የኦሮሚያ ብልፅግና አመራሮችን በጦር ፍርድ ቤት ያልገተረች ሀገር ራሷን ለቀጣይ እርድ አሳልፋ የሰጠች ብቻ ናት…!”
ደመቀ ዘዉዱ
ባለፉት አመታትና ወራት በኦሮሚያ ክልል የተፈፀመዉ የዘር ማፅዳትና ምንጠራ አለም በጀርመንና ሩዋንዳ ካያቸዉ የዘር ፍጅቶቾ በየትኛዉም መልኩ የማያንሱ ናቸዉ።
ሂደቱንም የተመለከትን እንደሆነ በመጀመሪያ እነሽመልስ አብዲሳ የታራጁን ቡድን ነጥለዉ የማንቋሸሽ ስራ ሰሩ፣ ነፍጠኛን ሰበርንዉ አሉ፣እነ ለማ ዲሞግራፊ መቀየር እንደሚፈልጉ ባደባባይ ተናገሩ።
እነ ዶ/ር አብይ ዘመኑን ሙሉ በዉሸት ትግል ሰዉ ሲፈጅ የነበረዉን ታጣቂ እየመሩ የወለጋ ጫካን አስረከቡት፣ከስልጠና እስከ ዘመናዊ ስናይፐር አስታጥቀዉ ለእርድ አሰማሩት፣ከሀገር ሀገር የሚዞርበትን የመንግስት መኪኖች አደሉት፣የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የሌለዉን የተሟላ ትጥቅ አለበሱት።
የታራጁን ማንነት በነሽመልስ ባደባባይ ተነግሮት ትጥቅ የተሟላለት አራጅ ቡድን እስካሁን የበርካታ ንፁሀንን ደም ማንነታቸዉን እየለየ አፍሷል። ከአካባቢው በማለፍ የአጎራባች ክልልሎችን በመዉረር ሰዉ እንደሰንጋ ማረዱን ተያይዞታል። ከሀሉ በላይ ይህ ቡድን የትጥቅና የፋይናስ እንዲሁም የስልጠና አቅርቦት የሚደረግለት በኦሮሚያ ብልፅግና መሆኑ ሲበዛ ያስቆጫል።
እስከዛሬ የደረሱ ዉድመቶችን ክሶ ወደፊት ሰላም እንዲመጣ ከተፈለገ ግን ይህንን ወራዳ ተግባር የፈፀሙ የኦሮሚያ ብልፅግና አመራሮች በአለም አቀፍ ፍርድ እንዲጠየቁ ማድረግ የዉዴታ ግዴታ ነዉ።