>

የኦሮሙማ ሃይሎች በአዲስ አበባና በዙሪያዋ ተሸንፈዋል! (ግርማ  ካሳ)

የኦሮሙማ ሃይሎች በአዲስ አበባና በዙሪያዋ ተሸንፈዋል!

ግርማ  ካሳ


የኦሮሙማ ሃይሎች ስል፣ ኦነኝ ብቻ አይደለም፡፡ የዶር አብይ አህመድን መንግስትንም ጨምሮ ነው፡፡

ኦሮሙማ ኦሮሞነት ሳይሆን የፖለቲካ ፍልስፍና ነው፡፡፡ የዚህ ፍልስፍና  ማእዘኑ ታላቋን ኦሮሚያ መገንባት ነው፡፡ ኦሮሚያ የምትገነባው ደግሞ በኢትዮጵያ ፍርስራሽ ላይ ነው፡፡  ዶር አሰፋ ጀለታ፣ የኦሮሙማ ጳጳስ የሚባሉ ምሁር ፣ ስለ ኦሮሙማ ሲናገሩ ፣ ” Oromummaa as the Oromo

nationalist ideology defines and promotes the Oromo political, material and cultural interests in order to develop an Oromo political community and transform it into a state through destroying all powers and ideologies, mainly Ethiopianism, which have kept Oromo society under political slavery” በሚል ነው፣   የኦሮሙማ ትልቅ ግብ፣ ኢትዮጵያዊነት ማጥፋት፣ “Destroying Ethiopiamnism” መሆኑ የገለጹት፡፡

በለንደን እነ ጃዋር መሀመድ ከጥቂት አመታት በፊት አድርገውን በነበረው የኦሮሞ ብሄረተኞች ስብሰባ ላይ ፕርፕፌሰር ብትኔ የሚል ስም የወጣላቸው፣ አቶ ዋቆ፣ ” ኦሮሚያ እንድትኖር ፣ ኢትዮጵያ መበተን አለባት” ነበር ያሉት፡፡

ኦህዴድ እነ ዶር አብይ፣ ኦነጎች፣ ኦፌኮዎች ወዘተ በስልጣን ዙሪያ እርስ በርስ ቢጎነታተሉም፣  በኦሮሙማ አጀንዳ ዙሪያ ጋር አንድ አይነት ናቸው፡፡ ዶር አብይ አህመድ ፣ ከዶር አሰፋ ጀለታ፣ ዳዎድ ኢብሳ፣ ጃዋር መሐመድ የተለየ ነው ብለን አሁንም የምናስብ ካለን ጅላጅሎች ነን ማለት ነው፡፡

እነዚህ ሰዎች ኢትዮጵያን እየፈራረሷት፡፡ በ እቅድና በስትራቲጂ ነው  እየሰሩ ነው ያሉት፡፡

1ኛ የኢትዮጵያዌት መሰረት የሆኑ ማእከላትን፣ ማህበረሰባት ማዳከም አንዱ አላማቸው ነበር፡፡ ያንንም፣ በስሜን ኢትዮጵያ እያደረጉት ነው፡፡ ትግራይ፣ ጎንደር፣ ወሎ በጦርነት እንዲፈራርሱ አድርገዋል፡፡ አቢሲኒያዎች(አበሾች) የሚሏቸው ሰሜኖች አቅመ ቢስ እንዲሆኑ ተደርገዋል፡፡  ይሄ አንዱና ትልቂ ስኬታቸው ነው፡፡

2ኛ የኦሮሞ ክልል የሚሉትን ከኦሮሞ የጸዳ  ለማድረግ በተናበበና በተቀናጀ መልኩ እየሰሩ ነው፡፡ በተለይም እንቅፋት የሆኑበት አማራዎች ናቸው በሚል አማራ ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ ነው ላለፉት ላለፉት 4 አመታት ያደረጉት፡፡ በብዙ የኦሮሞ ክልል አካባቢዎች የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋቶች በኦሮሞማ ኃይሎች ተፈጽመዋል፡፡ በአስር ሺሆች ተገድለዋል፡፡ በሚሊዮኖች ተፈናቅለዋል፡፡ እንደ ወለጋ ባሉ አካባቢዎች ብቻ አይደለም፣ ጥርነትና ግጭት ባልነበረባቸው የኦሮሞ ክልል አካባቢዎች፣ አማራው በቀበ፤ኤና በወረዳ አመራሮች ፣ እንዳይሰራ፣ እንዳይንቀሳቅስ ተደርጎ ተማሮ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡ ለምሳሌ በሃረርጌ፣ በአርሲ፣ በባሌ አነስ አነስ ባሉ ከተሞችና መንደሮች ይኖሩ የነበሩ ኦሮሞ ያልሆኑ ዜጎች ከ90% የሚሆኑት ፈርተው ለቀዋል፡፡

