>

የባንዲራው ነገር- ምክረ ሃሳብ፤ ሰሚ ካለ...?!? (ያሬድ ሀይለማርያም)

የባንዲራው ነገር- ምክረ ሃሳብ፤ ሰሚ ካለ…?!?

ያሬድ ሀይለማርያም


* … በአዲስ አበባ ት/ቤቶች ዙሪያ ከመዝሙርና ቋንቋ ጋር ያለውን ውጥረት ለመፍታት፤

ለመንግስት መምከር የምፈልገው ይህ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ከተማሪዎች ጋር የኦሮሚያ ክልልን ባንዲራ አውለብልቡ፣ የክልሉንም መዝሙር ዘምሩ በሚል የጀመረውን ንትርክና የተቀሰቀሰውን ውጥረት በቶሎ እንዲያቆም ነው። ነገሩ እያደር ወደ ሌላ ግጭት ሊያመራ ይችላል። ከዚህ ይልቅ እንደእኔ እሳቤ መፍትሔው፤

1ኛ/ የአገሪቱን ብሔራዊ መዝሙር በሁሉም ቋንቋዎች ማስተርጎም፣

2ኛ/ በክልሎች ውስጥ የሚገኙ ት/ቤቶች የብሔራዊ መዝሙሩን  በየራሳቸው አፍ መፍቻ ቋንቋ እንዲዘምሩ ማድረግ፤ የክልል መዝሙርም ካለ እዛው ያክሉበት።

3ኛ/ አዲስ አበባ ግን የፌደራሉ መቀመጫ እና እጅግ የተሰባጠረ ሕዝም ስለሆነ የብሔራዊውን መዝሙር በአማሪኛና በኦሮሚኛ ቋንቋ እንዲዘመር ቢደረግ። የክልል መዝሙር አዲስ አበባ ላይ እንዳይጫን ማድረግ።

ከአዲስ አበባ አንጻር ጥቅሙ፤

1ኛ/ ልጆች ከአማሪኛ ቋንቋ ቀጥሎ የአገሪቱን ሰፊ ተናጋሪ ያለውን ኦሮሚኛ ቋንቋ በቀላሉ እንዲለምዱ ያደርጋል።

2ኛ/ ሁሉም ልጆች በተለያየ ቋንቋም ቢሆን ብሔራዊ መዝሙሩን አብረው መዘመራቸው አንድ አይነት አገራዊ ስሜት ይፈጥራል።

Filed in: Amharic