>
5:13 pm - Monday April 20, 6612

ያርበኝነት ዘመን ትምህርት ለፋኖ ዘመን! ውሻን በርግጫ መምታት እንካ ሥጋ ማለት ነው  (መስፍን አረጋ)

ያርበኝነት ዘመን ትምህርት ለፋኖ ዘመን

ውሻን በርግጫ መምታት እንካ ሥጋ ማለት ነው  

መስፍን አረጋ

ጭራቅ አሕመድ ባራት ዓመት የስልጣን ዘመኑ በቀጥታና በተዛዋሪ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አማሮችን ጨፍጭፏል፣ አስጨፍጭፏል፡፡  ጭራቁ ግን በኦነጋዊነት ያበደ፣ በልቶ የማይጠግብ የቀን ጭራቅ ስለሆነ፣ አማራን ሙልጭ አድርጎ እስከሚብላ ድረስ አይጠረቃም፣ አይረካም፡፡  አማራን በልቶ ቢጭርስ ደግሞ ምዕራባውያን ጌቶቹ ዝንቡን እሽ እንድማይሉት በስካሁን ድርጊታቸው በግልጽ አሳውቀውታል፡፡  በተለይም ደግሞ የተለያዩ ሕዝቦችን (ቀይ ህንዶችን፣ ጥቁር አውስትራሊያኖችን …) ከምድረግጽ ያጠፋው የእንግሊዝ መንግስት::  ግልጽ በሆነ ምክኒያት የእንግሊዝ መንግስት፣ ለነጻነቱ ቀናዒ የሆነውን፣ በማንነቱ የሚኮራውን፣ ነጭን ከመጤፍ የማይቆጥረውን የአማራን ሕዝብ አምረሮ የሚጠላ ያማራ ሕዝብ ዘላለማዊ ጠላት ነው፡፡  በመሆኑም የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ቢጠፋ፣ ያፍሪካ አንድነት ምልክት የሆነችው አዲሳባ ደግሞ አማራና አማራዊነት ሙሉ በሙሉ የተወገደባት፣ አፍርቃዊ አፓርታይድ የነገስባት፣ የአፍሪቃውያን በጎጥ የመከፋፈል ዋና ምልክት የሆነች፣ አፍሪቃውያንን አንገት የምታስደፋ፣ አሳፋሪ ኦነጋዊ ከተማ ብትሆን ደስታውን እንደማይችለውና አስፍላጊውን እርዳታ እንደሚያድርግ፣ ጭራቅ አሕመድ ይገንዘባል፡፡  የሚያስገነዝቡት ደግሞ ጭራቅ አሕመድን በኦሮሙማ አደቁነው ያቀሰሱትና አሁን ደግሞ እንደ አንዝርት የሚያሾሩት ሌንጮ ለታን የመሳሰሉት ኦነጋዊ ጃርሳወች ናቸው፡፡   

ስለዚህም ጭራቅ አሕመድ እየተዘጋጀ ያለው ከወያኔ ጋር በስውር መተባበሩ ቀርቶ በግልጽ በመተባበር በአማራ ሕዝብ ላይ ግልጽ ጦርነት ከፍቶ፣ ምዕራባውያን ጌቶቹ በሰጡትና በሚሰጡት ዘመናዊ መሣርያ በተለይም ደግሞ በንቦቴ (drone) እየነቦተ የአማራን ሕዝብ ድምጥማጡን ለማጥፋት ነው፡፡ ወያኔ ከመቀሌ ወልድያ፣ ከወልድያ ደሴ፣ ከደሴ ኮምቦልቻ፣ ከኮምቦልቻ ሸዋሮቢት፣ ከሸዋሮቢት ደብርብርሃን በመራመድ፣ ያማራን ክልል ባምስት ርምጃ ብቻ ሙሉ በሙሉ ያቆራርጠበት ኦነጋዊ ትርዒት ሚስጥር የሆነብህ ቡልኻ አማራ ካለህ፣ አውቅህ ያልትኛህ ካልሆንክ በስተቀር አሁን ግልጥልጥ ሊልልህ ይገባል፡፡  ኦነግና ወያኔ በሕቡዕ እየተባብሩ ያን ያህል ጥፋት ባማራ ሕዝብ ላይ ከፈጸሙ፣ ምዕራባውያን ጌቶቻቸው ባዘዟቸው መሠረት በግልጽ ሲተባብሩ ደግሞ በአማራ ሕዝብ ላይ ምን ሊፈጽሙ እንደተዘጋጁ መገመት አያዳግትም፡፡  

