>
5:26 pm - Saturday September 17, 1053

ሞገስ አስገዶምና አብርሃ ደቦጭ (ጦቢያን በታሪክ)

ሞገስ አስገዶምና አብርሃ ደቦጭ

ጦቢያን በታሪክ – ቴሌግራም


…..ሌሎቹ ተጠቃሾች ደግሞ በአዲስ አበባ ያደጉት ኤርትራውያን ሞገስ አስግዶም እና አብርኃ ደቦጭ ናቸው። ሞገስ እና አብርኃ የተፈሪ መኮንን ት/ቤት ተማሪዎች ሲሆኑ ጣልያንኛም ይችሉ ነበር። ሞገስ በፋሺስት ፖለቲካዊ ቢሮ ተቀጥሮ ይሠራ ነበር። አብርኃ ደግሞ በጀርማን ሌጋሲዮን ከሚሠራ ሰው ጋር ይኖር ነበር — ሥራ አልነበረውም በሰዓቱ። በማርሻል ግራዚያኒ ላይ የጣልያኑ ልዑል ልደት በሚከበርበት ቀን ቦምብ ለመወርወር ያሰቡት በአሁኑ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ነበር። ሞገስ እና አብርኃ ግራዝያኒ ቆሞ በዓሉ ሲከበር በሚያይበት ጋር ቀስ ብለው ተጠግተው ወደ 5 ሰዓት አካባቢ ወታደሮች ለከተማዋ የኔቢጤዎች እና ቀሳውስት ምግብ ሊያከፋፍሉ ሊወጡ ሲሉ ቦምቦቻቸውን ወረወሩበት። ከግቢው ወጥተው በመጀመሪያ ወደ ባላምባራስ አበበ ዓረጋይ የጦር ሰፈር ሄዱ። ከዚያም ወደ ሱዳን ድንበር — ነገር ግን እዛ ያልታወቁ ሰዎች ገደሏቸው።

ግራዚያኒ በተወረወሩበት ቦምቦች ሳቢያ 365 ቁስሎች ነበሩት። ጣልያኖች እስካሁን በሚደረገው የኢትዮጵያውያን ደፈጣ ውጊያ እጅግ እየበሸቁ ቆይተው አሁን ደግሞ እንዲህ ሲደረግ ሞራላቸው ወደቀ። ወዲያው ነው ወታደሮቻቸው ማንንም እንዲገድሉ carte blanche ነፃ ፈቃድ የተሰጣቸው።

የሞገስን ቤት ፍለጋ ሲሄዱ የጣልያን ባንዲራ መሬት ላይ ተጥሎ ሚስማር እና ቢላዋ ተሰክቶበት አገኙ። የሞገስ ሚስት ደብረ ሊባኖስ ሄዳ ተሸሽጋ ነበር — ጣልያኖች ተከትለዋት ሄደው መነኮሳትን እና እዛ ያገኙትን በሙሉ ጨፈጨፉ። በሦስት ቀናት 30 ሺህ ኢትዮጵያውያንን ነው የገደሉት። ከዚያም ለወራት እንዲሁ ሲገድሉ ሲያሳድዱ ነበር። ከጣልያን ወረራ በፊት ዘመናዊ ትምህርት የተማሩ ኢትዮጵያውያን ናቸው ኢትዮጵያዊ ስሜት የሚቀሰቅሱት ብለው እነሱንም ገድለዋል።

ፀሐይ ብርሃነሥላሴ፡ ኢትዮጵያዊ ጦረኝነት

ገጽ 260—261

Filed in: Amharic