>
5:13 pm - Wednesday April 19, 7899

ኦነጋዊ ጴንጤወች (መስፍን አረጋ )

ኦነጋዊ ጴንጤወች

መስፍን አረጋ 

 

“አውሮጳውያን መዱስ የሚሰጡን፣ ለመጸለይ ዓይናችንን ስንጨፍን መሬታችንን ለመንጠቅ ነው፡፡” 

ጆሞ ኬንያታ (Jomo Kenyata) 

ታላቁ አፍሪቃዊ አርበኛ ጆሞ ኬንያታ አብክረው ሊያስገነዝቡን እንደሞከሩት፣ ሚሲዮኖች የክርስትና ሐዋርያወች ሳይሆኑ፣ የቅኝ ገዥወች ፊታውራሪወች ነበሩ፡፡  የአውሮጳ ጅቦች አፍሪቃ የገቡት ሚሲዮን ውሾቻቸው በቀደዱላቸው በር ነበር፡፡  ያገራችን ጴንጤወችስ?

ያገራችን ጴንጤወች በኢትዮጵያዊነት ላይ የሚጫወቱት ሚና፣ ሚሲዮኖች ባፍሪቃዊነት ላይ ከተጫወቱ ሚና ጋር አንድ ዓይነት ነው፡፡ የሚሲዮን ሚና በሐይማኖት ሽፋን አፍሪቃዊነት ማጥፋት እንደሆነ ሁሉ፣ የጴንጤም ሚና በሐይማኖት ሽፋን ጦቢያዊነትን ማጥፋት ነው፡፡  ሚሲዮንነት ያፍሪቃ ፀሮች ሐይማኖታዊ መሣርያ እንደነበረ ሁሉ፣ ጴንጤነትም የጦቢያ ፀሮች ሐይማኖታዊ መሣርያ ነው፡፡ 

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስትያን መካነ እየሱስ (Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus) በሚል ስያሜ ጴንጤነትን በጦቢያ ላይ በ1950ወቹ የዘሩት ጉዲና ቱምሳን የመሳሰሉ ቀንደኛ ኦነጋውያን ነበሩ፡፡ ለጴንጤነት ምሥረታ ከፍተኛውን እገዛ ያደረጉት ደግሞ የሉተራን (Lutheran) እና ፕሬስቢቴርያን (Presbyterian) ሚሲዮኖች ነበሩ፡፡  ነጮቹ ሚሲዮኖች ጦቢያን ለማፈራረስ የሚፈልጉት፣ የቅኝ ገዥወች ዋና እንቅፋት በመሆኗ ሲሆን፣ ኦነጋውያን ጴንጤወች ጦቢያን ለማፈራረስ የሚፈልጉት ደግሞ በጦቢያ ፍርስራሽ ላይ የኦሮሙማን አጼጌ (empire) ለመገንባት ነው፡፡  ስለዚህም ነጮች ሚሲዮኖችና ኦነጋዊ ጴንጤወች ግባቸው (goal) እየቅል ቢሆንም፣ ትልማቸው (strategy) ግን አምሳል ነው፡፡   ሁለቱም ግቦቻቸውን ሊመቱ የሚችሉት ጦቢያን በማፈራረስ ብቻና ብቻ ነው፡፡  

ጦቢያን ማፈራረስ የሚቻለው ደግሞ ጦቢያ የተገመደችባቸውን ገመዶች በመጣጠስ ነው፡፡  ከነዚህ ጦቢያን ካስተሳሰሩ ገመዶች ውስጥ ደግሞ አንዷና ዋናዋ የጦቢያ ርቱምነት (ርቱዕ ዕምነት፣ orthodox) ተዋሕዶ ናት፡፡  የሐይማኖትን ገመድ መበጣጠስ የሚቻለው ደግሞ በሐይማኖት ነው፣ እሾህን በሾህ እንዲሉ፡፡  ስለዚህም ኦነጋውያን ጴንጤነትን የመሠረቱት ለክርስትና አስተምህሮ ግድ ኑሯቸው ሳይሆን፣ ጦቢያን ለማፈራረስ የሚያስችላቸው ፍቱን መሣርያ ሆኖ ስላገኙት ብቻና ብቻ ነው፡፡  በሌላ አባባል ለኦነጋዊ ጴንጤወች፣ ጴንጤነት የግብ መምቻ እንጅ ግብ አይደለም፡፡  