3ኛ የኢትዮጵያ ምሰሶ የሆኑ ምልክቶች ላይ የተቀናጀ ጥቃት ጀምረዋል፡፡ አጤ ሚኒሊክ ኦሮሞው ጂማ አባ ጅፋር ፣ ወይንም ሌሎች የኦሮሞ ጎሳ መሪዎች በኦሮሞ ላይ ካደረጉት የበለጠ ጥፋት ኦሮሞ ላይ አልፈጸሙም፡፡ አጤ ሚኒሊክ እንደውም ከኦኦሮሞዎች ጋር የሰሩ፣ የኦሮሞ የጦር መሪዎች የነበሯችው ታላቅ መሪ ነበር፡፡ ሆኖም እነዚህ ሰዎች አጦእ ሚኒሊክ የኢትዮጵያ አባት እንደመህናቸው፣ የአጤ ሚኒሊክን ስም በዉሸት ትርክት ለማሳነስ ሞክረዋል፡፡ በአጤ ሚኒሊክ ላይ የተከፈተው ዘመቻ፣ ኦሮሙማ ኢትዮጵያዊነት ላይ ችግር ስላለበት ነው፡፡

ሌላው የኢትዮጵያን ፊደል ለኦሮምኛ መጠቀም ሲቻል፣ ፊደል ኢትዮጵያን የሚያሳይ ነው፣ ኦሮሞ ደግሞ ከኢትዮጵዊነት መራቅ አለበት በሚል፣ የአፍሪካ ኩራት የሆነው፣ ኦሮምኛን ሆነ ማንንም ቋንቋ በብቃት የሚገልጸውን ፊደል ትተው ፈረንጂች የፈጠሩላቸው ላቲን መጠቀም ጀመሩ፡፡

አረንጓዲኦእ ቢጫ ቀን ሰንደቅ ከኢትዮጵያ አልፎ የአፍሪካ፣ የጥቅር ህዝብ ምልክት ሆኗል፡፡ ኢትዮጵያዊነት ላይ ችግር ስላለባቸው፣ ይህን ሰንደቅ እንደ ጠላት ሰንደቅ እያዩ ኢትዮጵያዉያን በአገራቸው ሰንደቃቸውን እንዳያውለበለቡ እያደረጉ ነው፡፡

4ኛ  ኢትዮጵያዊነትን ሳይሆን ኦሮሙማ በውስጣቸው ፣ በአይምሯቸው እንዲቀረጽ የተደረጉ ሚሊዮኖችን አፍርተዋል፡፡ የቁቤ  ትውልድ የሚባለው፣ የኦሮሞ ወጣት፣ “”…ሌላ_ማሰብ_አንፈልግም_ከእናታችን_ከኦሮሚያ_በቀር ” እያለ የጥላቻ ጸረ ኢትዮጵያዊ መዝሙር እየዘመረ ነው ያደገው፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ የኦሮሞ ልጆች አይምሮና ልብ ውስጥ ኦሮሚያ እንጂ ኢትዮጵያ የለችም፡፡

እንግዲህ እውነታው ይህ ነው፡፡ ሆኖም እኛ አሁን በቅዠትና በሞኝነት ውስጥ ነው ያለነው፡፡ እነርሱ ስራቸውን እየሰሩ፣ እኛ ዝም ብለን ነው የተቀመጥነው፡፡ እነርሱ በ እቅድ ነው እነ ዶር አብይ አህመድ አስቀምጠው ። እያደነዘዙን ያሉት፡፡ እነ ዶር አብይ አህመድ እኛን በማደንዘዝና በመከፋፈል ላይ ሲያተኩሩ ሌሎች ደግሞ ቁሻሻ ስራቸውን ይሰራሉ፡፡

እነዚህ ሰዎች አላማችንን ሙሉ ለሙሉ ለማሳካት የቀረን አንድ ትልቅ ነገ ራለ ብለው ያምናሉ፡፡ እርሱም አዲስ አበባ Oromize ማድረግ፡፡ ለዚህም በእቅድ የዴሞግራኢ ለውጥ ለማድረግ ከሌሎች የኦሮሞ አካባቢዎች በመቶ ሺሆች በአዲስ አበባ አምጥተው አሰፈሩ፡፡ የፌዴራል መንግስትና የአዲስ አበባ መስተዳደር ስለተቆጣጠሩ፣ በአዲስ አበባ በተለያዩ መስሮኢያ ቤቶች ቅድሜ ለኦሮሞ እየሰጡ መስሪያ ቤቶችን በሙሉ ሞሏቸው፡፡ ተጋሩዎች ይዘውት የንመበሩት ቢዝነሶች ወርሰው፣ በሌብነትና በዝርፊያ በጥቂት አመታት ውስጥ በርካታ የኦሮሞ ባለሃብቶች ተፈጠሮ፡፡ በግድ ፣ የኦሮሚያ ባንዲራ ካልተሰቀለ፣ የኦሮሚያ መዝሙር ካልተዘመረ ብለው የአዲስ አበባ ተማሪዎችን ማስጨነቀ ጀመሩ፡፡ በአዲስ አበባ ፖሊስ ዩኒፎርም የኦሮሞ ክልል ልዩ ኃይል አባላትን በየቀበሌው አሰማሩ፡፡ ህዝቡ ሳይወድ በግዱ ፊንፊኔ የሚሏት አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት የሚለው አምኖ እንዲቀበል ለማድረግ ያለ የሌላ ኃይላቸውን አፈሰሱ፡፡

