“ነጯን ስንነጋገር፣..”
ዘመድኩን በቀለ
“…ነጭ ነጯን ስንነጋገር፣ ህወሓትን ልክ ያስገባት፣ በበቃኝም እጅ ወደላይ ያስባላት፣ አንዴ ደቡብ አፍሪካ ሌላጊዜም ከኬንያ ያሯሯጣት። ትጥቅም ያስፈታት። የዛሬን ማሩኝ እንጂ ሁለተኛ አይለምደኝም ያስባላት። ከበላጎ ጀምሮ እስከ መሆኒ ድረስ ያሯሯጣት የዐማራ ፋኖ እና የዐማራ ልዩ ኃይል ምት ነው። በተለይ ቤተ ዐማራ።
“…ሂዊ ከዐማራ የዘረፈችውን መኪና፣ ባጃጅ ሳይቀር፣ የሆስፒታል መሳሪያ፣ ኮምፒዩተር፣ ማሽኖች ዐማራ መልሶ ይቀማኛል ብላ ነው ከዐቢይ ጋር ተመሳጥራ አትርፈኝ፣ የዛሬን ማረኝ ያሰኛት። ዐማራ ለጊዜው ምሯታል። አሁን ወያኔ የፈረንጆቹንና የአፍሪካውያን ወንድሞቻችንን እግር አስሬ እየሳመች “ጅንጀሮ” ብላ የሰደበችውን ኦባሳንጆን አቅፎ እየሳመች ለታቦተ ጽዮንና ለጻድቁ አቡነ አረጋዊ ምስጋናም እያቀረበች… ነገ የሚነሣባትንም የሚልዮን ሟች የትግሬ ወጣት ቤተሰቦች ጥያቄና በሰሜን ዕዝ በሴት ወታደሮች ማኅፀን ሳንጃ ከትታ የፈጀቻቸው የኢትዮጵያውያን ወታደሮችም ፍትሕ የት እንደሚገትራት እያሰበች እስከ ጊዜው አርፋ መቀመጥ ነው።
“…አሁን ግን መጀመርታ ትጥቅ ትፍታ፣ ካምፕም ትግባ፣ ተቋማትን ለፌደራል መንግሥት ታስረክብ፣ ከመከላከያ ግምጃ ቤት የዘረፈችውንና ቆፍራ ለክረምቱ ውጊያ የደበቀችውን አሮጌ ከባድ መሳሪያም ታስረክብ። ተሃድሶዋን እየወሰደች ኢትዮጵያ የምትላትን እየሰማች አርፋ ትቀመጥ። ተሸናፊ ሲፎክር ያስጠላል። ይዘገንናልም።
“…የትግራይ ልጆች እንኳን ደስ አላችሁ። ሂዊ ያለ ኢትዮጵያ እንዴት እንደምታኖራችሁ እንኳንም አያችሁ። ነፃ አውጪያችሁ ደንቆሮ፣ መሃይም፣ በሽተኛ ልታደርጋችሁ እንደነበርም፣ መብራት፣ ውኃ፣ ኢንተርኔት፣ ስልክ፣ ባንክ፣ ነዳጅ፣ ሌላው ቀርቶ ጤፍ እንኳ ከጎጃም እንደሚጫንላችሁ የተረዳችሁ ይመስለኛል።
•ዐማራ ግን በአንድ ዓይንህ ተኛ…