ለኦነጋዊ ጴንጤወች ጴንጤነት የግብ መምቻ ሳይሆን በራሱ ግብ ቢሆን ኖሮ፣ ክርስትያናዊቷን ተዋሕዶን ከማጥቃታቸው በፊት በዋቄፈታ ላይ በዘመቱ ነበር፡፡  ዋቄፈታን እያንቆለጳጰሱ ተዋሕዶን ባላንኳሰሱ ነበር፡፡  መስቀል መሳለምን እያወገዙ፣ ኦዳን በቅቤ ባላወዙ ነበር፡፡  ኢሬቻን እያደነቁ፣ በመስቀል በዓል ባልተሳለቁ ነበር፡፡  ካቶሊክን ሳይነቅፉ፣ ተዋሕዶን ባልዘለፉ ነበር፡፡  እስልምናን እየፈሩ፣ ተዋሕዶን ባልደፈሩ ነበር፡፡   

ኦነጋዊ ጴንጤወች፣ ጴንጤነትን ላጀንዳቸው ማስፈጸሚያነት የሚጠቀሙ የክርስትና ቁማርተኞች እንጅ፣ ክርስቲያኖች አይደሉም፡፡  ዓላማቸው ተሳክቶላቸው በጦቢያ ፍርስራሽ ላይ የኦሮሙማን አፄጌ ቢመሠርቱ ደግሞ፣ በመጀመርያ የሚያደርጉት የቀሩትን ሁሉንም ሐይማኖቶች (ክርስትና፣ እስልምና፣ ወዘተ.) በሕግ ከልክለው፣ ዋቄፈታን ነጥለው ብቸኛ መንግሥታዊ ሐይማኖት ማድረግ እንደሆነ ጥርጥር የለውም፡፡

 እንቆቅልሹ ደግሞ አብዛኞቹ ጴንጤወች፣ የኦነጋዊ ጴንጤወችን እኩይ ዓላማ ባለመረዳት ጴንጤነትን በሐይማኖትነቱ ብቻ ተመልክተው የጰነጠጡ አገር ወዳድ ጴንጤወች መሆናቸው ነው፡፡  በሌላ አባባል አብዛኞቹ ጴንጤወች በኦነጋዊ ጴንጤወች የተደለሉ (convince) ወይም የተታለሉ (confuse) አገር ወዳድ ጴንጤወች ናቸው፡፡  እነዚህ አገር ወዳድ ጴንጤወች በሐይማኖት ሽፋን ዓይናቸው ስለተሸፈነ፣ ኦነጋዊ ጴንጤወች እየሱስ፣ በየሱስ የሚሉት ጦቢያዊነት እስኪደመሰስ ድረስ እንደሆነ አልተገለጠላቸውም፡፡  

እጅጉን የሚያሳዝነው ደግሞ በስብከትና በዝማሬ ክሂሎታቸው ጴንጤነትን እንደ ሰደድ እሳት በማስፋፋት፣ የሚወዷትን አገራቸውን የኢትዮጵያን ሞት የሚያፋጥኑት እነዚህ አገር ወዳድ ጴንጤወች መሆናቸው ነው፡፡  ኦነጋዊ ጴንጤወች ግን፣ ኢትዮጵያዊነት የተገመደበት ሌላኛው ገመድ ለሆነው ለአማርኛ ቋንቋ ክላቸው የመረረ ጥላቻ የተነሳ ቋንቋውን በቅጡ የማይችሉ፣ ቢችሉም የማይችሉ ለመምሰል የሚጣጣሩ ከንቱወች ስለሆኑ፣ በስበከትም ሆነ በመዝሙር የማጰንጠጥ ችሎታቸው ከመ አልቦ (ኢመንት) ነው፡፡  

ስለዚህም ተዋሕዶን በመግድል ጦቢያን መግደል ዋና ዓላማው ያደርግው ኦነጋዊ ጴንጤነት የተመሠረተው በኦነጋዊ ጴንጤወች ቢሆንም፣ የቆመው ግን በኦነጋዊ ጴንጤወች በተደለሉ ወይም በተታለሉ አገር ወዳድ ጴንጤወች ነው ማለት ነው፡፡  በሌላ አባባል የኦንጋውያን ጦቢያን የማፈራረሻ ስልት ለሆነው ለጴንጤነት መስፋፋት ወሳኙን ሚና የሚጫወቱት፣ ጦቢያን ከልባቸው የሚወዱ አገር ወዳድ ጴንጤወች ናቸው፡፡  

