>

በኦነግ ሽሜና  በኦነግ ሸኔ  መሃከል የሚከሰቱ ጥቃቅን ግጭቶችን በፋኖና በኦነግ ሸኔ መሃከል እንደተደረጉ በማስመሰል የሚቀርቡት ሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳዎች ?--(ሸንቁጥ አያሌው)

በኦነግ ሽሜና  በኦነግ ሸኔ  መሃከል የሚከሰቱ ጥቃቅን ግጭቶችን በፋኖና በኦነግ ሸኔ መሃከል እንደተደረጉ በማስመሰል የሚቀርቡት ሀሰተኛ ፕሮፖጋንዳዎች ግባቸው ምንድን ነዉ?

ሸንቁጥ አያሌው


–የአማራ ክልል ፋኖ ወደ ኦሮሚያ ክልል ገብቶ ከኦነግ ሸኔ ጋር እየተዋጋ ነዉ የሚለዉ የወያኔ እና የራሱ የኦነግ ሸኔ የተንኮል ፕሮፖጋንዳ እንጂ እዉነት አይደለም::

–ሰሞኑን ርዕዮት የተባለዉ የወያኔ የፕሮፖጋንዳ ማሽን እንዲሁም ልዩ ልዩ የወያኔ ሚዲያዎች እና የራሱ የኦነግ ሸኔ ሚዲያዎች የአማራ ክልል ፋኖ ኦሮሚያ ክልል ገብቶ ከሸኔ ጋር እየተዋጉ ነዉ የሚል ፕሮፖጋንዳቸዉን እያጦፉት ነዉ::

–የዚህ ፕሮፖጋንዳ ግብ ሁለት ነዉ::

1.   የአማራ ህዝብ እና የኦሮሞ ህዝብ የርስ በርስ ጦርነት ዉስጥ እንደገቡ ፕሮፖጋንዳዉን በማሰራጨት ህዝብቦች እርስበርሳቸዉ ወደ መጨፋጨፍ እንዲገቡ በዚህም መሃል ኦነግ ሸኔ የጀመረዉን የአማራን ህዝብ የማጽዳት ስራ ለማከናወን የተንኮል እቅድ ተይዞ ነዉ

2. በሌላ መልኩ ወያኔ ይሄን ፕሮፖጋንዳ የሚነዛዉ ኦነግ ሸኔ በሚያከናዉነዉ መጠነ ሰፊ የአማራዉ ህዝብ ፍጅት ሀገሪቱ ወደ ቀዉስ ስትገባ ተመልሼ ወደ ስልጣን እመጣለሁ ብሎ በማሰብ አሁንም የአማራ ህዝብ በስፋት እንዲጨፈጨፍ ሁኔታዎችን በማስላት ነዉ የአማራ ክልል ፋኖ ኦሮሚያ ገብቶ ከሸኔ ጋር እየተዋጋ ነዉ የሚል ፕሮፖጋንዳዉን የሚያጦፈዉ::

–በብልጽግና ሰራዊት እና በኦነግ ሸኔ ሰራዊት መሃከል የሚከሰቱ ጥቃቅን ግጭቶችን (ከስትራቴጂክ ልዩነት የተነሳ ሳይሆን ከጥቃቅን ታክቲካል አካሂያዶች የተነሳ በሚፈጠሩ ጥቃቅን ልዩነቶች የተነሳ) ልክ በፋኖ እና በኦነግ ሸኔ መሃከል እንደተፈጠሩ ግጭቶ አድርጎ በማቅረብ የአማራን ህዝብ እና የኦሮሞን ህዝብ በሰፋና በጠለቀ መልክ እርስ በርስ በማጋጨት የህዝቦች እርስ በርስ ጦርነት ለመፍጠር የኦነግ ሸኔ እና የወያኔ ፕሮፖጋንዲስቶች በስፋ መልክ ሰሞኑን ብዙ የተንኮል ቅስቀሳ እያደረጉ ነዉ::ከዚህ ቀዉስም እራሳቸዉን ተጠቃሚ አድርገዉ አስልተዋል::ከቀዉሱም በዐሸናፊነት እንደሚወጡ በጠባቡ ህሊናቸዉ አስልተዋል::

—የሆኖ ሆኖ የድሉን ባለቤት የየዋሃን አምላክ መድሃኒዓለም የሚወስነዉ ይሆናል::ሁሉም አጥልቆ በቆፈረዉ ጉድጓድ ጠልቆ ይገባበታል::

“ጽዋ በእግዚአብሔር እጅ ነውና፤ ያልተቀላቀለ የወይን ጠጅ ሞላበት፤ ከዚህ ወደዚያ አገላበጠው፥ ነገር ግን አተላው አልፈሰሰም፤ የምድር ኃጢአተኞች ሁሉ ይጠጡታል።”እንዳለ መዝ 75:8

———–

ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ይጠብቃት !

Filed in: Amharic