>

የጀግና እናት መከራ ፣ ስቃይና እንግልት   * የእናቴና የእማማ ፋናዬ እንግልት (ነብዩ ሲራክ)

የማለዳ ወግ…

የጀግና እናት መከራ ፣ ስቃይና እንግልት 

ነብዩ ሲራክ

 * የእናቴና የእማማ ፋናዬ እንግልት 

* የታጋይ ቤተሰብን እናመሰግናለን 

ስለሀገር ወገኑ ፍትህና ዲሞክራሲ ታጋይ ከልበ ሙሉው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የከልታማ እናት እማማ ፋናዬ የዛሬ መነኩሴ እናቴን ያለፈ መከራ ፣ ስቃይና እንጎልት ያስታውሱኛል ። ዛሬ እማማ ፋናዬ በሀገር ወዳዱ ልጃቸው የፍትህና ዲሞክራሲ ግንባታ ትግል ልጃቸው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሀሰተኛ ክስ እየተመሰረተበት ሲንገላታ የመከራና በደል ገፈት ሆነው ኑሮን በሰቀቀን እየገፋ ነው።

እናቴም  ከዘመነ ደርግ እስከ ወያኔ አገዛዝ ስለሀገርና ወገኑ በተባ ብዕሩ ታግሎ ባለፈው በጋዜጠኛ ልጇ በመጽሐፈ ሲራክ የእስርና የድብደባ እንግልት ያሳለፈችው የጨለማ ፣ የሰቀቀንና የመከራ ጊዜ ቢያልፍም አይረሳኝም😓 የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እናት እማማ ፈናዬም የዛሬው ገዠዎች የበደል ቀንበር ያጎበጣቸው ከልታማ እናት ናቸውና ክልትም ፣ ህመም ድካማቸውን አሳምሬ አውቀዋለሁ ። የእማማ ፋናዬ እና የመሰል በደል ለሀገርና ለወገን ሰላም ፣ ፍትህ እና ዲሞክራሲ ቀናኢ ልጅ ማፍራት መሆኑን አሰበውና እናም እማማ ፋናዬ እና እናቴ የእናት ድካም መከራ ፣ ስቃይና እንግልት ዘልቆ ሲያመኝ እናቴን ያስታውሰኛል። ትናንትም ሆነ ዛሬ በአብራክ ክፋይ ጀግና ልጆቻቸው ዋጋን የሚከፍሉ የታጋይ እናቶች ስቅየት ይመሳስልብኛል ።

እናት ፋናዬ ልጃቸውን ለኢትዮጵያ ሰጥተው በሽምግልና የመጦሪያ እድሜ ለታጋይ ልጃቸው ስንቅ አቀባይ መሆናቸው ቀጥሏልና ልቤን ሲሰበር እማማን ለማግኘት ደካማ ነፍሴ ፈቅዳ አታውቅም 😓 ትናንት የመላዕክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል  አውደ ምህረት ከተሜ ከልታማ እናት ከእመማ  ፋናዬን ጋር ተሜ ከወህኒ በወጣ ማግስት ተገናኘን ። የልጃቸውን ጉዳ አደራ ያሉት ቅዱስ ሚካኤል ለክብሩ ፀበል ጠምቀው ደግሰው አላሳፈራቸውም ። ልጃቸው ጋዜጠኛ ተመስገን ከወህኒ ወጥቷል። እማማ ስለታቸው ሰምሯል ፣ ደስ ብሎናል 🙂 እኔ እና ቤተሰቤ ፣ የእማማ ፋናዬ ልጀ ተሜና ቤተሰብ ፣ የተሜ አድናቂና ወዳጆች ዘመዶቹ ባንድ ጣራ ስር ፀበል ፀዲቁን ፉት እያልን ክፋ ደጉን አወጋነው ።  በእማማ ምርቃት ደምቀን በደስታ ሀሴት ሳቀን  🙂

   ጋዜጠኛ ተመስገንና ቤተሰቡ ስለ ፍትህና ዲሞክራሲ ዋጋ ከፍለዋልና እናመሰግናል 🙏

ነቢዩ ሲራክ 

ህዳር 13 ቀን 2015 ዓም

Filed in: Amharic