>

ሰበር የጦርነት ዜና  (መምህር ዘመድኩን በቀለ)

ሰበር የጦርነት ዜና

መምህር ዘመድኩን በቀለ

“…አትሌት ደራርቱ ቱሉ መቀሌ ገባች፣ ጌቻ ለተ ሰንበት ተሳሳሙ፣ ነዳጅ ስድሳ ምናምን ብር ገባ፣ በአዲስ አበባ ዙሪያ የዐማራ ቤቶች እየፈረሱ ነው፣ የቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኢትዮጵያ መጡ፣ ኦህዴድና ብአዴ እየተፋጩነው፣ መቀሌ መግባት እንጂ መውጣት ተከልክሏል፣ የስልክ አገልግሎትም በተወሰነ ቦታ ተቋርጧል ብላብላ ዓይነት ዜናዎችን ወደ ሕዝቡ በመልቀቅ ካደነዘዙ በኋላ…

“…በዛሬው ዕለት በራያ ምድር በሰሜን ወሎ፣ በኩኩፍቱና በአካባቢ ባሉ ቀበሌዎች ላይ ወያኔ ጦርነት ከፍታ በድጋሜ ይዛዋለች። ሰሞኑን የዐማራ ልዩ ኃይል በአስቸኳይ እንድትወጣ ብሎ መንግሥት ለምን ልዩ ኃይሉ እንዲወጣ እንዳስደረገው አሁን ግልጽ  እየሆነ መጥቷል። በቀደም መንግሥት ቢያዘንም መከላከያውን አምነን ከክልላችን መሬት ላይ አንወጣም ብለው የነበሩት የዐማራ ልዩ ኃይሎች ዛሬ ከህውሓት ኃይል ጋር ገጥመው ሲዋጉ ውለዋል።

“…መከላከያው የዐማራ ልዩ ኃይል እንዲወጣ አድርጎ ይዞት የነበረውን ስፍራ በሙሉ ለህወሓት ጦር ለቅቆ በማፈግፈጉ ምክንያት አሁን ላይ የዐማራ ልዩ ኃይል ለቆ የወጣባቸውን ቦታዎች በሙሉ ወያኔ ተቆጣጥራዋለች። አላማጣ አካባቢ ያለውና ሰሞኑን ውጣ ሲባል አልወጣም ብሎ የነበረው የዐማራ ልዩ ኃይል ከትናንት ጀምሮ ወደ ትግራይ የሚገባውን የእርዳታም ይሁን ማንኛውንም የጭነት የጫነ መኪና አግዷል። የቆቦ ከተማ በአሁን ሰዓት በተሽከርካሪዎቹ እገዳ ምክንያት በጣም ተጨናንቃለች። ይሄ ጉዳይ ይቀጥላል ወይስ የሚለውን ማየት ነው።

“…ሰሞኑን የለጠፍኩላችሁንና አዲስ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ወደ ትግራይ በቀን እየጎረፉ ይታይ የነበረውን እኔ መረጃውን ካወጣሁት መንግሥት ሠራዊቱን ወደ ትግራይ ማጓጓዙን ትቶ በሌሊት ሲያጓጉዝ ሲያጓጉዝ ማደሩም ተመልክቷል።

“…ዐማራ ለዋንጫ ጨዋታው ተዘጋጅ…!!

Filed in: Amharic