>

በኦሮሚያ ክልል በአማራው ላይ የሚደረገው የዘር ፍጅት በኪራሙ  ዛሬም እንደቀጠለ ነው...! ፅናት ሚዲያ

በኦሮሚያ ክልል በአማራው ላይ የሚደረገው የዘር ፍጅት በኪራሙ  ዛሬም እንደቀጠለ ነው…!

ፅናት ሚዲያ -Tsinat media 

ሕዳር 22 ቀን 2015 ዓ.ም


መንግስት አለ ወይ? አለ ከተባለስ የመጀመሪያ ስራው በአገሪቱ የሚኖሩ ዜጎችን ህይወት በሰላም ወጦ የመግባታቸውን ደህንነት ማስጠበቅ ካልቻለ መንግስት መኖሩ ምን ትርጉም አለው። አማራዎች እየተመረጡ እየተጨፈጨፉ መሆኑን ከኪረሙ ወረዳ የድረሱን ጥሪ ለፅናት ሚዲያ  ያሰሙት የጥቃቱ ሰለባዎች የእሮሮ ድምፅ ነው።

ምስራቅ ወለጋ አንገር ጉትን እና ሃሮ አዲሳለም የሚኖሩ አማራዎች ነፍሳችንን አድኑልን።  በወለጋ ምድር የሰው ልጂ እንደቅጠል እየረገፈነው ሲሉ ገለፁ።

የኦሮሞ ልዩሃይል ከኦነግ ሸኔ ጋር ጥምረት በመፍጠር በተጠና እና በተቀናጀ መልኩ አማራዎችን ከወለጋ ምድር ለማጥፋት በቀን እና ለሊት ከፍተኛ ጥቃት እየፈፀመብን ነው ሲሉ የችግሩ ሰለባዎች ከቦታው አድርሰውናል።

በክልሉ መንግስት የሚታገዘው የኦሮሚያ ጥምር ሃይሉ ላለፉት 4 አመታት ሲገድለን፣ሲያፈናቅለን እና ሃብት ንብረታችንን ሲዘርፍ የቆየ ቢሆንም አሁን ደግሞ  አማራ የተባለ ማህበረሰብ በህወት ከወለጋ ምድር መውጣት የለበትም በሚል በያቅጣጫው መንገዶችን በመዝጋት እየጨፈጨፉን ይገኛሉ በማለት ገልፀዋል።

የአማራ ተወላጆችን የጫነ መኪና ይቃጠላል በሚል የክልሉ አመራሮች ትዛዝ መሰረት የትኛውም ሹፌር አማራን አያሳፍርም ብለዋል።

እግሬ አውጪኚ በየጫካው ለማምለጥ የሞከሩ አማራዎችም በየጫካው በተሰገሰገው አራጂ ሃይል እስከቤተሰባቸው ታርደው የአውሬ ቀለብ ሆነዋል ሲሉ ጨምረዉ ይገልጻሉ።

ከአንገር ጉትን በቅርብ እርቀት በምትገኘዉ ውኬ በተባለች ቦታ የሃገር መከላከያ ሰራዊት ቢኖርም ትእዛዝ አልተሰጠንም በማለት ወታደሮቹ ካፕ ውስጥ ቁጪብለዋል በማለት ነዋሪዎች ለጽናት ሚድያ ተናግረዋል።

በተፈፀመባቸው ድንገተኛ ጥቃት የተገደሉ ሰዎችን አስከሬን ሳያነሱ ህይወታቸውን ለማትረፍ ሸሽተው መውጣታቸውን የተናገሩት ነገር ግን ከታጣቂዎቹ ጥይት ቢተርፉም አሁን ላይ የሚመገቡት ምግብ ባለማገኘታቸው እና ስጋት ውስጥ መሆናቸውን እንዲሁም ከባድ ችግር ላይ መውደቃቸውን ነው የገለፁት።

በትናንትናው ዕለት በአንድ መጠለያ ጣቢያ ብቻ ከ150 በላይ የአማራ ተወላጅ ተፈናቃዮች በኦሮሚያ ልዩ ኃይልና ኦነግ ሸኔ ጥምረት የተጨፈጨፉት  አስከሬናቸው በጅምላ መቃብር በኤክካቫተር መቀበሩን ምንጮቻችን አክለዉ ለፅናት ገልፀዋል።

https://fb.watch/h8vr3wA35U/

Filed in: Amharic