ስለዚህም የምዕራባውያን ሙሉ ድጋፍ ያለውን፣ በጭራቅ አሕመድ የሚመራውን፣ የኦነግንና የወያኔን ፀራማራ ጣምራ ጦር  ፊት ለፊት መግጠም፣ የእሳት ራት ከመሆን ውጭ ፋይዳ የሌለው አጉል ጀብደኝነት ነው፡፡  ባጭሩ ለመናገር ጭራቅ አሕመድ እየቋመጠ ያለው ዘመናዊ መሣርያ እስካፍንጫው የታጠቀውን የኦንግንና የወያኔን ጣምራ ጦር ይዞ፣ የነፍስ ወከፍ መሣርያ ካነገበው ከፋኖ ጋር ፊት ለፊት ለመግጠምና፣ ፋኖን በዚያውም መላውን የአማራን ሕዝብ የዶግ ዐመድ ለማድርግ ነው፡፡ 

የደፈጣ ውጊያ አስፈላጊነት

በሰው ኃይልና በመሣርያ ብዙ እጥፍ የሚበልጥህን ጠላት አንተ በመረጥከው መቸት (መቸ እና የት) እንጅ እሱ በመረጠው መቸት አትገጥመውም፡፡  ይህ ማለት ደግሞ ሌላ ምንም ማለት ሳይሆን የደፈጣ ውጊያ ማለት ነው፡፡  ስለዚህም የፋኖ ጦር በጭራቅ አሕመድ ከሚመራው የኦነግና የወያኔ ጣምራ ጦር ጋር መፋለም ያለበት በደፈጣና በደፈጣ ብቻ ነው፡፡  ለዚህ የደፈጣ ውጊያ ግብአት ይሆነው ዘንድ ደግሞ ያያቶቹን ያርበኝነት ትግል ማስታወሱ ብቻ ይበቃዋል፡፡

ያርበኝነት ዘመን ፋኖወች ጣልያንን ያርበደብዱ የነበሩት፣ ያገራቸውን ዱር፣ ተራራና ሸንተርር ተገን በማድርግ መሠረታዊ የደፈጣ ውጊያ ስልቶችን በመጠቀም ነበር፡፡  ምናልባትም ደግሞ እነዚህን የደፈጣ ውጊያ ስልቶች ለመጥቀም የመጀመርያወቹ እነሱ ሳይሆኑ አይቀሩም፣ ያገራችን ታሪክ ከጥንት ከጠዋቱ ጀምሮ የጦርነት ታሪክ ነውና፡፡  ግራም ነፈሰ ቀኝ፣ የቻይናው ማኦ ዜዶንግ በጽሑፍ ስላስቀመጣቸው ብቻ በሱ ስም የሚጠሩት፣ የደፈጣ ውጊያ የሚካሂድባቸው ሦስቱ ስልታዊ ትእዛዞች (The Three Tactical Commandments) የሚከተሉት ናቸው፡፡ 

  1. ጠላት ሲበረታ አፈግፍግ
  2. ጠላት ሲዳከም አጥቃ
  3. ጠላት ሲያርፍ አውክ

ያርበኝነት ዘመን ፋኖወች ከመደበኛ ውጊያ ወደ ደፈጣ ውጊያ የዞሩት ጣልያን አዲሳባን ከተቆጣጠረ በኋላ ነበር፡፡  ባሁኑ ጊዜ ደግሞ አዲሳባን የተቆጣጠረው አማራን ከምድረግፅ ለማጥፋት የተነሳው የጭራቅ አሕመድ ኦነግ ነው፡፡  ይህ ፀራማራ አውሬ ካዲሳባ የሚወጣው ደግሞ ከገጠር ወደ አዲሳባ በሚያመራ፣ በደፈጣ ውጊያ ጀምሮ እያደገ ሂዶ ወደ መደበኛ ውጊያ በሚሸጋገር የነጻነት ጦርነት ነው፡፡         