ስለዚህም አገር ወዳድ ጴንጤወች የኦነጋዊ ጴንጤወችን እኩይ ዓላማ ተረድተው የዓላማው አስፈጻሚ ላለመሆን ከወሰኑ፣ ተዋሕዶን በመግደል ጦቢያን ለመግደል የተፈጠረው ኦነጋዊ ጴንጤነት ባጭር ጊዜ ውስጥ ያከትማል፡፡  ጴንጤነትን በሐይማኖትነቱ ብቻ የሚመለከቱት አገር ወዳድ ጴንጤወች፣ ወደ ሐይማኖታቸው ሲያንጋጥጡ፣ ሐይማኖታቸው የቆመበትን አገራቸውን እንዳያጡ አበክረው ሊያስቡበት ይገባል፡፡  በተለይም ደግሞ ኦነጋዊው ጭራቅ አሕመድ በሽልማት መልክ ከፍተኛ በጀት መድቦለት ተዋሕዶን በየለቱ የሚዘልፈውን ዮናታን አክሊሉን እና መሰሎቹን ባለጌ ጴንጤወች አንቅረው ሊተፏቸው ይገባል፡፡

ሐይማኖታዊ ነጻነትን (religious freedom) ጨምሮ ሁሉም ነጻነቶች፣ የሀገር የነጻነት ዛፍ የሚያፈራቸው ፍሬወች ናቸው፡፡  ለምሳሌ ያህል ቢሊ ግራሃምን (Billy Graham) የመሳሰሉ ምዕራባውያን ጴንጤወች፣ ሰበካቸውን በጨረሱ ቁጥር be with our soldiers in harms way እያሉ አምላካቸውን ከወታደሮቻቸው ጎን እንዲቆም የሚማጸኑት፣ የሐይማኖት ነጻነት የሚቆመው ባገር ነጻነት ላይ መሆኑን  ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነው፡፡   

ኦነጋዊ ጴንጤወች ግን አገር የግዜር ነው እያሉ ለጦቢያዊነት ዘብ መቆምን ኀጢያት ያደርጉታል፡፡  ይህን የሚያደርጉት ደግሞ በጦቢያ ፍርስራሽ ላይ የኦሮሙማን አፄጌ ለመገንባት ያቀዱትን ፀረጦቢያ እቅድ የሚያከሽፍ፣ ለጦቢያ ቀናዒ የሆነ አፍቃሪ ጦቢያ ትውልድ እንዳይፈጠር በመፍራት ነው፡፡  አገር የግዜር ነው በሚሉበት አፋቸው ደግሞ ኦሮሚያ ኬኛ ይሉበታል፡፡  እልፍ አእላፍ የተዋሕዶ አርበኞች በደም ባጥንታቸው ባቆሟት አገር ላይ፣  የተዋሕዶ መዕምኖችን ባዕድ ለማለት ይዳዳቸዋል፣ በማን ላይ ቁመሽ ማንም ታሚያለሽ እንዲሉ፡፡  

ባጭሩ ለመናገር፣ ኦነጋዊ ጴንጤነት ማለት ሰሙ ክርስትና ወርቁ ኦሮሙማ የሆነ የኦነጋዊ ቁማርተኞች ቅኔ ነው፡፡  አገር ወዳድ ጴንጤወች ግን፣ በኦነጋዊ ጴንጤወች በመደለል (convince) እና በመታለል (confuse) እንዲያዩ የተደረጉት የጴንጤነትን ኦሮሙማዊ ገጽታ ሳይሆን፣ የጴንጤነትን ክርስቲያናዊ ገጽታ ብቻ ነው፡፡  የጴንጤነት ቅኔ፣ ሰሙ እንጅ ወርቁ አልተገለጠላቸውም፡፡  ስላልተገለጠላቸው ደግሞ በጴንጤነትና በተዋሕዶ መካከል ያለው መሠረታዊ ችግር ያሰተምህሮ (doctrine) ልዩነት ይመስላቸዋል፡፡    

