>

ይጠየቅ ጠቅላዩ!

ይጠየቅ ጠቅላዩ!

ግዜ የሰጠውን
ስልጣን ተረክቦ
ሀገርን እየመራ
በቋንቋ  ገድቦ

በመደመር ክልል
ከንቱ ብልፅግና
እርሱ እየጋለበ
ህዝቡ ቀርቶ መና

ስርአት አልበኛ
ታጣቂ  በርክቶ
ሰላማዊውም  ህዝብ
እቤቱ  ለቆ  ውጥቶ

ፈርዶ  እንደጲላጦስ
እጅ እየታጠበ
ሰውን  በዘር መድሎ
መንገድ   ካስገደበ

ሁሉ የኛ  እያሉ
ሀገር አስፈራርሰው
በመደመር ቀመር
ታሪክን ቀልብሰው

በዘረኞች መንበር
በሀገር  ሲቆመር
የጥፋት  ሀይሎችን
ተወዳጅቶ   ሲኖር

ሀገር   የደፈሩ
አስሮ እየፈታ
የህዝብ  ተቆርቋሪን
በእስር   እየገታ

የባእድ  ባንዲራ
ምልክቱ   አድርጎ
የኢትዮጵያን ታሪክ
ሊያጠፋ  ፈልጎ

በጀትን   መድቦ
የእምንት ደጅ የነካ
በህዝቡ  ጉሮሮ
እንጨትን  እያሰካ

በችሎታ  ማነስ
ሀገር  አበጣብጦ
እኔን  ስሙ ብቻ
ምክር ቤት ተቀምጦ

ያ ነበር ስተቱ
ሰዎች ያልተረዱት
ድጋፍን ሲሰጡ
ቀድመው ያላወቁት

የቱ ነው  እድገቱ
የመደመር  ፋና
የተፈለሰፈው
የውሸት ብልፅግና

ዘወትር በየለቱ
ኑሮ እያሻቀበ
የሚመራውን ህዝብ
በተንኮል   ያስራበ

ህዝብ ያልተቀበለው
ህገመንግስት ይዞ
ካሸባሪ ሲውል
ብዙሀን አፍዝዞ

የሂሳቡ  ቀመር
አንድ ዘር  አንግሶ
ሁሉን መቀራመት
ከሆነ  አግበስብሶ

የድምሩ  ስሌት
መቀነስ ከሆነ
ይጠየቅ  ጠቅላዩ
ብላችሁ ተነሱ
ሀገር   ገድሏልና
ክንዳችሁን   አንሱ

ዘምሳሌ

Filed in: Amharic