>

የጋሽ ታዴዎስ ታንቱ የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ሆነ...! (ስንታየሁ ቸኮል)

የጋሽ ታዴዎስ ታንቱ የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ሆነ…!

ስንታየሁ ቸኮል

 


*… በቀረቡባቸው አራት ተደራራቢ ሀሰተኛ የሽብር ክሶች ላይ እንዲከላከሉ ለታህሳስ 21 ቀን 2015 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል።

ሐቀኛው ጋዜጠኛ እና የታሪክ ፀሀፊ ጋሸ ታዲዎስ ታንቱ ትናንት ህዳር 20 ቀን 2015 ዓ.ም. የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የፀረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት የቀረቡ ሲሆን በዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ሲደረግ የነበረውን ክርክር ችሎቱ ውድቅ አድርጎታል። በመሆኑም  ከግንቦት 10 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ አሁንም በግፍ እስር ላይ ቀጥለዋል።

ጋሽ ታዴዎስ ታንቱ በቀረቡባቸው አራት ተደራራቢ ሀሰተኛ የሽብር ክሶች ላይ እንዲከላከሉ ለታህሳስ 21 ቀን 2015 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል። ይህ ለአንድ ወር ያህል የተለጠጠ ቀጠሮ  በእጅጉ ረጅም መሆኑም እየተነቀፈ ነው።

Filed in: Amharic