ኦነጋዊ ጴንጤወች ግን ለዋቄፈታ እንጅ ለክርስትና ዴንታ ስለሌቸው፣ ፀባቸው ከኢትዮጵያዊነት ጋር እንጅ ከተዋሕዶ አስተምህሮ ጋር አይደለም፡፡  ተዋሕዶነት ከጦቢያዊነት ጋር ባይቆራኝ ኖሮ፣ ኦነጋዊ ጴንጤወች የካቶሊክን አስተምህሮ የሚያከብሩትን ያህል፣ ተመሳሳዩን የተዋሕዶን አስተምህሮ ባከበሩ ነበር፡፡  ችግሩ ግን ካቶሊክ የጣልያን፣ ተዋሕዶ የጦቢያ መሆኑ ነው፡፡  

ጦቢያን የምትወዱ አገር ወዳድ ጴንጤወች ሆይ፣ እስኪ ራሳችሁን ጠይቁ፡፡  ሙስሊሙን፣ ካቶሊኩን፣ ብኻዩን… ወደ ጎን ትተው፣ ተዋሕዶውን ብቻ እግረ በግር እየተከታተሉ “እየሱስን ተቀብለሃል?” እያሉ መነዝነዝን ምን ይሉታል?  ተዋሕዶወች ብቻ እንዲጰነጥጡ የተፈለገበት ምክኒያት ምንድን ነው?  የተዋሕዶ ዐብያተ ክርስቲያኖች በቄሮ መንጋ ሲጋዩ፣ ኦነጋዊ ጴንጤወች ደስታቸውን መደበቅ እስከሚያቅታቸው ድረስ ፊታቸው እንደ ፈንድሻ የሚፈካው ለምንድን ነው?  በመንግሥታዊ ቢሮስፍና (bureaucracy) ውስጥ የተሰገሰጉ ኦነጋዊ ጴንጤወች፣ የሌሎች ሐይማኖታዊ በዓሎችን አከባበር እያመቻቹ፣ የተዋሕዶ ባዕሎች ግን እንዳይከበሩ አያሌ ቢሮስፍናዊ (bureaucratic) መሰናክሎችን የሚቸክሉት ለምንድን ነው?  የአማራ ሕጻናት ጎጆ እየተዘጋባቸው በሳት ሲንጨረጨሩ ለይምሰል እንኳን ማውገዝ ቀርቶ ተቃውሞ የማያውቀውን፣ እኔን ልትንኩ ብትሞክሩ መቶ ሺወች ባንድ ጅምበር ይታረዳሉ ብሎ በትቢት የፎከረውን፣ ኦነጋዊውን አረመኔ ጭራቅ አሕመድን ኦነጋዊ ጴንጤወች ከመሲህ የሚቆጥሩት ለምን ይመስላችሁዋል?   

አገር ወዳድ ጴንጤወች ሆይ፣ ዓይናችሁን ክፈቱ እንጅ፡፡  ኦነጋዊ ጴንጤወች በየሱስ ስም የከነቧችሁን ክናብ (ዓይነ ርግብ) ገልጣችሁ፣ ግማሹን ውነት (half truth) ሳይሆን ሙሉውን ውነት የምታዩት፣ የጴንጤነት ቅኔ ሰሙ ብቻ ሳይሆን ውርቁም የሚገለጥላችሁ፣ ኦነጋዊ ጴንጤወች ክርስቲያኖች ሳይሆኑ ጴንጤነትን ጦቢያን ለመግድያ የሚጥቀሙ የሐይማኖት ቁማርተኞች መሆናቸውን የምትረዱት መቸ ነው?   ጦቢያ ከሞተች በኋላ?  በዳግም ምጽኣት?

ድኅረ ኪታብ (Post-script)

ጴንጤወች ጴንጤ መባልን ስለሚቃወሙ፣ ራሳቸውን የሚጠሩት ፕሮቴስታንት (protestant) ብለው ነው፡፡  ጴንጤወች ፕሮቴስታንትፓስተርቸርችባይብል የመሳሰሉትን ባዕድ ቃሎች መጠቀም መብታቸው ነው፡፡  ነገር ግን አንድን ያማረኛ ተናጋሪ ራሱ እስካልፈቀደ ድረስ ያማረኛ ባልሆነ ቃል ጥራኝ ብለው ማስገደድ አይችሉም፡፡  