ነገር ግን ላይ ላዩን የተስካላቸው ቢመስልም፣ በተግባር ግን  በአዲስ አበባ ላይ የጀመሩት ከሽፎባቸዋል፡፡

እነርሱ በመቶ ሺሆች ኦሮሞዎችን በአዲስ አበባ ሲያሰፍሩ፣ 3፣ 4 እጥፍ ከሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ወደ አዲስ አበባ ብዙ ሰው ገብቷል፡፡ ከዚህ በኋላ ደግሞ ከትግራይ መቶኢ ሺሆች ይመጣሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው፡፡

እነርሱ የኦሮሙማ ባንዲራ ካልተሰቀለ፣ መዝሙር ካልተዘመረ ሲሉ፣ የአዲስ አበባ ተማሪ፣ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ሳይቀሩ እምቢ አሻፈረን እያሉ ነው፡፡ አዲስ አበባ አንቀበል እያለ ነው፡፡ አገራችን ኦሮሚያ የሚሉት ቅራቅቦ ሳይሆን ኢትዮጵያ፣ ሰንደቃችም የግብጽ የሚመልሰው አርማ ሳይሆን የአፍሪካ ኩራት የሆነው አረንግዴን ቢጫ ቀዩ ነው እያለ ነው፡፡

እነርሱ ፊንፊኔ የኦሮሞ ናት ሲሉ፣ “ቢመችሽም፣ ባይመችሽም፣ ሸገር ፊንፊኔ አይሆንልሽም፡ እያለ ነው፡፡

እነርሱ “መደምር፣ ብልጽግ ና  ህብረ ብሄርዊነት” እያሉ ሲበጠረጉ፣ ህዝቡ አታላይነታቸው፣ መሰሪነታቸውን፣ ሲረኝነትናቸው፣ተረኝነትና ዘረኝነታቸው አውቆ፣ ለአዲስ አበባ ህጅዝ ጥቅም የቆሙ፣ ለአዲስ አበባ የሚሰሩ፣ ሳይሆን በአዲስ አበባ ፤ላይ የተነሱ ጸረ አዲስ አበለነርሱያለውቤ መሆናቸውን እየተረዳ ነው፡፡ ህዝቡ በየቤቱ፣ በየጓዳው፣ በየእድሩ፣ በየ ማህበሩ የእንዚህ ሰዎች አካሄድና ፖለቲካ እንዳስጠላው እየተናገረ ነው፡፡

ወገኖች ኦሮሙማ በአዲስ አበባ ብቻ አይደለም፣ በአዲስ አበባ ዙሪያም ፣ በህዝብ ልብ ውስጥ የለም፡፡ ምን አልባት፣ ወለጋ፣ አርሲ ያሉ ኦሮሙማ ልባቸው ውስጥ ያለ ይኖራሉ፡፡ በአዲስ አበባ ዙሪያ ፣ በቡራዩ፣ በሰበታ፣ በዱከም፣ በሱሉልታ፣ በደብረ ዘይት፣ በናዝሬት….ያለው ማሀብረሰብ አብዛኛው ሕብረ ብሄራዊ እንደመሆኑ፣ ለኦሮሙማ ቦታ የለውም፡፡ የኦሮሙማ ሃይሎች እነዚህ አካባቢዎች በጠመንጃ ቢቆጣጠሩም በህዝቡ ልብ ውስጥ የሉም፡፡ በነዚህ አካባቢዎች ፖለቲካቸው ተሸንፏል፡፡

ስለዚህ በአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በአዲስ አበባ ዙሪያም ፣ እነዚህ የኦሮሙማ  እየተሸነፉ ነው፡፡ በነዚህ ቦታዎች ተሸነፉ ማለት ደግሞ የኦሮሙማ የጀርባ አጥንት ተሰባበረ ማለት ነው፡፡ ያለ አዲስ አበባ  የኦሮሞ ሪፑቢሊክ የሚሉትን መመስርት አይችሉም፡፡ አዲስ አበባ እስካለች ድረስ ኢትዮጵያ አትፈርስም፡፡ ምን አልክባት ወለጋ፣ ባሌ ያሉ ኢትዮጵያን አንፈለግም ብለው ትናንሽ የኦሮሚያ መንግስታት ሊመሰርቱ ይችላሉ፡፡ የተቀረው የኢትዮጵያ ክፍል ግን አዲስ አበባና ሸዋና የተቀሩ የኢትዮጵያ ግዛቶች ይዞ ይቀጥላል፡፡

Filed in: Amharic