ፀራማራ ሥላሶችና ቤዛማራ ሥላሶች

የአማራ ሕዝብ የሕልውና ጠላቶች ወያኔ፣ ኦነግና ብአዴን የሚባሉ ሦስትም አንድም የሆኑ ፀራማራ ሥላሶች ናቸው፡፡  የአማራ መድሕን የሚሆኑት ደግሞ በነዚህ ፀራማራ ሥላሶች አንፃር የሚቆሙ ቤዛማራ ሥላሶች ናቸው፡፡  እነዚህ ቤዛማራ ሥላሶች ደግሞ ሳተና ፋኖደመላሽ ፋኖ  እና ደጀን ፋኖ ሊባሉ ይችላሉ፡፡  

የሳተና ፋኖ ሚና 

በደፈጣ ውጊያ ላይ የፋኖ የመጀመርያ ግብ መሆን ያለበት፣ ገጠሩን ያማራ ክልል መሠርት አድርጎባስፈላጊው መቸት አስፈላጊውን ጥቃት እያደረሰ፣ በጭራቅ አሕመድ የሚመራው የወያኔና የኦነግ ጥምር ጦር ያለ አጃቢ (ኮንቮይ) እንዳይጓዝ በማስገደድ፣ የሰው ኃይል፣ የስንቅና የትጥቅ አቅርቦቱን በከፍተኛ ደረጃ ማስተጓጎል ነው፡፡

በድንገት እየተውረወረ ባስፈላጊው መቸት አስፈላጊውን ጥቃት የሚፈጽመው የፋኖ ክፍል ሳተና ፋኖ (commando fanno) ሊባል ይችላል፡፡  ሳተና ማለት የሚሳትን፣ ብርቱ፣ ሯጭ፣ ፈጣን፣ ቀልጣፋ ማለት ነው፡፡  በመሆኑም ሳተና ፋኖ (commando fanno) ማለት ተወርዋሪ ፋኖ ወይም ፈጥኖ ደራሽ ፋኖ ማለት ነው፡፡  ሳተና ፋኖ ባውሎ ነፋስ ይመሰላል፡፡  አውሎ ነፋስ ባልታሰበበት ሰዓት ካልታሰበበት አቅጣጫ በድንገት ነፍሶ፣ የሚጠራርገውን ጠራርጎ ወዳልታሰበበት አቅጣጫ  ይነጉዳል፡፡  ሳተና ፋኖም እንደዚሁ፡፡  ሳተና ፋኖ በመብረቅም ሊመሰል ይችላል፡፡  መብረቅ ሲበርቅ እንጅ መቸና በየት በኩል እንደሚበርቅ አይታወቅም፡፡  ከበረቀ በኋላ ደግሞ ዓይን ቢጨፍኑ ዋጋ የለውም፡፡  ሲበርቅ ቢጨፍኑ ከመወጋት አይድኑ፡፡  

የደመላሽ ፋኖ ሚና 

ደመላሽ ማለት የደም ብደር ከፋይ፣ ተበቃይ፣ ገዳይን ገዳይ ማለት ነው፡፡  ስልዚህም ደመላሽ ፋኖ ማለት ሻቢያ ፈዳይ ይለው የነበረው ዓይነት ነው፡፡   