ተዋሕዶወች ራሳቸውን ኦርቶዶክስ የሚሉት ምርጫቸው ስለሆነ ነው (ምንም እንኳን ኦርቶዶክስ ከሚለው የባዕድ ቃል ይልቅ ርቱምነት የሚለው አገራዊ ቃል የሚሻል ቢሆንም)፡፡  ማናቸውም ሐይማኖት ያማረኛ ስም እስከሌለው ድረስ፣ ያማረኛ ተናጋሪወች ያማረኛ ስም ሊያወጡለት ሙሉ መብት አላቸው (ስሙ አንቋሻሽ ወይም አራካሽ እስካልሆነ ድረስ)፡፡  ለምሳሌ ያህል የነብዩ ሙሐመድ እምነት ተከታዮች፣ አማረኛ ተናጋሪወችን እንደ ዐረበኛው ኢስላምሙስሊም እንጅ እንደ ዐማረኛው እስላም፣ እስልምና አትበሉ ማለት አይችሉም (እስላም፣ እስልምና የሚሉት ቃሎች ያሉባቸውን ችግሮች ዘርዝረው እስካላብራሩ ድረስ)፡፡   

የፕሮቴስታንት ያማረኛ ትርጉም ዓማፂ ወይም ደግሞ መናፍቅ (አምፆ የተከፍለ፣ የራቅ፣ የተለየ) ስለሆነ፣ የእምነቱን ተከታዮች ዓማፂያን ወይም መናፍቃን ብሎ መጥራት ያማረኛ ተናገሪወች ሙሉ መብት ነው፡:  ፕሮቴስታንቶች ባማረኛ ሲጠሩ ዓማፂያን፣ መናፍቃን ወይም ጴንጤ እንዳይባሉ ከፈለጉ ደግሞ ራሳቸውን በራሳቸው ባማረኛ ይሰይሙ፡፡  ይህን እንዲያደርጉ ግን ኦነጋዊ ጴንጤወች እንደማይፈቅዱላቸው እሙን ነው፣ ሐይማኖቱ ጦቢያዊነትን ተላብሶ ጦቢያዊነትን እንዳያራምድ ይፈራሉና፡፡ 

በመጨረሻም ለተዋሕዶ ማሳሰቢያ፡:  ጠላት የሚገባው በደካማ ጎን ስለሆነ፣ የሽንፈት መንስዔው የራስ ድክመት እንጅ የጠላት ጥንካሬ አይደለም፡፡  ጴንጤነት ደግሞ መንፈሳዊ ስካር ስለሆነ፣ ጥንካሬው የብቅል ነው፡፡  ስለዚህም ምንም እንኳን የኦነጋዊ ጴንጤነት ዓላማ ተዋሕዶን መግደል ቢሆንም፣  ተዋሕዶ ልትሞት የምትችለው ግን በኦነጋዊ ጴንጤነት ጥንካሬ ሳይሆን በራሷ ድክመት ነው፡፡  በመሆኑም ተዋሕዶ ሐይማኖት እሷ ራሷ ሙታ ጦቢያን ይዛ እንዳትሞት፣ ራሷን አብጠርጥራ መርምራ፣ በሽታወቿን በደንብ አውቃ፣ ፍቱን መድሐኒቶችን አጥብቃ መሻትና መራራ ቢሆኑም እንኳን ባፋጣኝ መውሰድ አለባት፡፡  

ማተቤን ከምትብጥሱ አንገቴን ቀንጥሱ እያሉ የሚዝምሩ ተዋሕዶወች ደግሞ ዮናታን አክሊሉና መሰሎቹ ተዋሕዶን እንዲያንኳስሱ ሊፈቅዱላቸው አይገባም፡፡  በዚህ ረገድ ደግሞ ከእስላም ወንድሞቻቸው ትልቅ ትምህርት መውሰድ ይችላሉ፡፡  ሐይማኖት ማለት ምክኒያታዊነትን የማያስተናግድ ዶግማ ስለሆነ፣ ማናቸውም ሐይማኖት በሐይማኖትነቱ ትክክለኛ ሐይማኖት ነው፡፡  ስለዚህም የተዋሕዶን አስተምህሮ አለመቀበል መብት ቢሆንም፣ አስተምህሮውን መዘለፍ ግን መብት አይደለም፡፡  እነ ዮናታን አክሊሉ ተዋሕዶን ቀን ከልት የሚዘልፉት ይህ መሠርታዊ ሐቅ ጠፍቷቸው ሳይሆን፣ ተዋሕዶን ለመግደል በኦነጋዊ ጴንጤወች በተለይም ደግሞ በጭራቅ አሕመድ በተሰጣቸው ሚና መሠረት ነው፡፡     

መስፍን አረጋ      mesfin.arega@gmail.com

 

Filed in: Amharic