>

የኦሮሞ ልዩ ኃይል እና የኦነግ ሠራዊት በአንዶዴ ከተማ ተኩስ በመክፈት ንፁሃን አማሮችን እየጨፈጨፉ ነው....! (ወግደረስ ጤናው)

የኦሮሞ ልዩ ኃይል እና የኦነግ ሠራዊት በአንዶዴ ከተማ ተኩስ በመክፈት ንፁሃን አማሮችን እየጨፈጨፉ ነው….!

ወግደረስ ጤናው


ከነቀምትና ከበደሌ ተነስቶ ጉትን ማዘጋጃ አርፎ ያደረው 31 FSR የኦሮሞ ልዩ ኃይል እና የኦነግ ሠራዊት ዛሬ ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ በአንዶዴ ከተማ ተኩስ በመክፈት ንፁሃን አማሮችን እየጨፈጨፉ ነው።

ጉትን አካባቢ ጥቂት የመከላከያ ሠራዊት አባላት ቢኖሩም ወደ አንዶዴ ግን እስካሁን የገባ የለም ሲሉ የመረጃ ምንጮች ገልፀዋል።

አንዶዴ ከተማ በአንገር ጉትን እና በጊዳ መሃል የምትገኝ ትንሽ ከተማ ነች።ከዚች ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ አብዛኛውን ከተለያዩ ቦታዎች የተፈናቀሉ አማራዎች ይገኛሉ።

ሴቶች፣ ህፃናት፣ አረጋውያን እና ሌሎችም የማህበረሰብ ክፍሎች ተፈናቅለው ከአንዶዴ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ ስለሚገኙ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በከባድ መሳሪያ የጀመረው ጭፍጨፋ በአስቸኳይ ካልቆመ የከፋ ዕልቂት በአማራዎች ላይ ይፈፀማል ሲሉ የመረጃ ምንጮች አስረድተዋል።

በተለያየ አቅጣጫ መንገድ በመዘጋቱ ተፈናቃዮቹ መሸሽ አይችሉም፤አሁን ባሉበት ሁኔታ የንፁህ መጠጥ ውሃ፣የምግብ፣የህክምና ወዘተ አገልግሎት ስለተቋረጠባቸው አስቸኳይ የደረቅ ሬሽን ድጋፍ ይፈልጋሉ ተብሏል።

Filed in: Amharic