የአማራ ሕዝብ ዋና ጠላት ጭራቅ አሕመድ ቢሆንም፣ ይህ ጭራቅ አማራን የሚዘነጣጥልባቸው ጥርሶቹ ግን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ብአዴኖች ናቸው፡፡  የብአዴን አንኳሮች (በረከት ስምዖን፣ አዲሱ ለገስ፣ ተፈራ ዋልዋ፣ ደመቀ መኮንን፣ ተመስግን ጡሩነህ፣ ሰማ ጡሩነህ፣ ግርማ የሽጥላ፣ ይልቃል ከፋል ወዘተ…) አማራ መኻል ቢወለዱም በንዑስ ማንነታቸው ሳቢያ አማራን ከኦንጋውያንና ከወያኔወች በላይ የሚጠሉ ፀራማሮች ናቸው፡፡ የአማራ ሕዝብ ለዚህ ሁሉ ውርደት የተዳረገው በወያኔና በኦነግ ኃይል ሳይሆን፣ እነዚህ አንኳር ብእዴኖች የአማራን ሕዝብ በገፍና በግፍ እያስጨፈጨፉ በራሱ በአማራ ሕዝብ መኻል ዝንባቸው እሽ ሳይባል ተኩራርተው እንዲኖሩ ስለተፈቀደላቸው ብቻና ብቻ ነው፡፡  

ስለዚህም የደመላሽ ፋኖ ሚና አማራን እያረዱና እያሳረዱ ያሉትን የወያኔ፣ የኦነግና የብአዴን አመራሮች፣ መውጫ መግቢያቸውን አጥንቶ፣ ባስፈላጊው መንገድ አደብ እንዲገዙ ማድረግ ነው፡፡ በተለይም ደግሞ አማራን የሚጭፈጭፉና የሚያስጭፍጭፉ ብአዴኖችና ዘመድ አዝማዶቻቸው የትም ይሁኑ የት የሰላም እስትንፋስ እንዳይተነፍሱ ማድረግ ነው፡፡   ባጭሩ ለመናገር የደመላሽ ፋኖ ሚና የአማራን ደም በደም ማጠብ ነው፣ ደም የሚጠራው በደም ነውና፡፡  

የደጀን ፋኖ ሚና

ደጀን ማለት በስተኋላ ሁኖ የሚጠብቅ፣ የኋላ ዘበኛ፣ ረዳት ሠራዊት ማለት ነው፡፡  ስለዚህም የደጀን ፋኖ ሚና ነጻ በወጡ ቀጥናወች ላይ ተሰማርቶ የቀጠናወቹን ሰላምና መረጋጋት ማስከበር ነው፡፡  ተጨማሪ ሚናው ደግሞ ለተወርዋሪ ፋኖ እና ደመላሸ ፋኖ የሠራዊት ምንጭ መሆን ነው፡፡  ነጻ የውጡ ቀጠናወችን በማስተዳደር ረገድ ደግሞ የሚከትሉትን የማኦ ዜዶንግን አሥሩ ስነስርዓታዊ ትዕዛዞች (The Ten Disciplinary Commandments) ማክብር የግድ ነው፡፡

