>

ሰለሞን ሹምዬ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ...!  (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር) 

ሰለሞን ሹምዬ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ…!

ኢትዮጵያ ኢንሳይደር


“ገበያኑ” የተሰኘው የዩቲዩብ መገናኛ ብዙኃን መስራች እና ባለቤት የሆነው ሰለሞን ሹምዬ በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ። ሰለሞን በቁጥጥር ስር የዋለው ዛሬ ቅዳሜ ታህሳስ 8፤ 2015 ፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ መሆኑን እህቱ ትግስት ሹምዬ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግራለች።

ሰለሞን ከመያዙ በፊት የፌደራል ፖሊስ አባላት እና የየካ ክፍለ ከተማ የወረዳ 1 አመራሮች ወደ መኖሪያ ቤቱ ረፋድ አምስት ሰዓት አካባቢ መሄዳቸውን ትግስት አስረድታለች። የጸጥታ ኃይሎቹ እና አብረዋቸው የነበረ ሲቪል የለበሰ ሰው ወደ መኖሪያ ቤታቸው የመጡት የፖሊስ ታርጋ በለጠፈች አንድ ፒክ አፕ እና በኮድ ሶስት “ዶልፊን” ተሽከርካሪዎች መሆኑን ጨምራ ገልጻለች። (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

Filed in: Amharic