>

"መንግስት ምንም እንዳልተፈጠረ ማስመሰልን ማቆም አለበት....!"  ጀዋር መሀመድ

“መንግስት ምንም እንዳልተፈጠረ ማስመሰልን ማቆም አለበት….!”

 ጀዋር መሀመድ

“በኦሮሚያ እየደረሰ ያለውን ሞትና ውድመት እየሰማን ነው።  በኪራሙ (ምስራቅ ወለጋ)፣ ኮምቦልቻ እና ጋባቴ (ሆሮ ጉዱሩ) እና ኩዩ እና ዋራ ጃርሶ (ሰላሌ/ሰሜን ሸዋ) ባለፉት 48 ሰዓታት ውስጥ በትንሹ 350 ሰዎች ተገድለው ከ400,000 በላይ ተፈናቅለዋል።  የኪራሙ ነዋሪዎች በሙሉ ወደ አጎራባች ወረዳ ለመሰደድ መገደዳቸውን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት በይፋ አስታውቋል።  ይህ አሰቃቂ ጦርነት አሁን ማብቃት አለበት።  መንግስት ምንም እንዳልተፈጠረ ማስመሰልን መተው አለበት። የህዝቦችን ስቃይ የሚያበቃበት እና ፖለቲካዊ እልባት በማግኘት የክልላችን ከፈጣን ውድቀት መታደግ አለብን። የእርዳታ ድርጅቶች ተፈናቃዮቹን ለመርዳት መነሳት አለባቸው።”

Filed in: Amharic