>

በሎንዶን ጎዳናዎች...! ያሬድ ሀይለማርያም

በሎንዶን ጎዳናዎች…!

ያሬድ ሀይለማርያም

ሁለት ቀን የፈጀውን በሴቶች ላይ ያቸጣጠሩ ጥቃቶችን ማስቆም ስለሚቻልበት ሁኔታ ለመምክር የኢንግሊዝ መንግስት በሎንደን ያዘጋጀው ስብሰባ ላይ ተካፍይ የቀረችኝን አንድ ቀን በሎንደን ጎዳናዎች ለአምስት ሰዓታት በእግሬ እየዞርኩ የከተማውን ዋና ዋና ቦታዎች ስቃኝ ዋልኩኝ። ታዲያ በመንገዴ ላይ አንድ ቀልቤን የሳበኝ ነገር አየሁ። እኔ ከነበርኩበት Westminster Hotel ወደ ፖርላማውና ቤተመንግስቱ አካባቢ ቁልቁል ዋናውን መንገድ ይዤ ስጓዝ በአንዱ ጥግ ላይ በኢትዬጲያ ባንዲራ ያሸበረቀ እና ዙሪያው በብረት የተከበበ፣ በርካታ ፎቶዎችና መፈክሮች የተለጠፉበት ቦታ ቀልቤን ሳበው። ተጠግቼም ለማየት ሞከብሎኛል።

ካነሳኋቸውም በርካታ ፎቶዎች መካከል ሁለቱን የመንገድ ትዝብቴ ሰለሆኑ ከዚህ  አካትቻቸዋለሁ። አንዳንዱ ያነሳኋቸው ፎቶዎች ሰቅጣጭ ምስሎችን ስለያዙ እዚህ አለጠፍኳቸውም። እኔን ያስደመመም ከፎቶው ጀርባ ያለው ነገር ነው። ጉዳዩ በኦሮሚያ ክልል በአማራ ተወላጆች ላይ ያለማቋረጥ የሚጸመውን ጭፍጨፋ በመቃወም እና አለም እንዲያውቀው ለማድረግ እንደሆነ ቦታው ላይ የነበረ አንድ ነጭ አብራራልኝ። ይህን ተቃውሞ ያዘጋጀውና የሚያካሂደውም አንድ በሎንደን የሚኖር ኢትዬጵያዊ እንደሆነ እና እዚህ ቦታ ላይ ተቃውሞውን እያቀረበ ሲውል ሲያድ ዛሬ 133ኛ ቀኑም እንደሆነ ነገረኝ። እኔ ለግማሽ ቀን በለንደን ጎዳናዎች በእግሬ ለተንቀሳቀስኩት በቅዝቃዜ ቆፈን ተቆራምጄ ነበር። ይህ ሰው በምን መልኩ ቅዝቃዜውን ተቋቁሞ ለ133 ቀናት እዛ ውሎ እንዳደረ ገረመኝ። በጽናቱም ተደመምኩ። ይይን ተቃውሞ የሚያሰማው ኢትዬጵያዊው ሰው ምግብ ሊያመጣ ዞር ባለበት ሰዓት ስለነበር የደረስኩት ይህ ፈረንጅ እያንዳንዱን ፎቶ እያሳየ ሰፊ ማብራሪያ ሰጠኝ።

በተረፈ ለንደንን በጨረፍታ አይቼ፣ በተለይ በተለይ ጓደኛዬን Wendmagegne Gashu  እና ወዳጄን ያሬድን አግኝቼ በመምጣቴ ደስ ብሎኛል

Filed in: Amharic