>

እቃቤ ህግ በመምህርነት መስከረም አበራ ላይ የ15 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠየቀ...! (ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

እቃቤ ህግ በመምህርነት መስከረም አበራ ላይ የ15 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ጠየቀ…!

ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

ፍርድ ቤቱ 7 የክስ መመስረቻ  ቀን ሰጠ…!

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመስከረም አበራ ላይ ክስ ለመመስረት ለዐቃቤ ህግ ሰባት ቀናት ፈቀደ

ከሁለት ሳምንት ገደማ በፊት በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር በዋለችው የ“ኢትዮ ንቃት” የዩቲዩብ መገናኛ ብዙሃን መስራች እና ባለቤት መስከረም አበራ ላይ ክስ የመመስረቻ ሰባት ቀናት በፍርድ ቤት ተፈቀደ፡፡ ፍርድ ቤቱ የክስ መመስረቻ ቀናቱን የፈቀደው ዐቃቤ ህግ መስከረም በተጠረጠረችበት ጉዳይ የተሰባሰቡ “የቪዲዮ እና ሰነድ ማስረጃዎችን ለመተንተን ጊዜ እንደሚያስፈልገው በማመን” መሆኑን አስታውቋል፡፡

ዛሬ በጽህፈት ቤት በኩል በሶስት ዳኞች በተሰየመው ችሎት ዐቃቤ ህግ የፖሊስ የምርመራ መዝገብ እንደደረሰው በመግለጽ ለክስ መመስረቻ 15 ቀናት እንዲፈቀዱለት በጽሁፍ ጠይቋል፡፡ ተጠርጣሪዋን ወክለው በችሎት የተገኙት ሶስት ጠበቆች በበኩላቸው ዐቃቤ ህግ የጠየቀው የክስ መመስረቻ ቀናት ሊፈቀዱለት አይገባም ሲሉ ተቃውመዋል፡፡

ጠበቆቹ ለተቃውሟቸው ያቀረቡት መከራከሪያ ዐቃቤ ህግ ምርመራውን በበላይነት ሲመራው የነበረ መሆኑን ነው፡፡ መስከረም አበራ የተጠረጠረችበት ወንጀል “ዋስትና የማያስከለክል” መሆኑንም ጠበቆቹ በተጨማሪ መከራከሪያነት አንስተዋል፡፡ የፌደራል ፖሊስ መስከረም አበራን ለመጀመሪያ ጊዜ ችሎት ፊት ባቀረበበት ወቅት “በሽብር የወንጀል ድርጊት” እንደጠረጠራት ለችሎቱ አስታውቆ ነበር፡፡ (

* * ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ይህን ሊንክ ይጫኑ፦ https://ethiopiainsider.com/2022/9218/

Filed in: Amharic