>

በአዲስ አበባ  በኦሮሚያ ልዩ ኃይል የታገዘ ህገወጥ የቤት ፈረሳ ነዋሪዎቹን ለምሬት ዳርጓል ....! (ጽናት ሚድያ)

በአዲስ አበባ  በኦሮሚያ ልዩ ኃይል የታገዘ ህገወጥ የቤት ፈረሳ ነዋሪዎቹን ለምሬት ዳርጓል ….!

ጽናት ሚድያ


ከኦሮሚያ ዉጭ የሆኑትን ተወላጆች  ለማባረር ዛሬ ሌሊት ታህሳስ 25/2015 ዓ/ም 11:00 ሰዓት ጀምሮ ለቡ ገብሬኤል አካባቢ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል የታገዘ ህገወጥ የቤት ፈረሳ እየተደረገ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል  ።

እንቁ ገብርኤል በተለምዶ ለቡ ባቡር ጣቢያ አካባቢ ተብሎ በሚጠራው 20 ዓመት እና ከዚያ በላይ የኖሩበትን ቤት መጤ በማለት ከኦሮሚያ ዉጭ የሆኑትን ተወላጆች ቤት በማፍረስ ለማባረር ዛሬ ሌሊት 11:00 ሰዓት ጀምሮ የኦሮሚያ መንግስት አፍራሽ ኃይል አቋቁሞ እያፈረሰ መሆኑን ከቦታው ለፅናት ሚዲያ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ይህን ሂደት አስቀድመን  ለማስቆም  ለፌደራል መንግስት ለማመልከት ወደ ቤተ-መንግስት  ገብተን የተሰጠን ምላሽ ከክልሉ መንግስት ጋር ጨርሱ የሚል መልስ ነው። የክልሉ መንግስት ደግሞ አንድም መጤ እንዳይኖር ብሎ አቶ ሽመልስ አስተላልፏል በሚል ምንም ተቀባይነት አተናል። አልፎ ተርፎ ወደ ሚዲያ ኢቢሲ የብዙኸን መገናኛ ብናናግር የደረሰለን የለም። ማፍረስ የጀመሩት ሌሊት 11:00 ሰዓት ነዉ።

https://fb.watch/hPZz4U8D_Q/

Filed in: Amharic