  1. ያለቃህን ትእዛዝ ቅንጣት ሳትጠራጠርና ላፍታ ሳታንገራግር ፈጽም፡፡
  2. የሕዝብን ንብረት አትንካ፣ መርፌም ብትሆን፡፡
  3. ከሕዝብ ስጦታ አትቀበል፣ ክርም ብትሆን፡፡
  4. ከሕዝብ ምንም ነገር አተዋስ፣ የግድ መዋስ ካለብህ ደግሞ የተዋስከውን ወዲያውኑ ተጠቅመህ በተዋስክበት ሁኔታ መልስ፣ ካበላሸህም ትክክለኛ ዋጋውን ክፈል (አልቀበልም ብትባል እንኳን በትሕትና አሳምነህ ሳትከፍል አትንቀሳቀስ)፡፡
  5. ከገበያም ሆነ ከየትም ቦታ ለምትገዛቸው ወይም ለምትሸምታቸው ነገሮች ሁሉ ተገቢ ዋጋቸውን ክፈል (አልቀበልም ብትባል እንኳን በትሕትና አሳምነህ ሳትከፍል አትንቀሳቀስ)፡፡
  6. በውጊያ ወቅት ላወደምከው ወይም ላጠፋኻው ወይም ለጎዳኻው የሕዝብ ሐብት፣ ንብረትና ሂወት ተገቢውን ካሳ ሙሉ በሙሉ ክፈል (አልቀበልም ብትባል እንኳን በትሕትና አሳምነህ ሳትከፍል አትንቀሳቀስ)፡፡
  7. የውጊያ ግርግር ለዘራፊ ያመቻልና፣ በግርገሩ የተዘረፈን፣ የተበዘበዘን ወይም የተመዘበረን የሕዝብ ሐብትና ንብረት አስመልስ፣ ማስመለስ ካልቻልክ ደግሞ ተገቢውን ካሳ እራስህ ክፈል (አልቀበልም ብትባል እንኳን በትሕትና አሳምነህ ሳትከፍል አትንቀሳቀስ)፡፡
  8. ሴት፣ ወንድ፣ ሕጻን፣ አረጋዊ ሳትል ማናቸውንም ሰው ስታናግር ሁልጊዜም በትሕትና አናግር፣ በተቻለህ መጠን ደግሞ እርዳ፡፡
  9. ልጃገረድ፣ ኮረዳ፣ ባለትዳር፣ ፈት፣ ጋለሞታ፣ ሴታአዳሪ ሳትል ሴትን አክብር እንጅ በጭራሽ እንዳትደፍር፡፡  ግዳጅ ላይ እስካለህ ድረስ ከሩካቤ ሥጋ ፈጽሞ ታቀብ፡፡
  10. ምርኮኛም ሆነ እስረኛ አታጎሳቁል፣ በተቻለህ መጠን ተንከባከብ፡፡

አንድም ሦስትም ቤዛማሮች 

የአማራ መሠረታዊ ጠላቶች ወያኔ፣ ኦነግና ብአዴን አንድም ሦስትም እንደሆኑ ሁሉ፣ የአማራ ቤዛ የሆኑት ደመላሽ ፋኖ፣ ተወርዋሪ ፋኖ እና ደጀን ፋኖ አንድም ሦስትም መሆን አለባቸው፡፡  የአካል ብልቶች ብዙ ቢሆኑም፣ የአንድ በአንድ ለአንድ ናቸው፡፡  ዓይን ጆሮን ንቆ አያስፈልገኝም ቢል፣ የደንቆሮ ዓይን ይሆናል፡፡  ጆሮ ዓይንን ንቆ አያስፈልገኝም ቢል፣ የእውር ጆሮ ይሆናል፡፡  እጅ እግርን ንቆ አያስፈልገኝም ቢል፣ የስንኩል እጅ ይሆናል፡፡  እግር እጅን ንቆ አያስፈልገኝም ቢል፣ የዱሽ እግር ይሆናል፡፡  የፋኖ መሪወች የመጀመርያው ተግባር ሁሉም የፋኖ ክፍሎችና አባሎች ላንድ ዓላማ ባንድነት የቆሙ አንድ መሆናቸውን በማሳመን በመካከላቸው ፋኗዊ ፍቅርና መከባበር እንዲያደር በማድረግ አንተ ትብስ አንቺ ትብስን ማስፈን ነው፡፡  

አማራና ኤርትራ፣ ላማራ ሕልውና የወልቃይት ወሳኝነት

በዝቅትኝነት ስሜት ያብዱት ወያኔና ኦነግ፣ አማራን የሚጠሉት አማራ በመሆኑ ብቻ ስለሆነ፣ እንሱን በተመለከተ ያማራ ሕዝብ ያለው ምርጫ ወይ እነሱን ማጥፋት ወይ በነሱ መጥፋት ብቻ ነው፡፡  በሌላ በኩል ግን በማንነታቸው የሚኮሩት ኤርትሬወች ባጠቃላይ ሲታዩ አማራን የሚጠሉት አማራ ቅኝ ገዛን ከሚል በተሳሳተ አመለካከት ላይ ከተመሠረተ የቁጭት ስሜት ብቻ ነው፡፡  በሌላ አባባል ኤርትሬወች የሚጠሉት አማረኛ ስለሚናገር ብቻ የአማራ ነው የሚሉትን የጦቢያን መንግስትና አስተዳደር እንጅ የአማራን ሕዝብ አይደለም፡፡  

