>
9:27 pm - Thursday May 19, 2022

የኃይለማርያም አድርባይነት የወለደው ክህደት! [ኤርሚያስ ለገሰ ]

የ ” ካፊቾ ልጆች” ዘመን እያለቀ ይሆን?

( አርከበ እቁባይ እየተሳካለት ይሆን? )

የ ” መለስ ትሩፋት” መጽሀፍ በገፅ 64 ላይ የካፊቾ ልጆች ጊዜያቸው ሲደርስ በሌላ ማስታወሻ ብዙ ነገር እንደሚያጫውቱን ቃል ገብታለች ። ቃሏን ትጠብቃለች ተብሎ ይጠበቃል።
ርግጥም የካፊቾ ልጆች ብዙ ያልተነገረ ታሪክ አላቸው። ከህውሀት ባልተናነሰ “የጠባብነት በሽታ” የተጠናወታቸው በመሆኑ ለአቶ መለስና ህውሀት የቅርብ ሰዎች ነበሩ። በዚህም ምክንያት የፍትህ ስርአቱን አቶ መለስ በሚፈልገው መልኩ አሽከርክረውለታል። እሱም ይህን በመረዳት የጠቅላይ ሚኒስትር ጵ/ ቤት፣ የፍትሕ ሚኒስትር ፣ ፀረ ሙስና ኮሚሽን፣ የአዲሳአባ ፍትህ ቢሮ በእነሱ እንዲመራ አድርጓል ።
የካፊቾ ልጆች በአዲሳአባ ፍትህ ቢሮ ሃላፊው ጸጋዬ ሀ/ ማርያም አማካኝነት ጓደኞቼ ነበሩ። በወር አንድ ቀን (ቅዳሜ ከሰአት)የጥሬ ስጋ የመብላት ማህበር ነበራቸው። እኔም ሳላቋርጥ እሳተፍ ነበር። ዛሬም ድረስ የጥሬ ስጋ ነገር ሲነሳ የቀድሞ ወዳጆቼ በአይኔ ላይ ይሄዳሉ። ካፊቾዎች ለጥሬ ስጋ እብዶች ናቸው። የዛሬን አይበለውና ቡና ቁርስ ላይ ሳይቀር ይቀርብ እንደነበር ሲያወጉ ሰምቻለሁ።
ይህ ማህበር መብላትና መጠጣት ብቻ ሳይሆን የሃገሪቷን ፓለቲካ ጭምር ይበልታል ። በአብዛኛውም የማህበሩ ኢ – መደበኛ ሊቀመንበር የሆነው ብርሐኑ አዴሎ በሚያቀርበው ወግ ጊዜው ያልፉል። ብርሐኑ የአቶ መለስን ጓዳ ጐድጓዳ ከማወቁም ባሻገር በወይዘሮ አዜብ ትእዛዝ ራሱ” ድርጅቱን!” ይሰልል ነበር። አንድ ጊዜ ” X” የምትባል እንስት ባለሥልጣን ከድርጅቱ ጋር የውጭ ጉዞ ተመቻችቶላት ብርሽ ባቀረበው ቅድሚያ ሪፓርት እንድትቀር ተደርጓል ።
ብርሀኑ በሐገሪቱ የወጡ አፉኝ ህጐች መሪ ተዋንያን ነበር። የፀረ ሙስና፣ የመያዶች ፣ የሚዲያ ፣የሽብርተኝነት ፣ የፓርላማ አባላት የስነምግባር አዋጅ፣ የምርጫ ቦርድና ፓለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ …ወዘተ በእሱ በኩል ያለፉ የአቶ መለስ ትሩፋቶች ናቸው።
ብርሐኑ በእሱ ፊርማ አሊያም የቃል ትእዛዝ በርካታ ሚኒስትሮችና ባለስልጣናትን ከስልጣን አባሯል ። ሚኒስተር አሰፉ ካሲቾ፣ ሚኒስትር ሂሩት ዴሌቦ፣ ሚኒስትር መፎሪያት፣ ም/ ሚኒስትር ስመኝ ውቤ… ከብዙ ጥቂቶቹ ናቸው። ለምን ፣ እንዴት፣ በምን መልኩ አባረራቸው?
ብርሐኑ አዴሎ የሐይለማርያም ወደ ስልጣን መምጣት ላይ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። ሐይሌ የህውሐት አካሄድ ግራ ሲገባውና ሆድ ሲብሰው ያግዘውና ያጽናናው ነበር። የደቡብ ክልል ፕሬዝዳንት ብርሐኑ አዴሎ ነው እስኪባል ድረስ!
ብርሐኑ ባለሥልጣናት የገቡበትን ሙስና እንዲያጣሩ ከተመደቡት ካድሬዎች አንዱ ነበር። የአጣሪ ኮሚቴው ሰብሳቢ ሐይለማሪያም ሲሆን ከአምስቱ አባላት ሦስቱ የካፊቾ ልጆች ነበሩ። ይህ ቡድን በርካታ ባለስልጣናት እንዲታሰሩ የውሳኔ ሐሳብ ለአቶ መለስ አቅርቦ ነበር። ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ዛሬ ከሀይለማርያም ጋር የውስጥ ሱሪ መቀያየር የቀራቸው አርከበ እቁባይ ነበር።
ብርሐኑ በትክክልም የስነ ምግባር ችግር አለበት። ጢንቢራውን እስኪስት ለሊቱን ሙሉ ይጠጣል። ሰክሮ ከቱቦ ስር የተገኘበትም ጊዜ ብዙ ነው። ሆዱ ያባውን ብቅሉን ሲጋት ያወጣዋል። በዚህ ምክንያት በየወሩ ሁለት ሶስት ቀናት አልጋው ላይ ይውላል። የካፊቾ ልጆች ቢመክሩትም አይሰማም። ፀፀቱ ከሚያገኘው ምክር ገዝፎ ይታየዋል።
ርግጥም እነ እስክንድር ፣በቀለ፣ ርዕዬት ፣ ኦልባና፣ አንዷለም ፣ አበበ ቀስቶ፣ ዞን ዘጠኞች ፣ ተመስገን ደሳለኝ… ወዘተ ረፍት የሚሰጡ አይደለም። እሱ የጳፉቸው እኛ ያስተጋባናቸው አፉኝ ህጐች ሰለባ ስለሆኑ ። ርግጥም አርከበ የሐይሌን እጅ ብእር እያስጨበጠ ማስፈረሙ የሚያስተኛ አይደለም። ይህ አድርባይነት የወለደው ሎሌነት የት ያደርስ ይሆን?… ዳግም ዶሮ ወጥ እንዳያሸክም ፀሎታችን ይሁን !!

Filed in: Amharic