቢይ መራሹ የብልጽግና ቡድን እና ከሽመልስ መራሹ የኦሮሚያ ቡድን ለማራቅ ሲጋጋጡ በሚያሰለች መልኩ ይደመጣሉ።
ነገር ግን በወለጋም ሆነ በሸዋና አሁን ደግሞ በአርሲ የአማራ ተወላጆችን እየመረጠና እየለየ በመጨፍጨፍ ዘመቻ ላይ የተጠመደው ታጣቂ ቡድን ከአቢይ መራሹ የብልጽግና ቡድን ጋር እውነተኛ ጦርነት ከገጠመውና በድሪባ ኩምሳ ወይም ጃል መሮ የሚመራው የኦሮሞ ነጻ አውጪ ሰራዊት ወይም OROMO LIBERATION ARMY (OLA) የሚባለው ታጣቂ ቡድን ሳይሆን እራሱን የኦሮሚያ ክልል መንግስት ነኝ በሚለው የኦሮሚያ ብልጽግና ወይም ኦህዴድ ተፈጥሮና ተደራጅቶ የመንቀሳቀሻ ፍኖተ ካርታ ወጥቶለት ትእዛዝ ከአራት ኪሎ እየተላለፈለት ያለው የኦሮሚያው ኢ መደበኛ ታጣቂ ቡድን ነው ጸረ አማራ ጭፍጨፋዎችን በዘመቻ መልክ እያጧጧፈ ያለው ቡድን።
. ይህ በመሆኑም እያንዳንዱ አማራ እንደ ሕዝብም ሆነ እንደ ድርጅት አሊያም እንደ ግለሰብም በጋዜጠኝነቱ በፖለቲከኛነቱና በአንቂነቱ በመላ ኦሮሚያ በሚኖሩ አማራዊያን ላይ መጠነ ሰፊ የጭፍጨፋ ዘመቻን እያካሄደ ያለው ጫካ ያለው OLA ሳይሆን በኦሮሚያ ብልጽግና የተደራጀውና በእነ አቢይና ሽመልስ የሚመራው የኦሮሚያው ኢ መደበኛ ታጣቂ ኋይል ነው እያለ እንዲገልጽና በእያንዳንዱ አማራ ግድያ የአቢይና የሽመልስ እጆች በደም ተጨማልቀው ያሉበት ተጠያቂ መሆናቸውን በሚገልጽ ሁኔታ የዜና ትርክቱን እንዲያስተካክሉ አበክረን እናስገነዝባለን!!!