ስለዚህም አማራና ኤርትራ በእከክልኝ ልከክልህ ወይም ሰጥቶ የመቀበል መርሕ መሠረት በወያኔና በኦነግ ላይ ሊተባብሩ ይቸላሉ፡፡  ባሁኑ ጊዜ ደግሞ ይህ ትብብር ይበልጥ የሚጠቅመው በወያኔና በኦነግ አጣብቂኝ ውስጥ ለገባው ለፋኖ ነው፡፡  ፋኖ ይህን ትብብር ከፈጸመ ወልቃይት የደጀን ፋኖ ዋና መናኸርያ፣ የሳተና ፋኖ ዋና መውርውርያ፣ የደመላሽ ፋኖ ዋና መሰማርያ ትሆናለች፡፡

አይቀሬው ያማራ ድል

ጭራቅ አሕመድ የራሱን ሽንፈት ራሱ ማሕፀን ውስጥ ፀንሷል፡፡  ይህን ያደረገው ደግሞ በሁለት ሁኔታወች ነው፡፡ 

የመጀመርያው ሁኔታ የጭራቅ አሕመድ ጦር አስኳል የኦነግ ሠራዊት መሆኑ ነው፡፡  የኦነግ ሠራዊት ግን ዕድሜው ከግማሽ ምዕተ ዓመት ያለፈ አዛውንት ሠራዊት ቢሆንም፣ በዚህ ረዥም እድሜው ግን፣ ተከላካይ የሌላቸውን የገጠር ቀበሌወችና አናሳ ከተሞች በድንገት አጥቅቶ፣ የደም ጥማቱን ለማርካት የሚያርደውን አርዶ ባፋጣኝ ከመሸሽ ባሻገር፣ በታሪኩ ካንድም ባላንጋራ ጋር በግንባር ገጥሞም ሆን አሸንፎ አያውቅም፡፡  የወያኔው ሰየ አብርሕ ‘’ኦነግን ከሳንቲም አንቆጥረውም” ሲል የሠራዊቱን ምንነት በትክክል ገልጾታል፡፡   ስለዚህም የኦነግ መንጋ ሠራዊት እንደ ተልባ ቢንጫጫም ባንድ ሙቀጫ ለመውቀጥ የሽዋ ፋኖ ብቻ ይበቃል፡፡     

ሁለተኛው ሁኔታ ደግሞ ጭራቅ አሕመድ አማራን እጎዳልሁ ብሎ ዘመናዊ ጦሩን ሽሽት ማስተማሩ ነው፡፡  የጦር አዛዦቹን ደግሞ ታንኩን ባንኩን ጣጥለው የሚሸሹ ቱሪናፋወች በመሆናቸው ብቻ እስከ ፊልድ ማርሻልነት አድርሷቸዋል፡፡  አንዴ የሸሸ ሠራዊት ደግሞ መቸም ቢሆን ቁሞ አይዋጋም፡፡  

ስለዚህም ፋኖ ጊዜና ቦታ ጠብቆ የጭራቅ አሕመድን ጦር መኻሉ ላይ ደህና አርጎ ከቦቀሰው፣ እንደ እንቧይ ካብ ይፈራርሳል፣ ከፈራርሰበት የፈርጠጠ አዲሳባ ይደርሳል፣ አዲሳባ እንደደርሰ እጁን ያነሳል፣ መሣርያውን ይመልሳል፣ እንደ ወንጀሉ የጁን ይቀምሳል፡፡  አብናቶቻችን አዲሳባን ነጻ ለማውጣት አመስት ዓመት ፍጅቶባቸዋል፡፡  ፋኖ ራሱን ከፀራማሮች አጽድቶ፣ ነጻነቴ ወይም ሞቴ ብሎ ተግዝቶ፣ በተግቢው መንገድ የሞት ሽረት ትግል ካደርገ ግን ያጼ ዳዊትን ከተማ መልሶ ለመቆጣጠር ካመት በላይ አይፍጅበትም፡፡

Email:  mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic