>

የአማራ ወጣቶች ማህበር የአማራ ፋኖን ትጥቅ ለማስፈታት በሚደረገው እንቅስቃሴ ዙሪያ ያወጣው የአቋም መግለጫ.... 

የአማራ ወጣቶች ማህበር የአማራ ፋኖን ትጥቅ ለማስፈታት በሚደረገው እንቅስቃሴ ዙሪያ ያወጣው የአቋም መግለጫ…. 

በቅርቡ በገዥው መንግስት ብልፅግናና በአሸባሪው ህወሃት መካከል በተደረገው የተኩስ አቁም ስምምነት ምክንያት በማድረግ በገዢው ስርዓት  በኩል የሚደረገው የአማራ ሀይሎችን ትጥቅ የማስፈታትና ከነባር  አፅመ ርስቶቻችን ወልቃይት እና ራያ ለማስወጣት የሚደረገው እንቅስቃሴ በፅኑ እናወግዛለን ።

ሰላም ለሁሉም አስፈላጊ ነገር መሆኑን ብናምንም። የአማራ ወጣቶች ከምንታገልበት አለማ አንዱ የአማራ ህዝብ ህልውናው እንዲረጋገጥለት ፤ለህዝባችን  ነፃነት ፣ፍትህና ሰላም እንዲመጣ ነው ።ነገር ግን በሰላምና በድርድር ሰበብ የአማራን ህዝብ ጥቅምና ፍላጎት ወደ ጎን በመተው በፋኖዎቻችን ላይ የሚደርስውን መዋከብ በፅኑ እንቃወማለን ።ስለሆነም ከዚህ በታች ያለውን ባለ አራት ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተናል።

1).በጦርነቱ ቀጥተኛ ተሳታፊ የሆነው መላው የአማራ ህዝብ ሆኖ እያለ ፤በሰላም  ድርድሩ ትክክለኛ የአማራ ወኪሎች ያልተወከሉበት ፤የአማራን ህዝብ ያገለለና በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆነን ፋኖን ትጥቅ የማስፈታት እንቅስቃሴ መጀመሩ ዘላቂ ሰላም ይመጣን ብለን ስላላመንን  የአማራ ህዝብ በትክክለኛ ወኪሎቹ ተወክሎ መደራደር አለበት ።

የአማራ ህዝብ ትክክለኛ ወኪሎችም ፦

1ኛ.ዶ/ር ወንደሰን አሰፋ

2ኛ.አቶ ቴዎድሮስ ትርፌ

3ኛ.ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ

4ኛ.ብ/ጀኔራል ተፈራ ማሞ ናቸው ።

2).ከሰላሳ አመት በፊት በፓለቲካዊ ውሳኔ እና በሀይል ተወስደው የነበሩ በደምና አጥንት ታላቅ መስዕዋትነት ወደ ነባር አፅመ ርሰታቸው የተመለሱ የወልቃይትና ራያ ጉዳይ እልባት ባላገኘበት ወቅት ትጥቅ ለማስፈታት የሚደረግ የገዢው ሰርዓት  እንቅስቃሴ በፅኑ እናወግዛለን ።ይህ አሳፋሪ የገዢው   እንቅስቃሴ በአሰቸኳይ  የማይቆም ከሆነ በመላው የክልሉ ከተሞች መረር ያለ ሰላማዊ ትግል እንደምናደርግ  እናሳስባለን ።

3).የአማራ ህዝብ በጠላትነት ፈርጆ ለበርካታ አመታት የተንቀሳቀሰው ፤እየተንቀሳቀሰ ያለው ወያኔ ለአራተኛ ዙር ጦርነት ዝግጅት እያደረገ ባለበት ሁኔታ ፤ህዝባችን ከስጋት ነፃ ባልሆነበት እና ባለገገመበት በዚህ ወቅት የአማራን ፋኖ ትጥቅ ለማስፈታት የሚደረግ እንቅስቃሴ ፈፅሞ ተቀባይነት የለውም ።

4).የአማራ ህዝብ ከምድረ ገፅ ካላጠፋን እንቅልፍ አንተኛም ብለው የተነሱት የጫካው እና  የከተማው የኦነግ  ሀይሎች እንዲሁም መሰሎቹ ፤ኦሮሚያ ክልል ተብሎ በሚጠራው ንፁሃን የአማራ ወገኖቻችንን የዘር ፍጅት እያደረጉ ባለበት ወቅት ፤ከአሮሚያ  ክልል አልፎም በደራ ፣በአጣዬ ወዘተ ዘልቀው በመግባት በርካቶችን እየገደሉ ፣ከተሞችን እያቃጠሉ ፣ከፍተኛ ሀብት ንብረትም እየዘረፍ ባሉበት ሁኔታ የአማራ ፋኖን ትጥቅ ለማስፈታት የሚደረገው የገዢው  መንግሰት እንቅስቃሴ የአማራን ህዝብ ቁጭ ብለህ ታረድ እንደማለት ይቆጠራል ። ይህ ተግባር እጅግ አስነዋሪ ከሰው ሰራሽ ህግ ይሁን ከተፈጥሮ ህግ ተፃራሪ እንቅስቃሴ ነው ።በአስቸኳይ ሊታሰብበት ይገባል ።

ህዳር 21/2015 ዓ.ም

የአማራ ወጣቶች ማህበር

አማራ በቆራጥ ልጆቹ ተጋድሎ ታሪኩን ያድሳል‼️

Filed in: Amharic